13/06/2026
የሀረሪ ክልል የCALM ፕሮግራም የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ለመገምገም የምክክር መድረክ አካሄደ።
ሰኔ 6/2018
* * * *
በሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ፣ በክልሉ እየተተገበረ የሚገኘውን "የአየር ንብረት አፈጻጸም እና የመሬት አያያዝ ፕሮግራም" (CALM) የ2018 በጀት ዓመት የፊዚካልና የፋይናንሻል አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በድሬዳዋ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄደ።
በመድረኩ የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ አመራሮች፣ የሸንኮር፣ ሐኪም፣ ዲሬ ጠያራ፣ ኤሬር እና ሶፊ ወረዳዎች የዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የውይይት መድረኩን የከፈቱት የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ አራርሶ፣ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በአፈጻጸም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሆነ ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የፊዚካል፣ የፋይናንስ፣ የተዘዋዋሪ ፈንድ እና የ"One Time Investment Fund" ዙሪያ ባለሙያዎች የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በግምገማውም የውሃ ተፋሰስ ልማት፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ የመሬት ማገሚያና የደን ልማት እንዲሁም የእርሻና ኑሮ ማሻሻያ ተግባራት ምን ያህል እንደተከናወኑና የበጀት አጠቃቀሙም ከፊዚካል ውጤት ጋር ያለው ተመጣጣኝነት የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ መሐመድ አብዱረህማን በዝርዝር አቅርበዋል።
የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ያህያ አብዱራሂም በበኩላቸው፣ የCALM ፕሮግራም ለኅብረተሰቡ የኑሮ ማሻሻያ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፣ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና የታዩ ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ የሥራ ዘመን በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ኑረዲን መሐመድ የፕሮግራሙን የመጀመሪያ ምዕራፍ (CALM 1) በማጠቃለል ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ (CALM 2) ለመሸጋገር፣ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅዶቻቸውን እስከ ሰኔ 20 ቀን 2018 ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥቷል።
በመድረኩ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ተሰጥቶ የተመዘገቡ ስኬቶች የተወደሱ ሲሆን፣ የቀሩ ሥራዎችን ለመጨረስ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ በመስማማት ተጠናቋል።
Website:- www.hararibofed.gov.et
E-mail:- [email protected]
Facebook:- www.facebook,com/HBoFED
TikTok:- https://www.tiktok.com/.bofec
T.me:- https://t.me/HBoFEC