Central Gondar Communications

Central Gondar Communications This is Central Gondar Zone Communication Office page we hope you will be using this page .

Ensure smooth flow of information between the Zonal Government and the public and facilitate the process of building a society enriched with information

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ሰላምና ጸጥታ እያስከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የእርድ እንስሳ ድጋፍ አደረገበጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰላምና ...
31/10/2025

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ አስተዳደር ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ሰላምና ጸጥታ እያስከበረ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት የእርድ እንስሳ ድጋፍ አደረገ

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰላምና ጸጥታን የማስከበር ስራ በሠራዊቱ፣ በሌሎች የጸጥታ መዋቅር አባላትና በህዝብ ተሳትፎ እየተከናወነ ሲሆን ወረዳው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት በአካባቢው ለሚገኘው የ57ኛ ክፍለ-ጦር የሀገር መከላከያ ሠራዊት የእርድ እንስሳ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርሁሴን ሁሴን በዚህ ጊዜ እንዳሉት በቅርቡ ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር ወደ ወረዳው የገባው የ57ኛ ክፍለ-ጦር የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከሌሎች የጸጥታ መዋቅር አባላትና ከህዝቡ ጋር በመተባበር በአጭር ጊዜ ሰላም ለማጽናት የሚያስችሉ ውጤቶችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ ገልጸው ህይወቱን እየሰጠ ሰላም እያረጋገጠ ለሚገኘው ሠራዊት የተደረገው የእርድ እንስሳ ድጋፍ ግዳጅን በላቀ ሁኔታ ለመወጣት እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

አክለውም ዋና አስተዳዳሪው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ነፍጥ አንግበው ህዝብን ሲያሰቃዩ የነበሩ ወጣቶች በምህረት እየገቡ መሆኑን አንስተው መንግስት ሠላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ ከጦርነት ውጭ ያሉ ሰላማዊ የድርድርና የምህረት በሮችን የዘረጋ በመሆኑ በጫካ የሚገኙ ወንድሞች ከግጭትና ጦርነት የምናተርፈው የሀብት ውድመት፣ የአካል ጉዳትና የህይወት መስዕዋትነት መሆኑን ተገንዝበው የሰላም አማራጮችን በመቀበል ህዝባቸውንና ሀገራቸውን እንዲክሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሠራዊት በ403ኛ ኮር የ57ኛ ክፍለ-ጦር ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ምክትል አዛዥ ሌትናል ኮሎኔል ቴዎድሮስ ዘመነ በበኩላቸው ከወረዳ አስተዳደሩና ከአካባቢው ህዝብ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ከሌሎች የጸጥታ መዋቅር አባላት ጋር በመቀናጀት የሚከፈለውን መስዕዋትነት በመክፈል የህዝባችን ስቃይና መከራ የሚያበቃበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም ብለዋል፡፡

ጎንደር ዙሪያ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

እየተደረገ ያለው ግጭት በአንድ ህዝብ ልጆች መካከል መሆኑን ያነሱት ሌትናል ኮሎኔል ቴዎድሮስ ዘመነ ሳይገባቸው የውጭ ጠላቶችን ተልዕኮ ይዘው የህዝብን ስቃይ በሚያራዝምና የሀገርን ልማት በሚያደናቅፍ ዓላማ በሌለው ውጊያ የተሰለፉ ወጣቶች በምህረት ወደ ህዝቡ በመቀላቀል ሰላማዊ ህይወት ለመኖር ለሚወስኑ ወንድሞቻችን መከላከያ ሠራዊቱ አስፈላጊውን የህይወት ዋስትናና እንክብካቤ ይሰጣል ብለዋል፡፡

እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ተልኳችን በብቃት እንድንወጣ አነሳስቶናል ሲሉ 34ኛ ዙር ተመራቂ  የመደበኛና አድማ ብተና ፓሊስ አባላት ገለፁ።በአማራ ክልል የተለያዩ  አካባቢዎች  ተወጣጥተ...
31/10/2025

እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ተልኳችን በብቃት እንድንወጣ አነሳስቶናል ሲሉ 34ኛ ዙር ተመራቂ የመደበኛና አድማ ብተና ፓሊስ አባላት ገለፁ።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተወጣጥተው ሲሰለጥኑ ቆይተው ጎንደር ከተማና ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተመደቡ የ34ኛ ዙር የመደበኛና የአድማ ብተና ፓሊስ አባላት በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ተመራቂ የመደበኛና የአድማ ብተና ፓሊስ ፓሊስ አባላት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ስራዎች በመጎብኘታቸው ሙያቸውን በተነሳሽነት መፈፀም እንዲችሉ የሚያነሳሳ መሆኑን በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ ፓሊስ መምሪያ ዋና ጠቅላይ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ ተናግረዋል።

የአድማ ብተና ፓሊስ የ9ኛ ሻለቃ አዛዥ ምክትል ኮማንደር አይቀርም መላኩ ደግሞ የመደበኛና የአድማ ብተና ፓሊስ አባላት የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸው በቅንነትና በታዛዥነት ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ የሚያነሳሳ መሆኑን ገልፀዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ዋና ፓሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፓሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ስማቸው ፈንታ በበኩላቸው ጉብኝቱ መደበኛ የፓሊስ አባላት ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው የወንጀል መከላከል ስራዎችን እንዲሰሩ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከተመራቂ የፓሊስ አባላት መካከል ኮንስታብል ሙሉጌታ ልመንህ ደግሞ በከተማዋ እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ስራዎች መደሰቱን ገልፆል ።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ የአደረጃጀት ምክትል አማካሪ አቶ ባንታየሁ ሞላ ደግሞ 34ኛ ዙር ተመራቂ የመደበኛና አድማ ብተና ፓሊስ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ማህበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ተባባሪ መሆኑን የገፁት አቶ ባንታየሁ ህዝቡን ባለቤት ያደረገ የሰላም ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ አንተነህ ታደሰ በበኩላቸው ተመራቂዎች ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተው በመስራት የህግ ማስከበር ስራዎችን በውጤታማነት እንዲያከናውኑ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

Gondar city communication

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ በጮንጮቅ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየለማ ያለ ቡና
31/10/2025

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ በጮንጮቅ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እየለማ ያለ ቡና

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ የበርበሬ ሰብል ከፊል ገፅታ
31/10/2025

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ የበርበሬ ሰብል ከፊል ገፅታ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ በገበባ ሳልጅ ቀበሌ የሰብል ልማት ከፊል ገፅታ
31/10/2025

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ በገበባ ሳልጅ ቀበሌ የሰብል ልማት ከፊል ገፅታ

በአለፋ ወረዳ ምርታማነትን ለማሳደግ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የገበሬ በዓላት እየተካሄደ ነው።
31/10/2025

በአለፋ ወረዳ ምርታማነትን ለማሳደግ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የገበሬ በዓላት እየተካሄደ ነው።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ በከርከር እንዲቪና ቀበሌ በክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ገፅታ
31/10/2025

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ በከርከር እንዲቪና ቀበሌ በክላስተር እየለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ገፅታ

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የአካባቢ ጥበቃ ስነምህዳር ተፋሰስ አያያዝ ቡድን የአፈፃፀም ግምገማ እና የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ ባሳለፍነው 2017 በጀት ዓመት እንቦጭ አረ...
31/10/2025

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የአካባቢ ጥበቃ ስነምህዳር ተፋሰስ አያያዝ ቡድን የአፈፃፀም ግምገማ እና የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ

ባሳለፍነው 2017 በጀት ዓመት እንቦጭ አረምን ከጣና ሐይቅ ላይ ለማስወገድ የተለያዩ ስራዎች መሰራቱ ተገልጿል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የአካባቢ ጥበቃ ስነምህዳር ተፋሰስ አያያዝ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ እያየኝ ብርሃኔ በዚህ ወቅት እንዳስታወቁት ባሳለፍነው 2017 በጀት ዓመት እንቦጭ አረምን ለማስወገድ የማኅበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ መርኃግብር በዞኑ በምዕራብ ደምቢያ፣ ምስራቅ ደምቢያ፣ ጎንደር ዙሪያ እና ጣቁሳ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች ላይ መሰራቱን አስታውቀዋል።

በዚህ አርሶ አደሩ ጣና ሐይቅ የሕይወታቸው መሰረት መሆኑን ተረድተው ላለፉት ዓመታት እንቦጭ አረምን ለማስወገድ ጥረት እያደረጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በዚህም የጣና ሐይቅ አዋሳኝ ወረዳዎችን የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ በመፍጠር በተከናወነው ስራዎች 1ሺህ 600 በላይ ሄክታር የሚሆነውን የእንቦጭ አረም ማስወገዳቸውን አስታውሰዋል።

በዘላቂነት አረሙን ለማስወገድ ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ለማድረግም የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በዛሬው እለትም በ2018 በሚከናወኑ ስራዎች ዙሪያ የዞንና ወረዳ የስራ ኃላፊዎችና ቡድኖች እንዲሁም ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ በጭሎ ቀበሌ የመጀመሪያና መካከለኛ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ። የምግብ ምገባ ስርዓቱን ያስጀመሩት የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ...
30/10/2025

በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ በጭሎ ቀበሌ የመጀመሪያና መካከለኛ ፩ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች የምገባ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ።

የምግብ ምገባ ስርዓቱን ያስጀመሩት የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሀብቴ ብርሌ እንዳሉትም ይህ ፕሮግራም መጀመሩ ተማሪዎች ሳያረፍዱ ትምህርታቸውን በሚገባ ለመከታተል ያመቻል ያሉ ሲሆን የምገባ ፕሮግራሙ ቀጣይነት እንደሚኖረው የገለፁ ሲሆን የህብረተሠቡን ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑንና ቀጣይም ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች የማስፋት ስራ እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም የምገባ መርሀ ግብሩ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኢንቨስትመንት መምሪያ ሀላፊ አቶ የአብስራ እሸቴ እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የትምህርት ፅ/ቤት ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የምገባ ስርዓቱም በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደር የተጀመረ ሲሆን የቅድመ አንደኛ ተማሪዎችን ያካተተ መሆኑን የት/ቤቱ ር/መምህር ወ/ሮ በጎሠው ዘለቀ ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በፕሮግራሙ ተገኝተው እንደተናገሩት በመንግስት የተጀመረው የምገባ ስርዓት ጥሩ መሆኑን እና ተማሪዎች የመማር ፍላጎታቸው እንዲጨምር ያደርጋል ሲሉ አስተያየቶችን ሰጠዋል።

300 የሚደርሱ ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራሙ ተካፋይ ሁነዋል።

ምስራቅ ደምቢያ ኮሚኒኬሽን

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በአምባጊዮርጊስ ዙሪያ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ዘር እየተከናወነ ነው።
30/10/2025

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በአምባጊዮርጊስ ዙሪያ ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ዘር እየተከናወነ ነው።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ "ሠላም ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።በመድረኩ ከወገራ እና ከዳባት ወረዳ እንዲሁም ከአምባጊዮርጊስ ከተማ  አስተዳዳር...
30/10/2025

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ "ሠላም ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ከወገራ እና ከዳባት ወረዳ እንዲሁም ከአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳዳር የተወጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የኤክስፖርት ምርቶች ግብይትን አስመልክቶ ከዞኑ ግብረ ሀይል ጋር በምርት አቅርቦትና በህግ ማስከበር ስራዎች ዙሪያ የ...
30/10/2025

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የኤክስፖርት ምርቶች ግብይትን አስመልክቶ ከዞኑ ግብረ ሀይል ጋር በምርት አቅርቦትና በህግ ማስከበር ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ

የግብረ ሀይሉ ም/ሠብሳቢ የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አይቸው ታረቀኝ እንደተናገሩት የኤክስፖርት ምርቶችን ግብይት ምቹ ለማድረግ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለዉ የግብረ ሃይል መዋቅር በተቀናጀ እና በተጠናከረ አግባብ በጥብቅ ዲሲፕሊን ተግባራትን እየገመገመ በመሄድ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወን እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለዚህም የግብይት ስርዓቱ ምቹ እንዲሆን ህገወጥ ነጋዴዎችንና ደላላዎችን መቆጣጠር እንደሚገባ ያስገነዘቡት ኃላፊው በህግ ማስከበርና መሰል ሰራዎች ላይ ጠንካራ የሆነ የቁጥጥር ስራዎችን በውጤታማነት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ የፀጥታ አካላት ወጥ በሆነ መልኩ ተቀናጅተዉ በመስራት ኃላፊነታቸዉን መወጣት ይጠበቅባቸዋልም ብለዋል፡፡

ከኤክስፖርት ምርቶች ግብይት ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግና አሰራሩን ተከትሎ እንዲፈፀም ለማድረግ የህብረተሰባችን የገበያ ፍላጎት በጠበቀ መልኩ ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ለማስቻል ተገቢዉን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Gondar Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Central Gondar Communications:

Share