Gondar city transport office

Gondar city transport office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gondar city transport office, Government Organization, Gondar.

26/11/2022

ጎንደር‼️
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከባጃጅ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ‼️
ከተማ አስተዳደሩ ከባጃጅ ጋር ተያይዞ ያገጠሙ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በጥናት እንዲለዩ አድርጓል።በጥናቱም ቀላል የማይባሉ የአሰራር ግድፈቶች ስለመኖራቸው አረጋግጧል።ከተማ አስተዳደሩ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ ባጃጅ ወደ ከተማው እንዳይገባ ክልከላ ቢያደርግም የተለያዩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው በሰሩት ሀላፊነት የጎደለው ተግባር በሽ የሚቆጠሩ የወረዳ ባጃጆች ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ ህጋዊ የከተማ ባጃጆች ክፉኛ እንዲጎዱ ማድረጋቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

እነዚህንና ሌሎችንም ግኝቶች መሰረት በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመወሰን የተገደደ ሲሆን ወሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግም የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።ውሳኔውን ለማደናቀፍና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣት የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የሚያጋጥሙ ከሆነም ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በሚያመች መንገድ ልዩ የምርመራ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጓል።
ውሳኔዎች

✔አዲስ ባጃጅ ወደ ከተማው ለማስገባት=70,000 (ሰባ ሺህ ብር ለከተማ አስተዳደሩ የገቢዎች ተቋም ገቢ ማድረግ ይኖርበታል)
✔የከተማ ፍቃድ ባይኖራቸውም የነዳጅ ድጎማውን እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)
✔ከሰው እጅ ያለ ባጃጅ ወደከተማው በማስገባት የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 100,000(መቶ ሺህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)
✔ከጉሙሩክ በጨረታ አሸንፈው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት ለሚመጡ ባጃጆ 100,000 ብር (ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)
✔ከኮድ ሁለት ወደ ኮድ አንድ ለመቀየር ለሚፈልጉ =30,000(ሰላሳ ሽህ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት)
✔እስከ ህዳር 30 ባለው ቀነገደብ ውስጥ የሚጠበቅበትን አሟልቶ የከተማ ፍቃድ ሳይኖረው ከተማው ላይ አገልግሎት ሲሰጥ የተገኘ ባጃጅ=30,000 ብር ተቀጥቶ ከከተማው እንዲወጣ የሚደረግ ሲሆን ተግባሩም ከህዳር 19/2015 እስከ ህዳር 30/2015 ዓ/ም ብቻ የሚፈፀም ይሆናል።

ተግባሩን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችም እንዲጠናቀቁ ተደርጓል። ጎን በጎንም የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣትና ተግባሩን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል። የከተማ ፍቃድ ሳይኖራቸው አላቸው የሚል መረጃ በመስጠት ግለሰቦችን ላልተፈለገ ወጭ የዳረጉ አካላትን ለይቶና ከግለሰቦች የሚመጣን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ምርመራም የሚካሄድ ይሆናል።

ውሳኔው ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አስፈላጊውን እገዛ ከማድረግ ይልቅ ለማደናቀፍ የሚሞክሩና ያለከተማ አስተዳደሩ እውቅና በራሳቸው ስልጣን የወረዳ ባጃጅ አስገብተው በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃም ለመውሰድ የምንገደድ ይሆናል።ህጋዊ ሆነው ሳለ ኮምፒዩተር ያልገባላቸው ካሉ በጥንቃቄና በጥልቀት በማጣራትና እውነታውን ፈልገን በማግኘት መፍትሄ የምንሰጥ ሲሆን የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ ሰንዶችን ይዘን የምርመራ አካል የምናደርግ ይሆናል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር
==========

ርቀትዎን በመጠበቅ ራስዎን ከአደጋ ይጠብቁ
12/01/2018

ርቀትዎን በመጠበቅ ራስዎን ከአደጋ ይጠብቁ

10/01/2018
03/03/2016

በጎንደር ከተማ ለነባር አሽከርካሪዎች ሥልጠና በመስጠት ከሌላው ጊዜ በተለየና ባመረ መልኩ ከጎንደር ዩኒቨርስቲና ከጎንደር ፍትህ መምሪያ ጋር በመነጋገር የተሰራ ሥራ

1. ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጅ ዲፓርተመንት ጋር በመሆን በአሽከርካሪዎች ዙሪያ ለ1 ሰዓት ስልጠና እንዲሰጡ ተደርጓል
2. ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት ሥራ ደንበኞች አያያዝ በተመለከተ ለ1 ሰዓት ሥልጠና መስጠት መቻሉ
3. ከፍትህ መምሪያ ለአሽከርካሪዎች የህግ ዕውቀት እንዲኖራቸው ለ1 ሰዓት ስልጠና መስጠት በአጠቃላይ በከተማው ለሚገኙ አሽከርካሪዎች አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር ጋር በተያያዘ ከላይ በተጠቀሱት 3 ርዕሶች ጨምረን ለ5 ቀናት የሰልጣን ብዛት 2000 ለሚሆኑ አሽከርካሪዎች በምሁራን ስልጠና እንዲሰጡ መደረግ መቻሉና
4. ከጎንደር ማተሚያ ድርጅት በስፖንሰር 2500 የሚሆን በየዓመቱ የሚታደስ መታወቂያ በማሳተም ለሰልጣኝ አሽከርካሪዎች መስጠት ናቸው

በጎንደር ከተማ ለነባር አሽከርካሪዎች ሥልጠና በመስጠት ከሌላው ጊዜ በተለየና ባመረ መልኩ ከጎንደር ዩኒቨርስቲና ከጎንደር ፍትህ መምሪያ ጋር በመነጋገር የተሰራ ሥራ

1. ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጅ ዲፓርተመንት ጋር በመሆን በአሽከርካሪዎች ዙሪያ ለ1 ሰዓት ስልጠና እንዲሰጡ ተደርጓል
2. ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት ሥራ ደንበኞች አያያዝ በተመለከተ ለ1 ሰዓት ሥልጠና መስጠት መቻሉ
3. ከፍትህ መምሪያ ለአሽከርካሪዎች የህግ ዕውቀት እንዲኖራቸው ለ1 ሰዓት ስልጠና መስጠት በአጠቃላይ በከተማው ለሚገኙ አሽከርካሪዎች አደጋን ተከላክሎ ማሽከርከር ጋር በተያያዘ ከላይ በተጠቀሱት 3 ርዕሶች ጨምረን ለ5 ቀናት የሰልጣን ብዛት 2000 ለሚሆኑ አሽከርካሪዎች በምሁራን ስልጠና እንዲሰጡ መደረግ መቻሉና
4. ከጎንደር ማተሚያ ድርጅት በስፖንሰር 2500 የሚሆን በየዓመቱ የሚታደስ መታወቂያ በማሳተም ለሰልጣኝ አሽከርካሪዎች መስጠት ናቸው

ለጎንደር ከተማ ነባር አሽከርካሪዎች በትምህርት መምሪያ አዳራሽ ስልጠና ሲሰጥ
03/03/2016

ለጎንደር ከተማ ነባር አሽከርካሪዎች በትምህርት መምሪያ አዳራሽ ስልጠና ሲሰጥ

የመሰረት 1ኛ ደረጃ እና መለስተኛ ት/ቤት የሀዋሪያ ጳውሎስ ኮሚኒዩቲ ስኩልናየህብረት 1ኛ ደረጃ እና መለስተኛ ት/ቤቶች የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ትምህርት ለተማሪዎች  ሲሰጥ
21/12/2015

የመሰረት 1ኛ ደረጃ እና መለስተኛ ት/ቤት
የሀዋሪያ ጳውሎስ ኮሚኒዩቲ ስኩልና
የህብረት 1ኛ ደረጃ እና መለስተኛ ት/ቤቶች የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ትምህርት ለተማሪዎች ሲሰጥ

13/11/2015

በከተማ አስተዳደሩ ህጋዊና ህጋዊ ያልሆኑ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች
ለመለየት ተከናወኑ ተግባራትነና ሥቲከር ከተሰጠ በኃላ የታዩ ለውጦች
1. ማንኛውም አሽከርካሪ ሆነ ባለሃብት ህግን ተከትሎ መስራት እንዳለበትና ማንኛውም ሰው ከህግ ውጭ ሆኖ ሥራ መስራት እንደማይችል መረዳት ተችሏል፡፡
2. በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ህጋዊ የባጃጅ ተሸከርካሪ በመለየቱ ህጋዊና ህገወጡን በተጀመረው ቁጥጥር መለየት ተችሏል፡፡
3. ትክከለኛውና ህጋዊ ባጃጅ ብቻ ወደ ሥራ ስምሪት ውስጥ በማግባት ህዝቡን ማገልገል ተጀምሯል፡፡
4. ህጋዊ ያልሆኑ ባጃጆች ንግድ ፈቃድ ወደአወጡበት አካባቢ መሄድና መስራት ጀምረዋል፡፡
6. ህጋዊ የሆነው ከማህበራት ተሰውረው የነበሩ ተሸከርካሪዎችም ወደ መህበራት በመሄድ ከ1 ወር እስከ 6 ወር የሚደርስ ክፍያቸውን እየፈፀሙ ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
7. ማህበራት ህጋዊ የሆኑ አሽከርካሪዎችን ብቻ ይዘው ወደ ስራ እንዲገቡና የህገወጥ ባጃጅ መደበቂያ እንዳይሆኑ እረድቷል፡፡
9. የ3ኛወገን ሙሉ በሙሉ እንዲገቡ መደረጉ ቦሎ ያላስደረጉትም ቦሎ እንዲያደርጉ መደረጉ ለቁጥጥርና ክትትል አመች ሆኗል፡፡
10. ሃይማነታዊም ሆነ ፖለቲካዊ ጽሑፎች እንዲነሱ መደረጋቸው የባጃጅ ተሸከርካሪ ንግድ ፈቃድ አውጥተው ወደ ስራ የገቡት ህብረተሰቡን ለማገልገል እንጅ ሌላ ተልእኮ ይዘው መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡
11. ፋብሪካው ከገጠመላቸው ወንበር ውጭ መጨመር ተገቢ አለመሆኑና ለወደፊቱ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡
12. በቅጣት ፓድ ሲያሽከረክሩ የነበሩ ቅጣታቸውን ከፍለው በመንጃ ፈቃድ እንዲያሽከረክሩ ተደርጓል፡፡በአጠቃላይ ሲገመገም በዚህ ተግባር በርካታ ውጤቶች የተገኙ ሲሆን ይህም ተግባር ወደኋላ እንዳይመለስ ጥብቅ የሆነ ክትትልና ቁጥጥር ያስፈልጋቸዋል፡፡

የሁለቱ ምልክቶች ልዩነት ምንድነው?
13/11/2015

የሁለቱ ምልክቶች ልዩነት ምንድነው?

ምልክቱ ምንን ያመላክታል??
02/11/2015

ምልክቱ ምንን ያመላክታል??

21/10/2015

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar city transport office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gondar city transport office:

Share