Harari Government communication affairs Office

Harari Government communication affairs Office ይህንን ፔጅ ላይክ በማድረግ ስለ ክልላችን ወቅታዊ የሆኑ መረጃዎችን ያግኙ።

06/09/2026

በርካቶችን የሙያ ባለቤት ያደረገው የሀረር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ... በቅርብ ቀን

የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ...
06/09/2026

የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእመርታ ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፣አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል ብለዋል።

ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል ነው ያሉት።

በ "ሌማት ትሩፋት" የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን።

ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን በማለት ገልፀዋል።

እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው ብለዋል።

በሀረሪ ክልል በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን የሕግ ታራሚዎችና አባላት ተመረቁየሀረሪ ክልል ማረሚያ ኮሚሽንና የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ፖሊስ ከሀረር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበ...
05/09/2026

በሀረሪ ክልል በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን የሕግ ታራሚዎችና አባላት ተመረቁ

የሀረሪ ክልል ማረሚያ ኮሚሽንና የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ማረሚያ ፖሊስ ከሀረር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሠለጠናቸውን 108 የሕግ ታራሚዎችና አባላቱን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አስመረቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ኃላፊ አቶ አዩብ አሕመድ፤ ተመራቂዎች ያገኟቸውን ሙያዎች በመጠቀም በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ተቋሙን እንዲያገለግሉ፣ ከማረሚያ ቤት ሲወጡም ራሳቸውንና ማኅበረሰባቸውን እንዲክሱ አሳስበዋል።

ኃላፊው አክለውም የሐረሪ ክልልና የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የአስተዳደር ወሰን ሳይለያያቸው ሁሉንም ታራሚዎች እኩል በማሠልጠን የሙያ ባለቤት ማድረጋቸው፣ ትክክለኛው ታራሚዎችን የማነጽና የማረም ሥርዓት እየተተገበረ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

የሐረሪ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አሕመድ በበኩላቸው፤ ማረሚያ ቤት ማረብ ብቻ ሳይሆን ታራሚዎች ክህሎት ጨብጠው የሚወጡበት ቦታ ሆኗል ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በዕለቱ ከሰለጠኑት 108 ተመራቂዎች መካከል 14ቱ ሴቶች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በሕይወት ዘመናቸው የሚጠቅሟቸውን በእንጨትና ብረታብረት፣ በልብስ ስፌት፣ በስነ ውበት እንዲሁም በኮንስትራክሽን ሥራዎች ሙያዊ ሥልጠና ማጠናቀቃቸውን አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም 229 ታራሚዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ ብለዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች በበኩላቸው ባገኙት ሙያዎች ተቋሙን ለማገልገል እና ወደ ማኅበረሰቡ ተቀላቀሉም አምራች ዜጋ ለመሆን ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች ውጤት ተገኝቷልየመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መገኘቱን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን...
05/09/2026

የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች ውጤት ተገኝቷል

የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መገኘቱን የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ።

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ዓመታዊ የክልል ጉባዔ በሐረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

መኩሪያ ሃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ከብቁ የሰው ኃይል ጋር በማቀናጀት ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ስራ ማከናወን ተችሏል።

የአገልግሎት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ዘመናዊ የፖሊሲና ፕሮግራም፣ አዋጅና ደንብ እንዲሁም መመሪያና ስታንዳርድ በመቅረጽ ለተግባራዊነቱ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በተለይም የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተወሰዱ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል።

በተለይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ በተደረገው ውጤታማ የሪፎርም እርምጃ ከፌደራል እስከ ክልል ድረስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል።

መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት የተገልጋዮችን እንግልት በመቅረፍ የአገልግሎት እርካታን እያሳደገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የተጀመረውን ስራ በዘላቂነትና በውጤታማነት ለማሳደግ የአመራር ቁርጠኝነትና የቴክኖሎጂ ትግበራ ቀጣይነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በቀጣይም የተቋማት አቅም ግንባታን በማጠናከር፣ የሰው ኃይልን ከቴክኖሎጂ ጋር የማብቃት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የሐረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ጆርዳን ይስሃቅ በበኩላቸው በክልሉ በአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በተለይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ጊዜና ገንዘብ ቆጣቢ አሰራርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

የማህበረሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄ በመመለስ ጥራትና ቅልጥፍናን በመጨመርና የብልሹ አሰራር ችግሮችን በማስቀረት የአገልግሎት እርካታን ማሳደግ እያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

መድረኩም የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ መደላድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባዔ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስና የክልል ቢሮ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በፌደራልና በክልሎች 2018 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 እቅድ ላይ በመወያየት አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ተመላክቷል።

ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ድንበር የለሽ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤​የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን ከአማራ ክልል መንግ...
05/09/2026

ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ድንበር የለሽ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፤

​የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ቡድን ከአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ጋር በባህርዳር ከተማ የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

​በልምድ ልዉዉጥ መድረኩ የተገኙት የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ እንደገለጹት፤ የአማራ ክልል የሀገራችን የቱሪዝም የስበት ማዕከልና ከራሱ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ትልቅ ሀብት ያለው ክልል ነው።

በባሕር ዳር ከተማ ተዘዋውረን የተመለከትናቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ጸጋዎች ለሀገራችን የወደፊት የቱሪዝም እድገት ትልቅ ተስፋ የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የባህርዳር በለዉጥ ላይ ነች የከተማዋ የለዉጥ ጉዞም የብልጽግና ጉዟችን ዋነኛ ማሳያ ምልክት ነዉ ብለዋል።

​ሃላፊዉ ክልሉ ከነበረበት የጸጥታ ችግር ወጥቶ አሁን ትኩረቱን ልማት ላይ ማድረጉን በቆይታቸው መታዘባቸውን ገልጸው፤ በቀጣይ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በጋራ እንደሚሠሩ አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል።

​የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ በበኩላቸው፤ ህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ለመገንባት ሚዲያው ዋነኛ መሳሪያ ነዉ። ከሀረሪ ክልል ጋር የነበረውን የቆየ መልካም ግንኙነት እና የተግባራት አፈጻጸም ልምድ በመካፈልና በማዳበር፣ ለክልላችን እንዲሁም ለሀገር ገጽታ ግንባታ የሚጠቅሙ ሥራዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል። የልምድ ልውውጡም ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና የነበሩ ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል።

​የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ዘበነ በበኩላቸው፤ የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ ከምናሳካባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ዲጂታል ኮሙኒኬሽን መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህ የሚመጥን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አሁናዊ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፤ የልምድ ልውውጡ በቀጣይ በጋራ ለሚከናወኑ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራዎች ጠንካራ መሠረት የጣለ ነውም ብለዋል።

የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ እና የውል ሥምምነት ተፈራረሙየሀረሪ ክልል የመንግሥት ...
04/09/2026

የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ እና የውል ሥምምነት ተፈራረሙ

የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ እና የውል ሥምምነት ተፈራርመዋል።

ተቋማቱ ሁሉን አቀፍ የሙያ እና የፋይናንስ አቅሞች፤ የሚዲያ፣ የስቱዲዮ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እና ልውውጥ እንዲሁም ለተሻለ ሀገራዊ ዕድገት መጎልበት በጋራ እንደሚሠሩ በስምምነቱ ተቀምጧል፡፡

የሚጠበቁበትን ፈጣን መረጃዎች በማቅረብ በኩል ተባባሪ በመኾን በአሚኮ ድረ-ገጽ እና ማኅበራዊ ገጾች ላይ እንዲታተሙ እና ሌሎች ተግባራትን እንደሚወጣም በስምምነቱ ተቀምጧል።

በዚህ ወቅትም የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ አሚኮ ከሀረሪ ክልል መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጋር በሁሉም የሚዲያ አማራጮቹ እና በሁሉም ቋንቋዎች በጋራ ሢሠራ ቆይቷል ብለዋል።

የሀረሪ ክልል የሥራ ኀላፊዎች የመረጃ ምንጭ እና የአሚኮ ቤተሰብ በመኾን አብራችሁን ስለሠራችሁ ልዩ ክብር አለን ብለዋል።

አሚኮ ባለቤቱ የአማራ ሕዝብ ቢኾንም ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያገለግል የሚዲያ ተቋም መኾኑን በሀረሪ ክልል በመገኘት እና በማገልገል አስመስክሯልም ነው ያሉት።

ስምምነቱ በሚዲያ እና በኮሙዩኒኬሽን ሥራ እንደ ቤተሰብ በጋራ ሥንሠራ የነበረውን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል። በሁሉም ቋንቋዎች ከዚህ በፊት ሥንሠራቸው የነበሩ ሥራዎችን በማጠናከር የሀረሪን ገጽታ፤ የቱሪዝም መዳረሻነት፤ አብሮነት እና ጥንታዊነት ለሁሉም የምናሳውቅበት ሥምምነት ነው ብለዋል።

አዲስ ሥራ ለመጀመር ሳይኾን የጀመርናቸውን ሥራዎች ለማጠናከር እና ውጤታማ ለማድረግ ተፈራርመናል ነው ያሉት።

የሀረሪ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሔኖክ ሙሉነህ "ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን" በሚል ድርጅታዊ መርህ የሚታወቀው አሚኮ ለዓመታት በሚዲያ እና ኮሙዩኒኬሽን ታሪክ ውስጥ የራሱን አስተዋጽኦ አስቀምጧል ብለዋል።

ለሀገር ገጽታ ግንባታ ግንባር ቀደም ኾኖ የሚሠራ ጠንካራ ተቋም መኾኑንም ገልጸዋል። አሚኮ በሀረሪ ክልል የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን፤ የአብሮነት እና የመቻቻል እሴቶችን፤ የቱሪዝም ሀብቶችን፤ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግባራትን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ሀገራት እንዲደርስ በብዙ ቋንቋ የሚዲያ ሽፋን እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በአሚኮ የዘገባ ሽፋን የሀረሪ ክልል ሕዝብ ደስተኛ ነው ብለዋል። የክልሉ መንግሥት በቀጣይ በይበልጥ ከአሚኮ ጋር ለመሥራት ስምምነት መፈራረሙንም ገልጸዋል። በቀጣይ ሚዲያውን ለመደገፍ የሀረሪ ክልል በትኩረት ይሠራልም ብለዋል።

አሚኮ አሠባሣቢ እና ገዥ ትርክት ላይ በትኩረት የሚሠራ፤ ብሔር ብሔረሰቦችን አቅፎ የያዘ እና በሁሉም ቋንቋ በመሥራት ቀዳሚ የኾነ ሚዲያ መኾኑንም አንስተዋል።

አሚኮ ከሀገር ባለፈ በአፍሪካ እና በዓለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሚዲያ ለመኾን የሚያደርገው ጉዞ ሩቅ አይደለምም ብለዋል።

የተቋማት ኀላፊዎቹ የአሚኮን ተቋም የጎበኙ ሲኾን በግቢ ውስጥ የአረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ባህርዳር ገቡ የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ባህርዳር ከተማ ገ...
04/09/2026

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ባህርዳር ገቡ

የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ባህርዳር ከተማ ገብተዋል።

ኃላፊው ባህር ዳር ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ በአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ እና በአሚኮ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉቀን ሰጠኝ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

አቶ ሔኖክ ባህርዳር የገቡት ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ለመፈራረም ነው።

በሐረሪ ክልል የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን እና ኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ ይፋ ሆነበሐረሪ ክልል የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን እና ኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ ማብሰሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።በ...
04/09/2026

በሐረሪ ክልል የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን እና ኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ ይፋ ሆነ

በሐረሪ ክልል የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽን እና ኒውትሪሽን ፍኖተ-ካርታ ማብሰሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጃሚዕ መሐመድ እንደገለጹት በክልሉ የምግብ ሥርዓትን ለማሻሻል በተከናወነው ቅንጅታዊ ሥራ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

ቀደም ሲል በክልሉ በሁለት ወረዳዎች ተጀምሮ የነበረው የሥርዓተ-ምግብ ፕሮግራም በአሁኑ ወቅት ወደ ስድስት ወረዳዎች ማደጉን የጠቆሙት ሃላፊው የፕሮግራሙን ስኬታማነት አጠናክሮ ለማስቀጠል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የምግብ ሥርዓት ትራንስፎርሜሽንና ኒውትሪሽን የክላስተር 2 ዋና አስተባባሪ ዶክተር አንቢሳ ሙለታ በበኩላቸው የፍኖተ-ካርታው መጀመር የሐረሪ ክልልና የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕይወት የሚቀይር እንዲሁም ሀገራዊ የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ የተገባ የጋራ ቃል-ኪዳን ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።

ዶክተር አንቢሳ አክለውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የምግብ ሥርዓት በአየር ንብረት ለውጥ፣ በአካባቢ መራቆት፣ በሕዝብ ቁጥር እድገት፣ በምግብ ዋጋ ንረት እና በእኩልነት እጦት ምክንያት ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

በመሆኑም ረሃብን ለማጥፋት፣ ሥርዓተ-ምግብን ለማሻሻልና አካታች የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥ የምግብ ሥርዓትን ማሻሻል ወሳኝ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2021 ይፋ ባደረገችው ሀገራዊ ፍኖተ-ካርታ አማካኝነት ጠንካራ ቁርጠኝነት ማሳየቷን ተናግረዋል።

የሐረሪ ክልላዊ መንግሥት ይህንን ሀገራዊ ፍኖተ-ካርታ ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታዎች፣ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮችና እድሎች ጋር በማጣመር ይፋ ማድረጉ የሚደነቅ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሐረሪ ክልል የከተማና የገጠር ግብርናን አቀናጅቶ ለመምራት ያለው ምቹ ሁኔታ፣ ከፍተኛ የንግድና የገበያ ትስስር ማዕከልነቱ፣ የሆርቲካልቸር አቅሙ እንዲሁም ታሪካዊና ባህላዊ እሴቶቹ ለትራንስፎርሜሽኑ እውን መሆን ሰፊ እድል የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለስኬታማነቱም የአመራር ቁርጠኝነት፣ የፖሊሲ እና ፕሮግራሞች ቅንጅት እንዲሁም ዘላቂ የፋይናንስ አቅርቦት ወሳኝ መሆናቸውን አመላክተዋል።

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የምግብ ሥርዓትና ኒውትሪሽን አማካሪ አቶ አብዱናስር አህመድ በበኩላቸው ይፋ የተደረገው ፍኖተ-ካርታ በክልሉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የስርዓተ-ምግብ ማነቆዎችን በመቅረፍ ዘላቂና አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

በተለይም የእናቶችንና ህፃናትን ኒውትሪሽን ለማሻሻል፣ መቀንጨርን ለመቀነስ እና ጤናማ ትውልድን ለመገንባት የተነደፉ የትኩረት አቅጣጫዎች በተግባር እንዲተረጎሙ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የምግብ ሥርዓት ሽግግርና ኒውትሪሽን የአየር ንብረት ለውጥ አስተባባሪ በሆኑት በዶክተር ከፈለኝ ጌታሁን በፍኖተ ካርታው ላይ ትኩረት ያደረገ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በማብሰሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የሐረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት አመራሮች፣ የልማት አጋሮች እና የግል ዘርፍ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ሰራተኞች ደም ልገሳ አካሄዱየኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።"በደም እጦት ሰው መሞት...
04/09/2026

የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ሰራተኞች ደም ልገሳ አካሄዱ

የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን አመራሮችና ሰራተኞች የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

"በደም እጦት ሰው መሞት የለበትም" የሚለውን የዓለም ጤና ድርጅት መርህ ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ አገሮች ዜጎቻቸው ደም መለገስን ባህል አድርገው ቀጥለዋል።

በዚህ ተግባር አንዳንድ አገሮች ስኬታማ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የድርጅቱን መርህ ለመተግበር በጥረት ላይ ይገኛሉ።

በአንድ አገር ሰው በደም እጦት እንዳይሞት ከአጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር 1 በመቶ ደም መስጠት እንዳለበት ይታመናል።

በኢትዮጵያ በደም እጦት ሰዎች እንዳይሞቱ ለማስቻል በየሦስት ወሩ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደም መለገስ ይጠበቅባቸዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት ግን የደም ለጋሾች ቁጥር ከግማሽ ሚሊየን ያነሰ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን አመራሮችና ሰራተኞች የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በተለያዩ ጊዜያት የደም ልገሳ በማድረግ አስተዋጽዖ እያበረከቱ ይገኛሉ።

በመሆኑም የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን አመራሮችና ሰራተኞች በዛሬው እለት የደም ልገሳ መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

መርሀ ግብሩ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም የማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ቸሩ ጅማ እንዳሉት ደም መለገስ እናቶች በወሊድ ወቅት የሚገጥማቸውን የደም እጥረት ለመሸፈን ድርሻው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለያዩ አደጋዎች ደም ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት ለከፋ አደጋ ሊጋለጡ የሚችሉ ዜጎቻችንን ህይወት ለመታደግ ደም የመለገስን ተግባር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጻል።

ደም ለሚሹ ወገኖች ለመድረስ ደም የመለገስ ባህላችንን ልናጎለብት ይገባል ብላል።

ደም መለገስ የዜጎችን ህይወት መታደግ መሆኑን የገለፁው ዳይሬክተሩ በቀጣይም ደም ልገሳ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ ሁሉም የደም ልገሳን ባህል በማድረግ ለሰብአዊነት እንዲተጋ ጥሪ አስተላልፏል።

ደም ለጋሾቹም በበጎ ተግባራቸው የሰው ህይወት በመታደጋቸው ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል :- አቶ ጌቱ ዋዬሳበሐረሪ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት  የመደጋገፍ እሴት...
04/09/2026

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል :- አቶ ጌቱ ዋዬሳ

በሐረሪ ክልል በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ዋዬሳ አመለከቱ።

በሀረሪ ከልል በክረምት በጎ ፍቃድ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት በክልሉ በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብሮነትና መደጋገፍ እሴት በመጎልበት የዜጎችን ህይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ይገኛል ።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተደመረ አቅም ዜጎችን በማገዝና ሃብትን አቀናጅቶ በመምራት ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

በተለይም በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በርካታ አቅመ ደካሞችንና አረጋዊያንን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ስራዎች እውን ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

በዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ 14 ተግባራት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት እድሳትና መልሶ ግንባታ፣ የአካባቢ ንጽህና ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ፣ ደም ልገሳ፣ የማጠናከሪያ ትምህርት የመስጠትና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል

ከዚህ በተጨማሪም ማዕድ ማጋራት፣ አዳዲስና ነባር የመማሪያ ክፍል ግንባታ እና እድሳት ፣ የትምህርት ቤቶች የተማሪ ወንበሮች ጥገና፣ ጽዳትና ውበት ስራዎችን ጨምሮ የማጣቃሻ መጽሀፍት የማሰባሰብ ስራ በበጎ ፍቃድ አገልግሎቱ የትኩረት የተሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መደጋገፍ፣ የመተጋገዝና አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመው የዜጎችን እውቀት፣ ገንዘብ፣ ጉልበት እና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎችን በሚገባ መጠቀምና ከድህነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ነው የጠቆሙት።

ይህ የመተጋገዝና የአብሮነት ባህል ድህነትን ለማሸነፍ ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ፣ አመራሩ የታቀዱትን ግቦች ወደ ሙሉ ተግባር ለመቀየር እያከናወነ የሚገኘውን ተግባራት ማጠናከር እንዳለበት አቶ ጌቱ አሳስበዋል።

እንዲሁም በክልሉ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት የሚከናወኑ መርሃ-ግብሮች የተሳኩ እንዲሆኑ ሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ በየደረጃ የሚገኝ አመራር፣ የመንግስት ሠራተኞችና መላው ሕዝቡ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Address

Ethiopia, Harari Peoples Regional State, Harar City
Harar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Government communication affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Harari Government communication affairs Office:

Shortcuts

Share