02/12/2017
የፌዴራሊዝም ስርዓት ብዙህነትን በብቃት ለመስተናገድ በርካታ ዕድሎችን የሚከፍት የመንግስት ስርዓት በመሆኑ ባለፉት ሁለት ክፍለ ዘመናት በሁሉም የዓለም ክፍሎች የሚከተሉት ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያም የፌዴራል ስርዓት በተከተለችባቸው ዓመታት በርካታ ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎችን አስመዝግባለች፡፡ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያለሙትን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባት ራዕይ እውን ለማድረግና ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ለማስቻል የፌዴራሊዝም ስርዓቱ ቁልፍ መሳሪያችን ነው፡፡
ስርዓቱም መላው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በመቻቻል በመከባበርና በአንድነት ለመኖር ያስቻላቸው በመሆኑ ዘብ ሆነው ይጠብቁታል፡፡