Harari Police Commission

Call Directions Contact the organization

Harari Police Commission Harari Police Commission
(1)

1.1 የሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን አመሰራረት /Establishemnt/

በአዋጅ ቁጥር 38/1996 አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ (2)(ረ) መሰረት የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በደንብ ቁጥር 38/1996 ለሀረሪ ክልል ፕሬዝዳንት ተጠሪ ሆኖ የተቋቋመ የሀረሪ ክልላዊ መንግስት መስሪያ ቤት ነዉ፡፡ ኮሚሽኑ አንድ ዋና ኮሚሽነር እና ሁለት ምክትል ዋና ኮሚሽነር የሚመራ ነው።

1.2.የሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን ራእይ፤ ተልእኮ እና እሴት

ራዕይ /vision

ክልላችን ሠላምና ደህንነት የሠፈነባትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ክልል ሆና ማየት ነው

ተልእኮ /mission

የሀገሪቱንና የክልሉን ህገ-መንግስትና ሌሎች ህጎችን አክብሮ በማስከበርና የህብረተሠቡን ተሳትፎ በማሳደግ ወንጀልንና የትራፊክ አደጋን መከላከል፤ ተፈፅሞም ሲገኝ በህግ አግባብ አጣርቶ አጥፊዎች ተገቢውን የህግ ውሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ የክልሉን ህብረተሰብ ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ፤

የሐረሪ ፖሊስ የተተከሉ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞችን የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ ሥራ አከናወነ። የአረንጓዴ ዐሻራ የተተከሉ ችግኞች በሕይወት እንዲቆዩና የታለመላቸውን የአካባቢ የኢኮኖሚና የማኅበ...
04/10/2026

የሐረሪ ፖሊስ የተተከሉ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞችን የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ ሥራ አከናወነ።

የአረንጓዴ ዐሻራ የተተከሉ ችግኞች በሕይወት እንዲቆዩና የታለመላቸውን የአካባቢ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ ከተከላ በኋላ ቀጣይነት ያለው የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ ተከናውኗል።

በዚህ መሠረት የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ቀደም ሲል በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተተከሉ ችግኞችን የውሃ ማጠጣትና የእንክብካቤ ሥራ አከናውኗል።

በሐረሪ ክልል የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 70 በመቶ ያህሉ ለምግብ ዋስትናና ለኢኮኖሚ ጥቅም የሚውሉ የፍራፍሬ ዝርያዎች ሲሆኑ 30 በመቶው ደግሞ የደን ዛፎችና ለእንስሳት መኖ የሚውሉ ዕፅዋት ናቸው።

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአካባቢ ጥበቃንና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ከማጠናከር ባሻገር የህብረተሰብ ተሳትፎን የሚያጎለብት አገራዊ ንቅናቄ መሆኑ ተገልጿል።

ለመጪው ትውልድ ጤናማና አረንጓዴ አካባቢ ማስረከብም የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት መሆኑ ተጠቁሟል።
ችግኞች የደን ሽፋንን ለማሳደግ የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ የውሃ ሀብትን ለማጎልበትና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም አረንጓዴ ዐሻራ የአካባቢ ጥበቃ ተግባር ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚ ዕድገት ለምግብ ዋስትናና ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያበረክት ዘላቂ የልማት ንቅናቄ መሆኑ ተጠቁሟል።

በመሆኑም የተተከሉ ችግኞች እንዲፀድቁና የተጠበቀውን ጥቅም እንዲያስገኙ የውሃ ማጠጣት የአረም ማስወገድና ሌሎች የእንክብካቤ ሥራዎች በቀጣይነት መከናወን እንዳለባቸው ተገልጿል።

ሁሉም ዜጎችም በተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ ላይ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በሐረር ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኞች መተከላቸው የሚታወቅ ሲሆን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ንቁ ተሳትፎ ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህ የውሃ ማጠጣትና እንክብካቤ መርሐ ግብር ላይ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር አህመድ አብዲ የወንጀል መከላከል ዘርፍ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ነገራ ዱፌራ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ያህያ አብደሰላም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና የፖሊስ አባላት እና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የፖሊስ ተመሪዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ ፦ ሳጅን ዮሐንስ መካ

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2019 ዓ.ም. የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ አፈጻጸምና የ2ኛ ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ ...
03/10/2026

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2019 ዓ.ም. የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ አፈጻጸምና የ2ኛ ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ዕቅዱ ከክልል እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ባሉ መዋቅሮች በተቀናጀ አሠራር የሚፈጸምበት ሁኔታ ቀርቦ በአፈጻጸሙ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ ተግባራትን “በአንድ ዕቅድና በአንድ ሪፖርት” መርህ መሠረት በተቀናጀ አሠራር ለመምራት የተዘረጋው አሠራር ተገልጿል። ተሳታፊዎችም በአፈጻጸሙ ዙሪያ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በማቅረብ ልምድና ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።

በመድረኩ የክልሉ ዘጠኝ ወረዳዎች ፖሊስ ጣቢያዎች የኮሚዩኒቲ ፖሊስ አስተባባሪዎችና የ36ቱ ቀበሌዎች ኦፊሰሮች ተሳትፈዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ግሩም ውብሸት የዳይሬክቶሬቱ የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ቀደም ሲል መገምገሙን ገልጸው በዚህ መድረክም የ2ኛ ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ጠቁመዋል።
እንደ ኮማንደር ግሩም ገለጻ በቀጣይ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር የወንጀል መከላከልን የሰላም ግንባታንና የፖሊስ–ማህበረሰብ ትብብርን ማጎልበት ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ይሆናሉ ብለዋል ።

በመጨረሻም የተያዙ ግቦችን ለማሳካት አመራሮች የኮሚዩኒቲ ፖሊስ አደረጃጀቶችና አጋር አካላት በቅንጅት በተጠያቂነትና በተከታታይ ክትትል እንዲሠሩ ኮማንደር ግሩም ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ ፦ ሳጅን ዮሐንስ መካ

አቶ ቶፊቅ መሀመድ- የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በመሆን በድጋሚ ተሾሙዋል መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ።
02/10/2026

አቶ ቶፊቅ መሀመድ- የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በመሆን በድጋሚ ተሾሙዋል መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ።

አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙሀረር፣መስከሰረም 22/2019(ሀክመኮ):-ላለፉት አመታት የሀረሪ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ኦርዲን በ...
02/10/2026

አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

ሀረር፣መስከሰረም 22/2019(ሀክመኮ):-ላለፉት አመታት የሀረሪ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ኦርዲን በድሪ በድጋሚ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በክልሉ ምክር ቤት ተሹመዋል።

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የመንግስት ምስረታና የ 7ተኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ በመክፈቻ ጉባኤው ላይ አቶ ኦርዲን በድሪን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሹመት ሰጥቷል።

አቶ ኦርዲን በድሪ ክልሉን በርዕሰ መስተዳድርነት በመሩበት የስራ ዘመናቸው የነበራቸውን የላቀ የአመራር ብቃት እና ያስገኙት ተጨባጭ ውጤት በምክር ቤቱ ቀርቧል።

አቶ ኦርዲን በድሪ ክልሉን በመሩባቸው ዓመታት ባከናወኗቸው በርካታ የልማት ስራዎችና ባስመዘገቧቸው ስኬቶች በተጨባጭ ውጤት ማምጣት ችለዋል።

በተለይም በውስን ሃብት የማይቻሉ የሚመስሉ ፕሮጀክቶችን በመድፈር በርካታ ስኬቶችን ያስመዘገቡና ክልሉን በአዲስ የእድገት ምዕራፍ ላይ እንዲገኝ ያስቻሉ መሪ ናቸው ።

የህዝቡን መሰረታዊ ችግሮችን መቅረፍ ያስቻሉ ስራዎችን እውን ከማድረግ ባሻገር ለሀረር ከሀገር ባለፈ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን ያስገኙ ስራዎች ማከናወን ችለዋል።

መርህን በተከተለ መልኩ ሁሌም ለለውጥ የሚተጉ ከመሆናቸውም ባሻገር የስራ ባህል እንዲቀየር አዳዲስ ሀሳቦችን በማመንጨትና በመተግበር ለህዝብ የቆሙ መሪ መሆናቸውን አስመስክረዋል።

ባለፉት አመታት ባከናወኗቸው ስራዎችም በክልሉ በከተማና በገጠር የሚኖረውን ማህበረሰብ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ፤ የሀረር ከተማን የኋልዮሽ ጉዞ በመግታት ስሟን ሆና እንድትገኝ በማስቻል በምሳሌነት የሚጠቀሱ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችለዋል

የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የ2019 ዓ.ም. የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ። የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2019...
01/10/2026

የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት የ2019 ዓ.ም. የ1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ተገመገመ።

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2019 ዓ.ም. የ1ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል።

ግምገማው በሩብ ዓመቱ የታቀዱና የተከናወኑ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ተግባራትን በመገምገም የአፈጻጸም ልምድና ተግዳሮቶችን በመለየት እንዲሁም በቀጣይ የሥራ ወቅት የተቀናጀ የሥራ አቅጣጫ ለመያዝ ያለመ ነበር።

በግምገማው መድረክ ላይ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ኮሚሽነር አህመድ አብዲ ባደረጉት ንግግር ዘላቂ ሰላምና ጸጥታን ለማስፈን ወንጀልን ከመፈጸሙ በፊት ለመከላከል እና ከተፈጸመ በኋላም ውጤታማ የምርመራ ሥራ ለማከናወን የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አደረጃጀቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህንን ሚና ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማጠናከር በፖሊስ መዋቅሮች መካከል የሥራ ትስስርና ቅንጅትን ማሳደግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመቀጠል የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክተር ኮማንደር ግሩም ውብእሸት በ2019 ዓ.ም. የ1ኛ ሩብ ዓመት የታቀዱና የተከናወኑ ዋና ዋና የሥራ ክንውኖችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በአፈጻጸሙ ዙሪያም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ የተለዩ የሥራ ክፍተቶችን ለማረም የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከር እና በሁሉም ወረዳዎች መካከል የሥራ ትስስርና ቅንጅትን ለማሳደግ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በተለይም የዘጠኙ ወረዳዎች የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አደረጃጀቶች በተቀናጀ መልኩ መሥራታቸው የመረጃ ልውውጥን የወንጀል መከላከል ሥራን እና የህብረተሰብ ተሳትፎን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም የህዝብ እርካታን በማሳደግ የፖሊስና የህብረተሰብ ትብብርን ማጠናከር ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ መሆኑ ተመላክቷል።

በመጨረሻም በ1ኛ ሩብ ዓመቱ የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር የታዩ ክፍተቶችን በማረምና በወረዳዎች መካከል የተቀናጀ የሥራ ትስስርን በማጠናከር በቀጣይ ወቅት የተሻለ የሥራ አፈጻጸምና የህዝብ እርካታ ለማስመዝገብ የጋራ የሥራ አቅጣጫ ተይዟል።

በግምገማው መድረክ ከዘጠኙ ወረዳዎች የተውጣጡ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ኦፊሰሮች የኮሚኒቲ ፖሊስ አደረጃጀት አስተባባሪዎችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ ፦ ሳጅን ዮሐንስ መካ

በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ የመስቀል ደመራ  በአል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።==========በሐረሪ ክልል የመስቀል ደመራ በአል በደመቀ...
27/09/2026

በሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ የመስቀል ደመራ በአል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
==========
በሐረሪ ክልል የመስቀል ደመራ በአል በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁ የፀጥታ ሐይሉ አስተዋፅኦ በመሆኑ ህዝባዊ ሀላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ ለሀረሪ ለፌድራል ፖሊስ እና ለመከላከያ ሰራዊት ለሚሊሻ አባላትና ደንብ ማስከበር እንዲሁም ለኮሚዩኒቲ አደረጃጀት የሐረሪ ክልል ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር አህመድ አብዲ ምስጋና አቅርበዋል ።

የፀጥታ ሐይሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ከበአሉ ዋዜማ ጀምሮ ባሉ ቀናቶች በምሽትም በቀንም የተጠናከረ ጥበቃ በማድረጋቸው ስኬታማ እንደነበር ተናግረዋል።

ፖሊስ የደህንነት ካሜራዎችን በመጠቀም የበአሉን ስፍራና የከተማውን የፀጥታ ሁኔታ ከማእከል ሆነው በአመርሮች ቁጥጥር ይደረግ እንደነበረ ጠቁመዋል።

ህብረተሰቡ በአሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረጉ በአሉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተጠናቋል ብለዋል።

የሐይማኖት አባቶች የሐረር ከተማ ህዝብ በአሉ በደመቀ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ ሀይሉ ድጋፍ በማድረጋችሁና በተወሰኑ ቦታዎች ለበአሉ ደህንነት ሲባል የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በመገታት በትእግስት ለጠበቃቹ ሁሉ በኮሚሽኑ ስም የላቀ ምስጋናዬን አቀርባለው ብለዋል ኮሚሽነር አህመድ አብዲ

26/09/2026
የአድማ ብተና ሐይላችን በደመራ በአል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በጥንቃቄ ይጠብቃሉ
26/09/2026

የአድማ ብተና ሐይላችን በደመራ በአል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት በጥንቃቄ ይጠብቃሉ

የተቋሙ ሐላፊዎች የደመራ በአል አከባበርና በከተማው ያለውን ፀጥታ በአንድ ማክል ሆነው በካሜራ እየተቆጣጠሩ መመሪያ በማስተላለፍ ላይ እንዳሉ
26/09/2026

የተቋሙ ሐላፊዎች የደመራ በአል አከባበርና በከተማው ያለውን ፀጥታ በአንድ ማክል ሆነው በካሜራ እየተቆጣጠሩ መመሪያ በማስተላለፍ ላይ እንዳሉ

ምእመኑ የደመራ በአልን ለማክበር በስፍራው ሲደርሱ የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ውሐ የማደል ስነስርአት አከናውነዋል።
26/09/2026

ምእመኑ የደመራ በአልን ለማክበር በስፍራው ሲደርሱ የፖሊስ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ውሐ የማደል ስነስርአት አከናውነዋል።

Address

Near 847J+M43, Awzin Street, 9°18'50"N 42°07'48"E • 1. 86 Km
Harar
3200

Telephone

+251256667537

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Police Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Harari Police Commission:

Shortcuts

Share