Azezo subcourt/ አዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት

Azezo subcourt/ አዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Azezo subcourt/ አዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት, Government Organization, azezo, Gondar.

20/06/2023

የፅሁፍ ማስረጃ የሚቀርብበት ሥነ-ስርዓት

20/06/2023
19/06/2023

ቤት ሰብሮ በመግባት የተለያዩ አልባሳት ፣ኮንካ ቴሌቪዥን እና ስማርት ሳይክል የሰረቀው እና እጅ ከፍንጅ የስርቆት ወንጀል የተከሰሰው ወጣት በ10 አመት /አስር አመት/ቀላል እስራት መቀጣቱን የአዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አስታወቀ፡፡
ከሳሽ - - - ዐቃቢ ህግ
ተከሳሽ - - - ባንተነው መተኪያ
አድራሻዉ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ነዋሪ የሆነዉ ተከሳሽ ያልተገባ ብልጽግና ለማግኘት አስቦ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ሲሆን አዘዞ ከተማ ቀበሌ 19 ልዩ ቦታ አባሳሙኤል ሚካኤል ሰፈር ከግል ተበዳይ መኩሪያው ብርሀኑ መኖሪያ ቤት ቤቱን ሰብሮ በመግባት የግል ተበዳይ ንብረት የሆነ፡-
1ኛ. ኮንካ ቴሌሺዥን ግምቱ 10000 /አስር ሽህ ብር/
2ኛ.እስማርት ሳይክል ግምቱ 31000 /ሰላሳ አንድ ሽህ ብር/
3ኛ.2 ጅንስ ሱሪ የተለያዩ ቀለም ያላቸው እያንዳንዱ ዋጋ 2000 /ሁለት ሽህ ብር/ ጠቅላላ 4000 /አራት ሽህ ብር/
4ኛ.የሴቶች የባህል ቀሚስ ግምቱ 7000 /ሰባት ሽህ ብር/ ጠቅላላ ድምር 52000/ሀምሳ ሁለት ሽህ ብር/ የሚያወጣውን ንብረት ሰርቆ ከቤት አውጥቶ ከቤቱ ደጃፍ ላይ ከደረደረ በኋላ ተጨማሪ ንብረት ለመውሰድ ከቤት ውስጥ እየሰረሰረ እያለ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ እጅ ከፍንጅ በመያዙ በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣዉን የኢ.ፌ.ድ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 669/3/ለ/ የተመለከተዉን በመተላለፍ በተከሰሰበት የእጅ ከፍንጅ ስርቆት ወንጀል ተከሷል ሲል የአዘዞ ንዑስ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት ክስ መስርቷል፡፡
ተከሳሽ በዐቃቢ ህግ በቀረበበት ክስ መሰረት የተመሰከረበት በመሆኑ ጥፋተኛ ከመባሉ በፊት እንዲከላከል ተፈቅዶለት ተከሳሽ 2 የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ቢያሰማም የተከሳሹ ምስክሮች ቃል እርስ በእርስ የተጣረሰ በመሆኑ ከጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ያላስረዳ ስለሆነ ተከሳሽን ፍ/ቤቱ ጥፋተኛ ነዉ በማለት የጥፋተኝነት ዉሳኔ ሰጥቷል፡፡
የዐቃቢ ህግ የቅጣት አስተያየት ተከሳሽ ከአሁን በፊት በከባድ ስርቆት ተከሶ 6 አመት ተቀጥቶ የክስ ሪከርድ ያለበት በመሆኑ እና እና ከእስር የተፈታበት ጊዜም በ14/7/2014 ዓ/ም ስለሆነ እና ከጥፋቱም ሊማር ስላልቻለ አሁንም እርሱን እና ሌሎችን ሊያስተምር የሚችል አስተማሪ ቅጣት ይሰጥልን ሲል አሳስቧል፡፡
የተከሳሽ የቅጣት አስተያየት የቤተሰብ አስተዳዳሪ ነኝ ሶስት ልጆችና ሚስት አለኝ፣
አሁን በፊት 5 አመት የተቀጣሁበት ነፃ የተባልኩት ስላለኝ እንደ ቅጣት ማክበጃ እንዳይያዝብኝ፡፡
ፍ/ቤቱም በመመሪያ አንቀጽ 4/7/ በተሰጠው ፍቅደ ስልጣን መሠረት በእርከን 29 ውስጥ በመንሸራሸር የወንጀል ህጉን አንቀጽ 1 ላይ የተቀመጡትን አላማና ግብ ግምት ውስጥ በማስገባት ሌሎችን ያስተምራል የወንጀል ድርጊት እንዳይፈፅሙ ያስጠነቅቃል ያለውን ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከግንብት 10 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በሚታሰብ በ10 አመት ቀላል እሰራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን አዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት አስታውቋል፡፡

19/06/2023

Address

Azezo
Gondar

Opening Hours

Monday 02:30 - 06:30
19:30 - 23:30
Tuesday 02:30 - 06:30
19:30 - 23:30
Wednesday 02:30 - 06:30
19:30 - 23:30
Thursday 02:30 - 06:30
19:30 - 23:30
Friday 02:30 - 05:30
19:30 - 23:30

Telephone

+251581141049

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Azezo subcourt/ አዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Azezo subcourt/ አዘዞ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤት:

Share