Angereb Kebele PP የአንገረብ ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Angereb Kebele PP የአንገረብ ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት

Angereb Kebele PP የአንገረብ ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ይህ የአንገረብ ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት ገፅ ነው፡፡

የአማራን ህዝብ እረፍት በመንሳት የኢኮኖሚ ሰቀቀንን ማስታገስ እና ዕኩይ ዓላማን ማሳካት አይቻልም! በክልላችን በደንብ ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር አስተማማኝና ገቢ ለማግኘት መማር እና ማገናዘብ...
18/07/2023

የአማራን ህዝብ እረፍት በመንሳት የኢኮኖሚ ሰቀቀንን ማስታገስ እና ዕኩይ ዓላማን ማሳካት አይቻልም!

በክልላችን በደንብ ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር አስተማማኝና ገቢ ለማግኘት መማር እና ማገናዘብ የማይጠይቅ መሆኑን ነው። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በግልፅ እንደሚታዬው ሳይደክሙ ገንዘብ ለማግኘት ብሎም የኢኮኖሚ ሰቀቀንን ለማስታገስ የአማራን ህዝብ ዕረፍት መንሳት እና ችግሩንም ለገቢ ምንጭነት መጠቀም ነው።

የአማራ ፖለቲካ የተለያዬ ዓላማ እና ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች እና ቡድኖች ገብተው የሚፈተፍቱበት፣ የፖለቲካ ተሳትፏቸውም የግል ዓላማቸውን በማሳካት እና የኢኮኖሚ ሰቀቀናቸውን በማስታገስ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለህዝቡ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም።

እንዲያም የአማራ ህዝብ ሰላም እጦት፣ መታወክ እና ችግር ውስጥ መግባት ዕኩይ ዓላማ ላነገቡ ሀይሎች ከፍተኛ የገቢ ምንጫቸው ነው። እነዚህ ሀይሎች እራሳቸውን የህዝብ ነፃ አውጭ አድርገው በመሳል "እኔ አውቅልሀለሁ በሚል" መታበይ ለህዝቡ በደል እና ጭቆና እየደረሰበት እንደሆነ በመስበክ በስነ-ልቦናው እንዲጎዳ እና ሆድ እንዲብሰው ተግተው ይሰራሉ። ምናልባት ህዝቡ ሰላሙ የተረጋጋ እና ወደ ልማቱ የተመለሰ ከመሰላቸው አዳዲስ የግጭት እና የብጥብጥ አጀንዳዎችን ጠምቀው ይረጫሉ። ምክንያቱም የገቢ ምንጫቸው የተመሰረተው በህዝቡ ችግር ላይ ስለሆነ ነው።

የነዚህ ሀይሎች አሰላለፍ እና የጥቅም ትስስር የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ፍላጎት ነው። ይህም የሚፈፀመው በሀገር ውስጥ ባሉ እና ከሀገር ውጭ ባሉ ሀይሎች ነው።

ከሀገር ውጭ ያለው ሀይል የግል ዓላማውን ለማሳካት የፖለቲካ ፍላጎት ያለው ሲሆን በሀገር ውስጥ ያለው ደግሞ የኢኮኖሚ ሰቀቀኑን ለማስታገስ የገንዘብ ፍላጎት ነው ያላቸው። በመሆኑም ሀገር ውስጥ ያለው ሀይል ውጭ ካለው ሀይል አፍራሽ አጀንዳዎችን እየተቀበለ በማምጣት ህዝቡ ወደ ግጭት ውስጥ እንዲያመራ እና ክልሉ እንዲታመስ ተግቶ ይሰራል። ለአገልግሎቱም ጠቀም ያለ ገንዘብ እየተዋጣ በግል እና በቡድን ውጭ ካለው ሀይል ይላክለታል።

ሀገር ውስጥ ያለው ሀይል ከውጭ የሚላክለት ገንዘብ ያነሰው ከመሰለው እና የበለጠ ለማግኘት ከጓጓ ሀገር ውስጥ በተለይም በአማራ ክልል ውስጥ የግጭት መንስዔዎችን ይጠነስሳል። እራሱ የሚፈጥራቸውን ችግሮች መልሶ በማንሳት መንግስት እና ህዝቡን ለመነጣጠል የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ይነፋል። አልፎም መንግስትን በማስወገድ ህዝቡን ለማውጣት እየታገለ እንደሆነ በመስበክ ለትግል በሚል ተጨማሪ ገንዘብ ከውጭ ያስልካል። በሚያገኘው ገንዘብም ቤት እና መኪና ይገዛል፤ ህይወቱን በኢኮኖሚ ያደራጃል፤ በተረፈውም ታጋይ መስሎ ለመታዬት ጠብመንጃ ገዝቶ ይታጠቃል። የጠመንጃው ፎቶ ወደ ውጭ ሲላክ ተዓማኒነት ከመፍጠር ባለፈ ለሌላ የገቢ ምንጭም ይሆናል።

የህዝባችን ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮዓዊ ችግሮችም ቢሆኑ ለጥቅመኛው ቡድን ትልቅ ዕድሎች እና የገቢ ምንጮች ናቸው። ህዝቡን በችግሮቹ እየገቡ በተቆርቋሪነት ስሜት "መንግስት ጨቁኖሀል፣ ከሌላው ተለይተህ ልትጠፋ ነው፣ ስለዚህ ልማትህን አቁመህ ለህልውናህ ታገል" የሚሉ ወሬዎችን በመንዛት ከፍተኛ የሽብር ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ። መንግስትን ጠላት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን ጠላት፣ ኦሮሞውን ጠላት፣ ትግሬውን ጠላት፣ አጠቃላይ የፀጥታ አካላትን ጠላት እንዲሁም የክልሉን ህዝብ በዘውግ በመክፈል አንዱን የአንዱ ጠላት አድርገው ይሰብካሉ።

ከሰሞኑ ደግሞ የፀጥታ ሀይሉ በተለይ ፖሊስ እና ሚሊሻው እየፈረሰ እና መንግስት በመክዳት ወደ ጫካ እየገባ እንደሆነ ከፍተኛ የሆነ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ይገኛሉ። በተጨማሪም የመንግስት አመራሩ ወረዳውን እና ዞኑን ጥሎ እየሸሸ እንደሆነ በሀሰት እየሰበኩ ሲሆን የተደራጀው ጥቅመኛ ቡድን አካባቢዎችን እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ በራሱ ያስነግራል።

የዚህ ሰሞነኛ የሀሰት መልዕክት ዋና ዓላማው ደግሞ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባሉ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲገባ፣ የመንግስት አመራሩ ተረጋግቶ ህዝቡን እንዳይመራ እና ሰላም ተናግቶ ክልሉ ወዳቀዱት ብጥብጥ እንዲያመራ በማለም ነው። ምክንያቱም የጥቅም ሰንሰለታቸው ዓላማና ግብ ክልሉን ማፈራረስ ስለሆነ ነው። ከላይ እንደተገለፀው የነዚህ ሀይሎች የጥቅም ምንጭ እና ዕኩይ ዓላማ መሳካት የክልሉ መበተን ነው። ዓላማቸው እስከተሳካና ጥቅማቸው እስከተበረ ድረስ የህዝብ ችግር እና የክልሉ መታወክ ደንታቸው አይደለም።

ይሁን እንጂ የነዚህ ሀይሎች ዓላማ እና ፍላጎት ከህዝብ የተደበቀ አይደለም። መንግስትም ድርጊቱን እና ሰንሰለቱን በውል ያውቀዋል። ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ ዕኩይ ዓላማ ያነገቡ እና በሥሙ ብሎም በችግሩ የሚነግዱ ሀይሎችን አምርሮ ሊታገላቸው ይገባል። በዚህ ዘመን አማራን ያከለ ታላቅ ህዝብ እንዴት የማንም ወሮ በላ ቡድን እና ግለሰብ መጫወቻ ይሆናል። በሰላሙ መታወክ ምክንያት ከሌላው ኢትዮጵያዊ በተለዬ እንዴት በልማቱ ወደ ኋላ ይቀራል። ስለዚህ መላው ህዝብ ችግር እየደገሱለት በችግሩ የሚነግዱ ሀይሎችን ታገሱ ሊላቸው ይገባል።

መንግስት እንደ መንግስት ህግ የማስከበር እና የህዝቡን ሰላም የማስጠበቅ ሥራ ሊሰራ ይገባል። ለዚህ ደግሞ አመራሩ እና ህብረተሰቡ ተናቦ እና ተቀራርቦ በመሥራት እነዚህን በህዝብ ችግር የኢኮኖሚ ሰቀቀናቸውን ለማስታገስ እና የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት የሚሰሩ ሀይሎችን አጋልጦ በማውጣት በጋራ ሊታገሏቸው ይገባል። እነዚህ ሀይሎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ህዝቡን ነው እየጎዱት የሚገኙት። ስለሆነም የመንግስት ቀዳሚ ተግባሩ የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ በመሆኑ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እና ህዝቡን ብሎም ክልሉን ሊታደግ ይገባል።

 !!“ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን!” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሁኔታዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የፋሲል ክፍለ ከተማ፤ በአንገረብ ቀበሌ አስተዳደር ከጥቃቅን አን...
01/06/2023

!!

“ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ህዝባችንን እናሻግራለን!” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ሁኔታዎችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የፋሲል ክፍለ ከተማ፤ በአንገረብ ቀበሌ አስተዳደር ከጥቃቅን አንቀሳቃሽ አባላት ጋር ኮንፈረንስ ተካሄደ።

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"

👉 የአንገረብ ቀበሌ አስተዳደር የFacebook ገፅ https://www.facebook.com/profile.php?id=100071294142260&mibextid=ZbWKwL

01/06/2023

Address

Gondar
6200

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Angereb Kebele PP የአንገረብ ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Angereb Kebele PP የአንገረብ ቀበሌ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት:

Share