ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Gunchire
  • ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት

ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት በከተማችን የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እናስተዋውቃለን!!

መስከረም 5፣2019(ጉንችሬ)በጉንችሬ ከተማ አስስተዳደር የ2019 የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯልበከተማ አስተዳደሩ በሚገኘው የጉንችሬ ቁ.1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የትምህር...
15/09/2026

መስከረም 5፣2019(ጉንችሬ)
በጉንችሬ ከተማ አስስተዳደር የ2019 የትምህርት ዘመን በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኘው የጉንችሬ ቁ.1 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።

የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አ/ቋድር ሂጅራ በትምህርት ማስጀመሪያ ወቅት እንደተናገሩት ፥ ለትምህርት ዘመኑ የሚያስፈልጉ የመማሪያ መጻሕፍት፣ ቁሳቁሶችና የመማሪያ ክፍሎች ዝግጅቶችን አስቀድሞ የማጠናቀቅ ስራ መሰራቱን ጠቁሟል።

በሁሉም የከተማው የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች፣ መምህራንና የትምህርት ማህበረሰብ አባላት ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለሳቸውንም የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ናስር ተናግረዋል

ወላጆችና የትምህርት ማህበረሰቡ ለተማሪዎች ውጤታማነትና መልካም ሥነምግባር የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ሀላፊው አሳስቧል፡፡

በእለቱም የከተማው ከንቲባ አቶ አ/ቋድር ሂጅራ፣የከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀቢብ ናስር ፣የዞን ደጋፊ ባለሙያ፣መምህራኖችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

#የከተማው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው

‎የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ  ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ፣ የ2019 ዓ.ም መነሻ እቅድ አስመልክቶ ጉባዔ እና የእውቀና ሽ...
15/09/2026

‎የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ፣ የ2019 ዓ.ም መነሻ እቅድ አስመልክቶ ጉባዔ እና የእውቀና ሽልማት መድርክ እየተካሄደ ይገኛል ።

‎መስከረም 05፣2019 ዓ.ም (ጉንችሬ)

‎ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸወን በማዘመን ለማህበረሰቡ ቀልጠፍ እና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መሰራት እንዳለባቸውም ተገልጿል።

‎ በመድረኩም የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አ/ቋድር ሂጅራ ፣የከተማው ዋና የመንግሥት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሴ ደሴ፣የከተማው ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘይነባ መሃመድ እና ሌሎችም የከተማው አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

‎የጉንችሬ አከባቢ ቅድሚያ ማህበር ፕሮጀክት በ 29 ሚሊየን  3 መቶ 15 ሺህ ብር በላይ ወጪ ደረጃውን የጠበቀ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።‎‎(መስከረም...
14/09/2026

‎የጉንችሬ አከባቢ ቅድሚያ ማህበር ፕሮጀክት በ 29 ሚሊየን 3 መቶ 15 ሺህ ብር በላይ ወጪ ደረጃውን የጠበቀ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

‎(መስከረም 4/ 2019 ዓ.ም ጉንችሬ ) በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

‎ለግንባታውከ 29 ሚሊየን 3መቶ 15 ሺህ 2 መቶ 87 ብር በጀት ወጪ እንደሚፈጅና ግንባታው ከመስከረም ወር 2019 ጀምሮ እስከ መስከረም 2021 ዓ.ም ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ተብሏል ።

‎የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አ/ቋድር ሂጅራ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስርዓት በተካሄደበት ወቅት እንደገለፁት ቅድሚያ ማህበር ለጉንችሬ እና የአከባቢው ማህበረሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚታወቅ መሆኑን ገልጸው በተለይም ህጻናት ላይ ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለብዙ ቤተሰብና ህጻናት የተስፋ ብርሃን እንዲፈነጥቅ አስችሏል ብለዋል።

‎መንግስት ለትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንና ከነዚህም ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧ የነበረው የትምህርት ስረአት ከመሰረቱ ለመቀየር ህጻና ከታች ጀምሮ በቂ እውቅ ይዘው እንዲወጡ ለቅድመ አንደኛ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

‎ቅድሚያ ማህበርም የመንግስትን አቅጣጫ በመከተል ደረጃውን የጠበቀ ቅድሚያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገንባት የነገረ ሀገር ተረካቢ ህጻናት ላይ አሻራ በማኖሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎የቅድሚያ ማህበር የበላይ ጠባቂ ዶ/ር አስቻለው አበበ በበኩላቸው ቅድሚያ ማህበር ከተመሰረተ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችና ህጻናት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮችን ሲቀርፍ ቆይቷል ብለዋል።

‎አሁንም ህጻናትን ከስረ መሰረቱ ኮትኩቶ ለማሳደግ ደረጃውን የጠበቀ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ወሳኝ መሆኑንና በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት ገንብቶ ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

‎የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ተወካይ እና የመምህራን ልማት ዳይሮክተሬት ዳይሬክተር አቶ ባቂ በሰማ እንደተናገሩት በእውቀት የዳበር በስነምግባር የታነፀ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት ደረጃውን የጠበቀ ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ የሆነ ትምህርት ቤት መገንባት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል።

‎ይህም በመንግሥት አቅም ብቻ የሚቻል ባለመሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እያደረጉት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነና አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

‎የቅድሚያ ማህበር ደጋፊ የሆነው ሄልፕ ዋን ናው መስራች ሲኢኦ (CEO) ሚስተር ክሪስ ማርሎው በበኩላቸው ሀገር ተረካቢ ትውልድ የሚያፈራ ደረጃውን የጠበቀ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

‎በመርሃ ግብሩም የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር አመራሮች የቅድሚያ ማህበር የስራ ኃላፊዎች ፣የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
‎ ዘገባው የከተማው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው

ትውልድን መቅረጽ፣ አገርን ማጽናት፡ የትምህርት ጥራት የጋራ ኃላፊነታችን(የዕለቱ መልዕክት)አዲሱ የ2019 የትምህርት ዘመን ሲበሰር፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ትምህርት...
14/09/2026

ትውልድን መቅረጽ፣ አገርን ማጽናት፡ የትምህርት ጥራት የጋራ ኃላፊነታችን

(የዕለቱ መልዕክት)

አዲሱ የ2019 የትምህርት ዘመን ሲበሰር፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱና ወላጆች ለልጆቻቸው የተሻለ ነገን ተስፋ አድርገው ደፋ ቀና ሲሉ መመልከት በራሱ ታላቅ አገራዊ ጸጋ ነው።

ትምህርት የሰውን ልጅ ስብዕና ዳግም የሚገነባ ረቂቅ መሣሪያ ከመሆኑም በላይ፣ በሁለንተናዊ አስተሳሰብ ትርክት ግንባታ ውስጥ አገርን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም የማዕዘን ድንጋይ ነው።

ይህ የትምህርት መጀመሪያ ወቅት የክፍል በሮች የሚከፈቱበት ብቻ ሳይሆን አዲስ የተስፋና የዕውቀት በር ወለል ብሎ የሚከፈትበት ሊሆን ይገባል።

ይሁንና ይህን ተስፋ ወደ እውነታ ለመቀየር፣ የትምህርት ጥራትን እንደ ሀገራዊ ደኅንነት ጉዳይ ቆጥሮ ይበልጥ መሥራትን የግድ ይላል።

የ2019 የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶችን አገራዊ ብዝሃነትን በአዲስ መልክ ወደሚተረጉም፣ ዜጎችን በጋራ ጥቅሞች ዙሪያ ወደሚያስተሳስር እውነተኛ የአገረ መንግሥት ግንባታ ማዕከልነት የሚያሸጋግር ሊሆን ይገባል።

አገር የሚገነባው በአብዛኛው ማኅበረሰብ ዘንድ የጋራ ስምምነት በተደረገባቸው አዎንታዊ ትርክቶች እንጂ በከፋፋይ የበቀል ትረካዎች አይደለም።

ይህን ስትራቴጂያዊ የአስተሳሰብ ሽግግር እውን ለማድረግ ደግሞ የትምህርት ጥራት ጉዳይ ቁልፉ መሣሪያ ነው።

የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በጊዜያዊ አጀንዳዎች ወይም በዘመቻ ብቻ የሚሳካ ግብ አይደለም፤ ሥርዓታዊ ቁርጠኝነትን ይፈልጋል።

ጥራት የሚጀምረው ከክፍል ውስጥ ግብዓት፣ ከመማሪያ መጻሕፍትና ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲሁም ከተማሪዎች የዕውቀት መሠረት ቢሆንም፤ ከሁሉ በላይ ግን ማስተማርን፣ ዜጋን እንደ ማነጽ የተመለከተ መምህር ከሌለ፣ የትኛውም ሥርዓተ ትምህርት ውጤታማ ሊሆን አይችልም።

ባለፉት ዓመታት የተጀመረው የፈተና ሥርዓትን ከኩረጃና ከማጭበርበር የማጽዳት ሥነ ምግባራዊ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ቢሆንም፣ ይህ የችግሩ አንድ ገጽታ ብቻ ነው።

ትልቁ ሥራችን ተማሪዎች ፈተና ከመፍራት ይልቅ እውነተኛ ዕውቀት፣ ክህሎት፣ በፈጠራ የታነጸ ጥልቅ አስተሳሰብና ሥነ ምግባር የታጠቁ እንዲሆኑ፤ ትምህርት ቤቶችን ከማንኛውም ውጥረት የጸዱ ምቹና ሠላማዊ አካባቢዎች ማድረግ ያስፈልጋል።

የትምህርት ሥርዓታችን አገራዊ መግባባትን እንዲፈጥር ከተፈለገ፣ ስትራቴጂያዊ የሆኑ አገራዊ ምሰሶዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል።

ለአብነትም ከውጭ ግንኙነት አንጻር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወዳጅም፣ ጠላትም የሚያፈራው የህልውናው መሠረት በሆነው የውሃ ሐብቱና የባህር በር ጉዳይ ስለሆነ፣ ስለ ወንዞቻችንና ስትራቴጂያዊ ጥቅሞቻችን ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ጥልቅ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል።

በተጨማሪም ተማሪዎች የሀገራቸውን ቋንቋዎች እንዲማሩ የሚያደርገው የብዝሃ ቋንቋ አሠራርና ወጣቶች በብሔራዊ አገልግሎት አማካኝነት ከተወለዱበት መንደር ወጥተው የሌላውን ባህል፣ ሥነ-ልቦና እና ማኅበራዊ እሴት በተግባር እንዲለማመዱ ማድረግ፣ የጋራ ትርክትን በተግባር ለመገንባት የማይተካ ሚና አላቸው።

የትምህርት ጥራትና የትውልድ ግንባታ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የወላጆች፣ የማኅበረሰብ መሪዎችና የሲቪክ ማኅበራት የጋራ ኃላፊነት ነው።

ወላጅ የልጁን ውጤት ብቻ ሳይሆን ዕለታዊ ተሳትፎውን በቅርበት የሚከታተልበት፣ ማኅበረሰቡም ትምህርት ቤቶችን የራሱ ሀብት አድርጎ የሚጠብቅበት የባለቤትነት መንፈስ ሊሰፍን ይገባል።

የ2019 የትምህርት ዘመን የትውልድ ዕጣ ፈንታ የሚቀለስበት፣ የትምህርት ጥራት እንደ ሀገራዊ ደኅንነት ተቆጥሮ በተግባር የምንቆምበትና ኢትዮጵያን የሚያስቀጥል ብሩህ አእምሮ የምንቀርጽበት መሆን ይገባዋል።

ትውልድ ሳይማር አገር እንደማይጸናው ሁሉ፤ ጥራት የሌለው ትምህርትም ተስፋን ያቀጭጫል።

የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ከመስከረም 5 ጀምሮ ይጀምራልየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃ...
13/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2019 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ከመስከረም 5 ጀምሮ ይጀምራል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ማልደዮ የ2019 ትምህርት ዘመን አጀማመር አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኃላፊው በመልዕክታቸው እንደገለጹት፤ ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ አጀማመር በክረምቱ ወቅት ዘሁለገብ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።

ከእነዚህም መካከል የተማሪዎች ልየታና ምዝገባ፣ የகூ ተጨማሪ መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ የቆዩ ክፍሎች ጥገና፣ የወንበሮችና ጥቁር ሰሌዳዎች ሟሟላት እንዲሁም የትምህርት ቁሳቁሶችን ለተማሪዎች ተደራሽ የማድረግ ተግባራት ይገኙበታል።

በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራው በቀጥታ ከመስከረም 5/2019 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚጀመር አቶ ማቴዎስ ገልጸዋል።

ከመስከረም 05 እስከ 08/2019 ዓ.ም ባሉት ቀናትም የትምህርት ሳምንት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል ብለዋል።

በዚሁ ወቅትም የትምህርት ብክነት መንስኤዎችን ለመቀነስና ለመፍታት፣ ያልተመዘገቡ ተማሪዎችን ለይቶ ለማስመዝገብ፣ የተመዘገቡትም ሙሉ በሙሉ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመጡ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠራ አቶ ማቴዎስ አስታውቀዋል።

የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ወላጆች፣ መምህራንና ባለድርሻ አካላት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አጥብቀው እንዲከታተሉና የትምህርት ውጤታቸውን እንዲያሻሽሉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ትምህርት ቢሮ

መስከረም 3/2019 ዓ.ም (ጉንችሬ)‎ የሳምንቱ አበይት ዜናዎች‎‎የጉንችሬ ከተማ  ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም 4ተኛ ሩብ ዓመት 7ተኛ ዓመት በ28ኛ መደበኛ ጉባኤው  ለ2019 በጀት ዓመት 2...
13/09/2026

መስከረም 3/2019 ዓ.ም (ጉንችሬ)
‎ የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
‎‎የጉንችሬ ከተማ ምክር ቤት የ2018 ዓ.ም 4ተኛ ሩብ ዓመት 7ተኛ ዓመት በ28ኛ መደበኛ ጉባኤው ለ2019 በጀት ዓመት 204 ሚሊየን 763 ሺህ 4መቶ 55 ብር ረቂቅ በጀት መርምሮ አፅድቋል።

‎"ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በጉንችሬ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎች በመጎብኘት ተከበር።

‎በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በክረምት ወራት የ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ቤቶች አጠናቆ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

‎በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጉንችሬ አጥቢያ "ኢቲ0"190 የልጆች የልማት ፕሮጀክት፣ ተጠቃሚ የሆኑ የህፃናት ወላጆች ምስጋና አቀረቡ!!

‎በከተማው በሁለንተናዊ ዘርፍ እየታዩ ያሉ ለውጦች በ2019 በጀት ዓመት አጠናክሮ ለማስቀጠል ህብረተሰቡ በልማቱ ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ ማድርግ እንዳለበት የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ገለጸ።

‎"ብዝሃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ቃል ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር አንድነትና አብሮነትን በሚያጎለብቱ ተግባራት ተከብሯል።

‎ተቋማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግቦችን መነሻ በማድረግ እቅድ በማቀድ አመርቂ ውጤት እንዲመጣ መትጋት እንደሚገባ የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

‎በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜ 3 የጽናት ቀን"ጽኑ መሰረት ብርቱ ሀገር"በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበር ።

የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል !መስከረም 03/2019 ዓ.ምብሪክስ ወደ ሰፊ ጥምረት አድጓል፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አሁን 11 ሙሉ አባላት ያሉት ሲሆን በሩሲያ ካ...
13/09/2026

የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል !

መስከረም 03/2019 ዓ.ም

ብሪክስ ወደ ሰፊ ጥምረት አድጓል፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አሁን 11 ሙሉ አባላት ያሉት ሲሆን በሩሲያ ካዛን ጉባኤ ይፋ የተደረጉ 10 አጋር አገራትንም በልዩ የአጋርነት ማዕቀፍ በማካተት ተጽእኖውን አጠናክሯል።

የብሪክስ ጥምረት የዓለምን ሕዝብ ቁጥር ግማሽ ያህል፣ የዓለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርትን (GDP) 40 በመቶ ገደማ፣ እና የዓለምን ንግድ ሩብ ያህል ይወክላል። መጠኑ እጅግ ግዙፍ ነው። ብሪክስ ከእንግዲህ ተራ ጥምረት ብቻ አይደለም፤ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ዋነኛ ኃይል እየሆነ ነው።

የብሪክስ አባል ሀገራት በአለምአቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ የሀብት፣ የቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከል መዳረሻ ናቸው። የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የዚህ ጥምረት አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አድርጓታል።

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ድምፅ በመሆን የአህጉሪቱን ጥያቄዎች እና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ከቀሪ የቤት ሥራዎች አንዱ ይህን ታሪካዊ ዕድል በመጠቀም የጥምረቱን ግዙፍ አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ሀብቱ በቀጥታ በሚገኝበት አካባቢ እንዲመረት ማድረግ ነው።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና በማደግ ላይ ባለው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች እውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁነት አላት።

በማዕድን ዘርፍ ኢትዮጵያ ያሏትን እንደ ሊቲየም፣ ታንታለም እና ፖታሽ ያሉ ለዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የኢነርጂ ሽግግር ወሳኝ የሆኑ ሀብቶችን በሀገር ውስጥ በማቀነባበር የኢንዱስትሪ እሴት ሰንሰለቱን ለመቀላቀል ሰፊ ሥራዎችን እየሠራች ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ የሀብት ባለቤት የሆኑ ሀገራት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወጥተው የተጠናቀቁ ምርቶች አምራች እንዲሆኑ የሚያስችል የጋራ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ይፈጥራል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ የታዳሽ ኃይል አቅም በመጠቀም አረንጓዴ እና ንጹህ የኢነርጂ አቅርቦትን ለሀገራት ማዳረስ ትችላለች። የውኃ፣ የጂኦተርማል እና የሶላር ኃይል ሀብቶችን በማልማት ለቀጣናው እና ለአጋሮች አስተማማኝ የኃይል ማዕከል ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ይጥላል።

ኢኮኖሚያዊ ትስስሩ ከሀብት ማውጣትና ማቀነባበር ባሻገር በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተቋማዊ ጽናት ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል። የአሠራር ሥርዓቶቻችንን በማጠናከር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)ን ጨምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የአፍሪካን ልማታዊ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች በትክክል እንዲያገለግሉ የጋራ ጥረቶችን ማቀናጀት ያስፈልጋል። ለዚህም ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት።

ለዘላቂ ዕድገት መረጋገጥ የፋይናንስ ሥርዓቶች ፍትሃዊ መሆን አለባቸው፤ በዚህ ረገድ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የዕዳ ጫና የሚያቃልል አስተማማኝ እና ፍትሃዊ የዕዳ እፎይታ ሒደት ማሳደግ ወሳኝ ነው። የብሪክስ መድረክ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በመጠቀም ፍትሃዊ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠንካራ ድምፅ ማሰማት የሚችልበት አቅም አለው።

ከኢኮኖሚ ሽግግር ጎን ለጎን የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከምግብ ዋስትና እና ከዘላቂ ልማት ጋር ማስተሳሰር ይገባል። እንደ ኢትዮጵያ «የአረንጓዴ አሻራ» ተነሳሽነት ያሉ አሠራሮች ለአየር ንብረት ጽናት የሚሰጡትን አስተዋጽኦ በማስፋት የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ ተጨባጭ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ የጋራ ዕድገት ለመለወጥ የሚያስችል ታሪካዊ ዕድል ይፈጥራል። ኢትዮጵያም ይህን ዕድል የአፍሪካ ድምጽ በመሆን ጭምር መጠቀም ጀምራለች ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) (ጉንችሬ ፣መስከረም 3/2018) በክልሉ በ...
13/09/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(ጉንችሬ ፣መስከረም 3/2018) በክልሉ በከተሞች እና በገጠር የተጀመሩ የኮሪደር ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ተገቢ ስለመሆኑም ተመላክቷል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)እንደገለጹት የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ክልሉ ሲመሰረት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ በ300 በመቶ እድገት ማሳየቱን አብራርተዋል።

የክልሉ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከ2017 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ10 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው በማለት አብራርተዋል።

የገቢ ስራችን ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይ በዘርፉ የተሻለ ለውጥ እንዲኖር ይሰራል ብለዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ በከተሞች እና በገጠር የተጀመሩ የኮሪደር ስራዎች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

በክልሉ ከዚህ ቀደም በሰባት ከተሞች 165 ኪ/ሜ የኮሪደር ልማት ስራ ተግባራዊ መደረጉን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ በተጨማሪ 17 ከተሞችን በመጨመር የ50 ኪ/ሜ የኮሪደር ልማት ስለመጀመሩም ጠቅሰዋል።

በክልሉ በ6 ከተሞች 7 መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ መጀመራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

የንግድ ስርዓቱን ለማዘመን ብሎም በኑሮ ውድነት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በተከታታይ በተሰራው ስራ ከ180 በላይ የሰንበት እና ከሰንበት እስከ ሰንበት የግብይት ማዕከላትን መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

በዚህም ምርት ከአርሶ አደሩ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው ማህበረሰብ እንዲደርስ ማድረጉን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ሳምን ቱን ሙሉ የግብይት ስርዓት በመፈጠሩ በዋጋ ማረጋጋት ረገድ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ጠቅሰዋል።

በክልሉ ምስረታ ወቅት የነበሩ የጸጥታ ችግሮች እልባት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

በክልሉ ውስን ቦታዎች የጸጥታ ችግር ማጋጠሙን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ ከነዚህ ጥቂት ቦታዎች ውጪ ክልሉ የ24 ሰዓት የሰዎች እንቅስቃሴ የሚስተዋልበት ስለመሆኑም አስረድተዋል።

የክልሉ የጸጥታ ምክርቤት ውሳኔ ባስተላለፈባቸው ጉዳዮች ላይ በ2019 በጀት ዓመት መፍትሄ እንደሚሰጥባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው

‎መስከረም 2/2019 ዓ.ም (ጉንችሬ) ‎በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በክረምት ወራት የ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ቤቶች አጠናቆ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።‎‎በክረም...
12/09/2026

‎መስከረም 2/2019 ዓ.ም (ጉንችሬ)
‎በጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በክረምት ወራት የ በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ቤቶች አጠናቆ ለባለቤቶቹ ለማስረከብ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

‎በክረምቱ በጎ ፈቃድ የተሰሩ ቤቶች ለመኖሪያነት ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንና በርና መስኮት ያልነበራቸው ቤቶች በዛሬው እለት የማስገባቱ ስራ ተከናውኗል።

‎በከተማው በዘንድሮው አመት ቤት ለመገንባት አቅም ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በልዩ ትኩረት ቤት ተገንብቶላቸዋል።

‎የተገነቡ ቤቶች ለመኖሪያነት ምቹ ለማድረግ በጎ ፈቃደኛ የማህበረሰብ ከፍሎች እያደረጉት ያለውን ተግባር አጠናክረው በመቀጠል በገንዘብ የማይታመን የህሊና እርካታ ማገኘት እንዳለባቸው ተገልጿል።

‎ቤት የተገነባላቸው ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተናገሩት ቤታቸው ተገንብቶ ለመኖሪያ ምቹ እየተደረገላቸው መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልፀው በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለተሳተፉና አስተዋጽኦ ለበረከቱ አካላት አመስግነዋል።

‎በፕሮግራሙ የከተማው ወጣቶችና እስፓርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካብቱ ተካ፣የከተማው ወጣቶችና እስፓርት ምክትል ኃላፊ አቶ አዳነ ንጋቱ ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ዘገባው የከተማው መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ነው
‎‎በተጨማሪም ከታች ያሉትን ሊንኮች በመጫን ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያገኙ
‎📌በፌስቡክ
https://www.facebook.com/gunchireadiminstrationtowncity
‎📌በቴሌግራም
https://t.me/cummugovaffairsofficegunchire
‎ 📌 በቲውተር
https://x.com/gunchirecitygov
‎📌 በቲክቶክ
https://vm.tiktok.com/ZS91K4XwcWTuB-UQTZP/
‎📌 በኢንስታግራም
https://www.instagram.com/gunchire.comu?igsh=djhxMnBmNWw0dnFk
‎📌 በዩቲዩብ
https://youtube.com/-by6hf3wh5s?si=OebcCF92T8h4HVTI
‎ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን !

መስከረም 2፣2019(ጉንችሬ)በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጉንችሬ አጥቢያ "ኢቲ0"190 የልጆች የልማት ፕሮጀክት፣ ተጠቃሚ የሆኑ የህፃናት ወላጆች ምስጋና አቀረቡ!!በዛሬው እለት ከግ...
12/09/2026

መስከረም 2፣2019(ጉንችሬ)
በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጉንችሬ አጥቢያ "ኢቲ0"190 የልጆች የልማት ፕሮጀክት፣ ተጠቃሚ የሆኑ የህፃናት ወላጆች ምስጋና አቀረቡ!!

በዛሬው እለት ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በ2018 በጀት አመት በልማት ፕሮጀክቱ ታቅፈው በየትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እውቅና የመስጠትና ለ2019 በጀት አመት የትምህርት ቁሣቁስና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል

በኢትዮጵያ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ጉንችሬ አጥቢያ "ኢቲ0" 190 የልጆች የልማት ፕሮጀክት በኩል ድጋፋ በማድረግ በህፃናት ሁለንተናዊ እድገት ላይ አሻራ ለሚያሳርፉ ለጋስ ድርጅቶችና አካላት በህፃናት ወላጆች ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

ህፃናት በጥብቅ የድህነት አስተዳደግ ምክንያት ከሚደርስባቸው ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊ ፣ስነልቦናዊና አእምሮአዊ ጥቃቶች ለመጠበቅና ለመከላከል ፣ከቤተሰቦቻቸውና ከማህበረሰቡ ሳይነጠሉ መሠረተዊ ፍላጎቶቻቸው በማሟላት ማደግና ትምህርታቸው መከታተል እንዲችሉ ማድረግ የፕሮጀክቱ ዋና አላማ ነው።

የልጆች ልማት ፕሮጀክቱ በ2018 በጀት አመት የተሠሩ ጠቅላላ አመታዊ ሪፖርት በፕሮጀክቱ ዋና ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ይስሃቅ ሰይፉ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል

በተለይ በትምህርት ልማት ዘርፍ ለመማሪያ ቁሳቁስ እና በመንግስትና በግል ትምህርት ቤት ለሚማሩ የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የትምህርት ክፋያ መሸፈን መቻሉን ። በጤናው ዘርፍ ለታመሙ ህፃናት ከቀላል እስከ ከባድ የህክምና ወጪ መሸፈኑ፣ የአልባሳት፣ የምግብ ድጋፋ መደረጉ ዋና ዳይሬክተሩ ባቀረቡት ሪፖርት ተደምጧል።

የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ብሎም ጤናቸውን በተገቢው እንዲጠበቅ ከልማት ፕሮጀክቱ በተጨማሪ ወላጆች ከፍተኛ ክትትል በማድረግ ሀላፊነታቸው እንዲወጡ አቶ ይሳቅ አሳስበዋል ።

በኑሮ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ህፃናት መሠረታዊ ፍላጎት በማሟላት በሁለንተናዊ እድገታቸው ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራው "ኢቲ0"190 የልጆች ልማት ፕሮጀክት ለ244 ህፃናት በትምህርት፣ በጤና፣ በስርአተ ምግብ፣ በኢኮኖሚ ፣በስነልቦናና በማህበራዊ ረገድ ድጋፍ በማድረግ፣ በመንግስት አቅም ማከናወን ያልተቻለውን በማገዝ አበረታች የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል ሲሉ በምስጋና ፕሮግራሙ የተገኙ የመንግስት አካላት ገልፀዋል።

የፕሮግራሙ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆኑ የህፃናት ወላጆች እንደ ገለፁት፣ ለህፃናቱ እድገት ፕሮጀክቱ እያደረገው ያለው ድጋፍ በእነሱ የገንዘብ አቅም የማይቻል መሆኑን በመግለፅ፣ ይህንን ችግር በመረዳት ለህፃናት ልጆቻችን እድገት በማስብ፣ ድጋፍ ለሚያደርጉልን ለጋስ አካላት ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳቸው ብለዋል።

በእለቱ ለወላጆች አስተማሪ የሚሆኑ ድራማዎች እና ግጥሞች በፕሮጀክቱ በተቀፉ ተማሪዎች ቀርቧል

በመጨረሻም፦ በቀጣይም ፕሮጀክቱ ተደራሽነቱ ለማስፋት ቤተ መፃህፍት ግንባታ፣ የህፃናት መጫወቻ ግንባታና ለሌሎችም ለማከናወን በትኩረት ይሰራል ተብሏል።

#የከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነው!!

Address

Gunchire

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share