Gurida,ጉርዳ ኸተራት

Gurida,ጉርዳ ኸተራት my wish highly eagerd to gurage strength and cooperation Available every were openly and friendly.

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! አብደለ አህማድ, Sew Mehon, Sadam Hussien
06/07/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! አብደለ አህማድ, Sew Mehon, Sadam Hussien

ንፁህ የተጣራና በምንም ያልተበረዘው ባህላችን። እናመሠግናለን!!!
29/09/2023

ንፁህ የተጣራና በምንም ያልተበረዘው ባህላችን። እናመሠግናለን!!!

06/07/2023

ወልቂጤ ከተማ በሊጉ መቆየቱን አረጋግጧል

በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ የመውረድ ስጋት የነበረበት ወልቂጤ ከተማ አዳማ ከተማን ገጥሞ በአቻ ውጤት ቢጠናቀቅም አርባምንጭ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በተመሳሳይ አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ክትፎዎቹ በሊጉ መቆየታቸውን አረጋግጠዋል::

ሰኔ 29/2015
ሸገር ስፖርት አሬና

Mashallah, Alhamdurillah በጣም ያምራል በሁሉም የሀገራችን ክፍል እና በአለማች በሰላምና በድምቀት ተከበሮ በማየታችን ምንም ለማይሳነው ጌታችን (አላህ) ክብር ይገባው።
21/04/2023

Mashallah, Alhamdurillah በጣም ያምራል በሁሉም የሀገራችን ክፍል እና በአለማች በሰላምና በድምቀት ተከበሮ በማየታችን ምንም ለማይሳነው ጌታችን (አላህ) ክብር ይገባው።

09/01/2023

ሁሌም ፈጣሪህን አስብ።
(ለዕለቱ የመረጥንላችሁ ፍቶ)

18/11/2022

"መቼም በማያወላውል ልብ ጉራጌ ክልል ነው"
ህዝቡ አሁንም በሰላማዊ መንገድ ህገመንግስታዊ መብቱ በመጠየቅ ላይ ነው። በመንግስት በኩል ጆሮ ዳባ ልበስ መባሉ ግን እንደ ጉራጌን የሀገር ውለታው እንደ መካድ ነው ከልብ ያሳዝናል። የጉራጌ ማህበረሰብ ቆርጦ የመጣው ይምጣ ብሎ ትግሉን በማይቀለበስ ሁኔታ ተነስቷ መፍትሔው መንግስት አስቸኳይ የፈጠነ ምላሽ መስጠት ብቻ ነው። እስቲ ዲሞክራሲያ አካሄድ በዚሁ እንልመድ በጣምቀላል ነው።
"መቼም በማያወላውል ልብ ጉራጌ ክልል ነው"

በአሉ የደስታና የፍቅር ይሁንላቹ; የአባቶቻችንና የእናቶች ንፁህ አንጡረ ውርስ የሆነው ምርቃት ተቀብላቹ ቀጣይ የስራ ስንቅ ይዛቹ ለመምጣት ለመምለሚቷ ውቢቷ የባላገሮች ምድር በመከሰታቹ እጅግ...
18/09/2022

በአሉ የደስታና የፍቅር ይሁንላቹ; የአባቶቻችንና የእናቶች ንፁህ አንጡረ ውርስ የሆነው ምርቃት ተቀብላቹ ቀጣይ የስራ ስንቅ ይዛቹ ለመምጣት ለመምለሚቷ ውቢቷ የባላገሮች ምድር በመከሰታቹ እጅግ ደስ ብሎናል ይመቻቹ።

ወንድማችን ኢዘዲን እንኳን ደስ አለህ ይገባሀል። ቶሎ ወደ ስራ እንድትገባል በጉጉት እየጠበቅንህ ነው በማንኛው መንገድ ልንረዳህ እኛ ወንድሞችህ ዝግጁ ነን በርታልን አይዞህ።
27/08/2022

ወንድማችን ኢዘዲን እንኳን ደስ አለህ ይገባሀል። ቶሎ ወደ ስራ እንድትገባል በጉጉት እየጠበቅንህ ነው በማንኛው መንገድ ልንረዳህ እኛ ወንድሞችህ ዝግጁ ነን በርታልን አይዞህ።

ክልላችን በሰላማዊ ትግላች የሚጸናበት 11ኛ ሰዓት ላይ ደርሷል ማንም ሳይሰለች ያለንን ሁሉ ትግል ተጠቅመን ስራችን በሰላማዊ መንገድ መስራት አለብን አደራ ይህን ጊዜ በቀላሉ እያሳለፍን ባይሆ...
17/08/2022

ክልላችን በሰላማዊ ትግላች የሚጸናበት 11ኛ ሰዓት ላይ ደርሷል ማንም ሳይሰለች ያለንን ሁሉ ትግል ተጠቅመን ስራችን በሰላማዊ መንገድ መስራት አለብን አደራ ይህን ጊዜ በቀላሉ እያሳለፍን ባይሆንም ትግላችን ግን እስከ ግባችን ነው ምንም ይሁን ምን ፍንክች የለም።

24/07/2022
እልልልል.......ከፍ አለልን ሰንደቃችን በጣም ደስ ብሎናል። ደስታ አጨላሚዎች እጃቹ; አይናቹ ;ኪሳቹ ይያዝልን።
24/07/2022

እልልልል.......ከፍ አለልን ሰንደቃችን በጣም ደስ ብሎናል። ደስታ አጨላሚዎች እጃቹ; አይናቹ ;ኪሳቹ ይያዝልን።

 #ሰበር ዜናየብልፅግ ፓርቲ ዛሬ የወሰነውና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰኑት ሰበር ዜና።“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!ውድ የሀገሬ ልጆች፣የተከበራችሁ የኢት...
22/11/2021

#ሰበር ዜና
የብልፅግ ፓርቲ ዛሬ የወሰነውና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወሰኑት ሰበር ዜና።

“ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን!
ውድ የሀገሬ ልጆች፣
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ወዳጆች፣
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጀግንነትና መሥዋዕትነት ክብሯንና ነጻነቷን አስጠብቃ የኖረች ሀገር ናት። ይሄን ወዳጅም ጠላትም ያውቀዋል። ድንበሯን ሊደፍሩ የሞከሩ አይበገሬ ክንዷን አይተዋል። ሊያስገብሯት የቋመጡ አቀርቅረው ተመልሰዋል። ክህደት ለፈጸሙባት ተገቢውን ትምህርት መስጠት፣ ከጀርባ የወጓትን አይቀጡ ቅጣት መቅጣትን ታውቃለች። ለሺህ ዘመናት የተጎናጸፈችው ነጻነትና ሉዓላዊ ክብር በችሮታ የተገኘ አይደለም። ያለ ዋጋ ነጻነትን አጽንቶ መጠበቅ አይቻልምና፤ ኢትዮጵያ የሚለው የነጻነት ስም የደም ዋጋ ተከፍሎበታል፣ ብርቱ ጀግኖች ሞተውለታል።
በታሪክ የምናውቃቸው አባቶቻቸው በአስተዳደርና በርእዮተ ዓለም ይለያያሉ፤ ለመብት፣ ለፍትሕና ለእኩልነት በነበራቸው አመለካከት ይለያያሉ። ለኢትዮጵያ የግዛት አንድነት፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ባላቸው ቦታ ግን ልዩነት አልነበራቸውም። በቋንቋ፣ በብሔርና በጎሳ ብዝኃነት ቢኖራቸውም የአልደፈርም-ባይ ቆራጥነታቸው አንድ ያደርጋቸዋል። የግል ፍላጎታቸው የቱንም ያህል የተራራቀ ቢሆን፣ የጋራ ጠላት ሲመጣ ኢትዮጵያዊነት ከግላዊነታቸው በላይ ይቀመጣል።
ድሮም ሆነ ዛሬ የእያንዳንዳችን ፍላጎት፣ የሁላችንም ሕይወት ከኢትዮጵያ በታች ነው። እኛ ኖረን ኢትዮጵያ ከምትሞት እኛ ሞተን ኢትዮጵያ እንድትኖር እንፈልጋለን። የሁላችንም የሆነች፣ ነጻነትና ፍትሕ የሰፈነባት፣ በገናናነቷና በነጻነቷ በዓለም አደባባይ የምትጠራ ሀገር እንድትኖረን ምኞታችን ነው። ለኢትዮጵያ ትልቅ በመመኘት፤ ሀገራችን አንገቷ ቀና እንዲል በመፈለግ፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት ዐቅማችን የፈቀደውን ሁሉ አድርገናል። ፖለቲካችን ከመገዳደል ወደ መተጋገል እንዲቀየር ታግለናል። ኢትዮጵያ የሁላችን ናት ብለን በሰው ሀገር የሚንከራተቱት ሁሉ እንዲገቡ ለማድረግ ሞክረናል። ካለፈው በጎውን ወስደን ጥፋቱን በይቅርታ ለማረም ተንቀሳቅሰናል። “በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር” ብለን አዲስ ምዕራፍ ከፍተናል። የመለያየትና የጥላቻን ግንብ አፍርሰን የመደመርና ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት ድልድይን ልንገነባ ቃል የገባነውን ወደ ተግባር ለመተርጎም ዐቅማችን የፈቀደውን አድርገናል።
ኢኮኖሚው እንዲያገግምና መዋቅራዊ ለውጥ እንዲያመጣ፤ የዳኝነት ሥርዓታችን እንዲሻሻል፣ የሰብአዊ መብት አያያዛችን እንዲስተካከል፤ የውጭ ግንኙነት መርሐችን ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ታግለናል። በዚህ መካከል እንደ ሰው በርትተናል። እንደ ሰውም ደክመናል። እንደሰው አልምተናል፣ እንደ ሰውም አጥፍተናል። በኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ በኢትዮጵያ ክብርና በኢትዮጵያ ታላቅነት ግን ለአፍታም አዘንብለን አናውቅም።
ኢትዮጵያ የምታጓጓ ሀገር ናት። ከትናንትናዋ ይልቅ ነገዋ ታላቅ ነው። መከራ ማለፍ ነባር ችሎታዋ ነው። ይሄንን የገጠመንን መከራም እናልፈዋለን። ኢትዮጵያ ማሸነፏ አይቀርም። አሁን ኢትዮጵያን ለመታደግ የመጨረሻውን ፍልሚያ የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን። ጠላቶቻችን በውጭና በውስጥ ተቀናጅተው ዘምተውብናል። በአንድ በኩል ታሪካዊ ጠላቶቻችን በራሷ ፈቃድና በራሷ መንገድ ብቻ የምታድግ ኢትዮጵያ ላለማየት የጥፋት በትር ሰንዝረዋል። ኢትዮጵያ አፍሪካዊ በሆነ መንገድ ከተነሣች፣ ተነሥታም ካሸነፈች፣ ከዚህ በኋላ ለማንም የማትመለስ ትሆናለች። ይሄን አፍሪካዊ መንገድ ለማደናቀፍ ሁሉንም ዓይነት የክፋት መሣሪያዎች አሰልፈዋል። የውጭና የውስጥ ጠላቶቻችን የእነርሱን ብርታት በኢትዮጵያ ድካም ላይ ለመገንባት ተነሥተዋል። የኢትዮጵያ ፍላጎት ይዞ ማለፍ እንጂ ጥሎ ማለፍ አልነበረም፤ ለዚህ ነው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን በዋናነት ጎረቤት ተኮር እንዲሆን ያደረግነው፤ ይህ ትግል የመላ ጥቁር ሕዝቦች ትግል ነው። ኢትዮጵያ አንበርክኮ ጥቁር ሕዝብን ለማሳፈርና አዲሱን የቅኝ ግዛት ቀንበር ለመጫን የሚደረግ ሤራ ነው።
ጥቁር ሕዝቦች የራሳችን ታሪክ፣ ባህል፣ ማንነትና ክብር እንዳይኖረን ሆን ተብሎ የሚደረግ አንገት የማስደፋት ትግል ነው። ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተከፈተ ዘመቻ፣ ኢትዮጵያን በማንበርከክ ጥቁር ሕዝቦች የነጻነትና የአሸናፊነት አርአያ እንዳያገኙ የተከፈተ ዘመቻ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ። ለጥቁር ሕዝብ ክብርና ልዕልና ስትሉ፣ በፓን አፍሪካ መንፈስ፣ ሁላችሁም ጥቁር ሕዝቦች፣ ከኢትዮጵያ ጋር እንድትቆሙ ጥሪ አቀርብላችኋለሁ።
በመጨረሻም ይህ ትግል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትግል ነው። ልጆቻችን ሀገር እንዲኖራቸው የሚደረግ ትግል ነው። ልጆቻችን ክብርና ነጻነትን ለብሰው፣ በዓለም አደባባይ በኩራት ቀና ብለው እንዲሄዱ የሚደረግ ትግል ነው። በዓለም ላይ በክብር የምንጠራበት ስም እንዲኖረን የሚደረግ ትግል ነው። መኖር ወይም አለመኖራችንን የሚወስን ትግል ነው። ያለ ጥርጥር ግን እናሸንፋለን። ኢትዮጵያን ጠርቶ መሸነፍ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።
ጊዜው ሀገርን በመሥዋዕትነት መምራት የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። ከእንግዲህ እኔ መከላከያን በግንባር ሆኜ ለመምራት ከነገ ጅምሮ ወደ ትግሉ ሜዳ እዘምታለሁ። ታሪክ ከሚያደንቃቸው የኢትዮጵያ ልጆች አንዱ ለመሆን የምታስቡ ሁሉ ለሀገራችሁ ስትሉ ዛሬውኑ ተነሡ፤ ግንባር ላይ እንገናኝ፡፡ የእኛ መዝመት የሚፈጥረውን ክፍተት ከግንባር የቀሩት በሙሉ ዐቅማቸው ሸፍነው ይሠራሉ፡፡ በግንባር ያልተሰለፉ የክልልና የፌደራል አመራሮች ከመቼውም ጊዜ በላይ የልማትና አስተዳደር ሥራዎችን በሙሉ ዐቅማቸው ይከውናሉ።
ጎልማሶች በዘዴና በብልሃት አካባቢያቸውን እየጠበቁ፣ አረጋውያን እናትና አባቶች በጸሎት እየተጉ፣ ሁሉም ሰው ተባብሮ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ያረጋግጣል። ከዚህ በኋላ በሩቁ ተቀምጠን ተቺና አራሚ የምንሆንበት ጊዜ አይደለም። መደረግ ያለበትን እኛው ራሳችን እናድርገው። ለኢትዮጵያ ከእኛ በላይ ከየትም አይመጣም። ኢትዮጵያ የሚለው ስም የአሸናፊዎች ስም ነው፤ የነጻነት ምልክት ነው። አልጠራጠርም፣ የእኔ ትውልድ ለአሸናፊ ስሙና ለነጻነት ምልክቱ የሚጠበቅበትን ዋጋ ከፍሎ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በክብር መዝገብ ላይ በወርቅ ብዕር ያትማል።
አመሰግናለሁ!!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትሩር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ኅዳር 13፣ 2014 ዓ.ም

Address

G. D. Assosiation
Gunchire
11

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gurida,ጉርዳ ኸተራት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share