Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ

  • Home
  • Ethiopia
  • Harar
  • Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ

Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ This is official page of Harari Regional Health Bureau. this page delivers News, Health related information and vacancy announcements on daily basis.

17/09/2026
15/09/2026
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ!ለመላው የክልላችን ሕዝብ፣ ለጤና ባለሙያዎችና ለሠራተኞቻችን በሙሉ፤በመጀመሪያ መላው የክልላችን ሕዝብና የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች ለ...
10/09/2026

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ!
ለመላው የክልላችን ሕዝብ፣ ለጤና ባለሙያዎችና ለሠራተኞቻችን በሙሉ፤በመጀመሪያ መላው የክልላችን ሕዝብና የጤናው ዘርፍ ባለሙያዎች ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።ያለፈው ዓመት የኅብረተሰባችንን ጤና ለመጠበቅና የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት በትጋት የሠራንበት ዘመን ነበር። በአዲሱ ዓመትም ይህንን ስኬት በማስቀጠል፣ የጤና ተቋሞቻችንን ጥራትና አቅም ይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት የምንሠራ ይሆናል።የጤና ሥርዓታችንን በማዘመንና ምላሽ ሰጭነቱን በማረጋገጥ፣ ጤናማና ደስተኛ ማኅበረሰብ የመፍጠር ራዕያችንን ለማሳካት ከመላው ማኅበረሰብና ከአጋሮቻችን ጋር የጀመርነውን የልማት ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለን።ኅብረተሰባችን ጤናውን በመጠበቅ ረገድ የሚያደርገውን ንቁ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ እያልኩ፤ ማኅበረሰቡ ጤናውን ከሚጎዱ ልማዶችና ተግባራት በመራቅ፣ የራሱንና የአካባቢውን ጤና በመጠበቅ ደስታውን በኅብረት፣ በመተሳሰብና በመጋራት እንዲያከብር አደራ እላለሁ።አዲሱ የ2019 ዓ.ም ለሁላችንም የጤና፣ የደስታ፣ የሰላም፣ የፍቅርና የብልጽግና ዘመን እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።
🌻🌻 መልካም አዲስ ዓመት! 🌻🌻 #ኢትዮጵያ

የሐረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በጤና እና በማህበራዊ ዘርፎች የድጋፍ እና የጉብኝት መርሐ ግብር አካሄዱ ሐረር — ጳግሜ 4 ቀን በሚከበረው "የህብር ቀን" ም...
09/09/2026

የሐረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የህብር ቀንን ምክንያት በማድረግ በጤና እና በማህበራዊ ዘርፎች የድጋፍ እና የጉብኝት መርሐ ግብር አካሄዱ

ሐረር — ጳግሜ 4 ቀን በሚከበረው "የህብር ቀን" ምክንያት በማድረግ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ካቢኔ አባላት በሕይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሁሉን አቀፍ ሆስፒታል በመገኘት ለሕሙማን የምግብ እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።

በተጨማሪም በሆስፒታሉ የግብአት ድጋፍ ያደረጉት አመራሮቹ፣ ህሙማንን ከመጠየቃቸው ባሻገር በሆስፒታሉ እየተከናወኑ የሚገኙ አዳዲስ አገልግሎቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

አመራሮቹ በጤናው ዘርፍ ያደረጉትን እንቅስቃሴ በማስቀጠል የአብረሃ ባሕታ ሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ እና ፌስቱላ ማዕከልን የጎበኙ ሲሆን፣ በተመሳሳይ በአብራሃ ባህታ አራጋውያን ማዕከል በመገኘት ለአረጋውያን ማዕድ አጋርተዋል።

በዚሁ የበጎ አድራጎት እና የጉብኝት መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሐረሪ ብሔራዊ ጉባኤ አፈ ጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር፣ የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ጳግሜ 4 "የህብር ቀን" በሐረሪ ክልል በነዚህ እና በተለያዩ ህዝባዊ ስነ ስርዓቶች በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

🏃‍♂️ ጳጉሜን 4 "የኅብር ቀን" በሐረሪ ክልል በታላቅ የማስ ስፖርት ንቅናቄ ተከብሯል! ❤️💛💚 #የኅብርቀን  #ጳጉሜን4  #ሐረሪ  #ኢትዮጵያ  #የማስስፖርት  #አንድነት
09/09/2026

🏃‍♂️ ጳጉሜን 4 "የኅብር ቀን" በሐረሪ ክልል በታላቅ የማስ ስፖርት ንቅናቄ ተከብሯል! ❤️💛💚

#የኅብርቀን #ጳጉሜን4 #ሐረሪ #ኢትዮጵያ #የማስስፖርት #አንድነት

Address

Harar

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Telephone

+251256661963

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Harari Regional Health Bureau የሐረሪ ክልል ጤና ቢሮ:

Shortcuts

Share