Gondar City Prosperity Party /GPP/

Gondar City Prosperity Party /GPP/ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gondar City Prosperity Party /GPP/, Political Party, Ethiopia, Gondar.

ወገን የህፃናት የእናቶች መረጃ  ድርጅት ለ130  ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች የገቢ ማስገኛ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ድርጅቱ ለ130  ተጋላጭ ለሆኑ  ሴቶች የገቢ ማስገኛ ለእያንዳንዳቸው  1...
25/10/2025

ወገን የህፃናት የእናቶች መረጃ ድርጅት ለ130 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች የገቢ ማስገኛ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ድርጅቱ ለ130 ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች የገቢ ማስገኛ ለእያንዳንዳቸው 10ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ።

የወገን ህፃናትና እናቶች መረጃ ድርጅት ስራ-አስኪያጅ ወይዘሮ ህብስት መኮነን እንደገለጹት ድርጀቱ በጤና፣ በንፁህ ውሃ አቅርቦት ፣ በትምህርት ፣ በግብርና እና በሌሎች ዘርፈ ብዙ የማህበረሰቡን ችግር ፈች ድጋፍ እና በርካታ ስራዎችን እያከናወነ ያለ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል ።

በዚህ ሳምንት ብቻ የበርካታ እናቶች እና እህቶች አስከፊ ችግር ለመቅረፍ እና መከላከል ይቻል ዘንድ ከተለያዩ የማዕከላዊ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች ለተወጣጡ 32 የህክምና ባለሙያዎች ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በፊስቱላና ማህፀን መውጣት ዙሪያ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እንዲያገኙ ማድረጉን እና
ዛሬ ደግሞ በገቢ ማስገኛ ለተሰማሩ ለ130 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች ለእያንዳንዳቸው 10ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል ።

በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ታሳቢ በማድረግ የህይወት ክህሎት ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል ።

በዚህ ዓመት 900 በላይ ለሚሆኑ እናቶች የገቢ ማስገኛ ለእያንዳንዳቸው ከ10ሺህ እሰከ 20 ሺህ ድጋፍ መደረጉንም ገልጸዋል ።

ወገን የህፃናት የእናቶች መረጃ ድርጅት የቦርድ አመራር ዶክተር አዳነ ከበደ በበኩላቸው ወገን በተለያዩ ስራዎችን በመስራት በርካታ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል ።

ለዛሬ ያደረገው ድጋፍ ለስራ መስሪያ በመሆኑ የንግድ ክህሎታቸውን በማዳበር ሁለትና ከዚያም በላይ በመቀናጀት ወይም በተናጠል ከተረጂነት ለመውጣት መስራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል ።

በመስራት መቆጠብ ለተሻለ ስራ ራስን ማዘጋጀት እንደሚገባም ገልፀው በጋራ ሆኖ በመስራት ክፍተቶች በመሙላት ሀብት ለመፍጠር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው አስርድተዋል ።

ካላችሁበት የኑሮ ዘቤ ለመወጣት በጋራ መስራት፣መደጋገፍ ፣መቆጠብ እና ሀብት በማፍራት በኢኮኖሚው ተወዳዳሪ መሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሴቶች ንቅናቄ ተሳትፎ ማስፋፊያ ቡድን መሪ አቶ ተከታይ ጫቅሉ ደግሞ ወገን በጎንደር ከተማ ለበርካታ ሴቶች ድጋፍ እያደረገ ያለ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል ።

ድርጅቱ ለበርካታ ሴቶች ፣ህፃናት ድጋፍ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በገቢ ማስገኛ ዝቀተኛ ገቢ ያላቸውን ድጋፍ በማድረግ በኑሮ ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል ።

ድጋፍ ለሚሹ የህብርተሰብ ከፍሎች ድርጀቱ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

ድጋፍ የተደረገላቸው ለድርጅቱ ምስጋና አቅርበዋል ።

በፋሲል ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ- ምግባር ኮሚሽን በስነ-ምግባር መመሪያ ዙሪያ ለክፍለ ከተማና ለቀበሌ አመራሮች ለቀበሌ የኮሚሽን አመራሮችና ለህብረት አመራር አባላት  ...
25/10/2025

በፋሲል ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ- ምግባር ኮሚሽን በስነ-ምግባር መመሪያ ዙሪያ ለክፍለ ከተማና ለቀበሌ አመራሮች ለቀበሌ የኮሚሽን አመራሮችና ለህብረት አመራር አባላት ስልጠና ተሰጠ።

በስልጠናው የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች የቀበሌ ኮሚሽን አመራሮችና የህብረት አባላት ተገኝተዋል ።

የፋሲል ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ም/ሀላፊ አቶ ታደሰ ፈረደ ይህ መመሪያ “የብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀቶችና አባላት የተልዕኮ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 26/2017” ተብሎ እንደሚጠቀስ ያብራሩ ሲሆን አንቀጽ ሁለት፡- ትርጉም ዝርዝር ተግባራትን በማንሳት አብራርተዋል።

የመመሪያው ዓላማ የፓርቲው አባላትና አደረጃጀቶች በግልጽ ተልዕኮ ላይ ተመስርተው በየደረጃው በታቀደና በተቀናጀ አግባብ ጠንካራና ውጤታማ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው በማድረግ የፓርቲውን ጥንካሬ፣ ውጤታማነትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልፀዋል።

የአባላትና አደረጃጀቶች ተልዕኮ አፈጻጸም መርሆዎችየአባላትና አደረጃጀቶች ተልዕኮ አፈጻጸም ስራ በሚከተሉት መርህን መሰረት ያደረገ በትኩረት እንደሚመራ የገለፁ ሲሆን የአባላትና አደረጃጀቶች ተልዕኮ በፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተመስርቶ በአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ላይ የተመሠረተና ውጤታማ መሆን ይኖርበታል በማለት ገልፀዋል።

የፋሲል ክፍለ ከተማ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ አስካል ተገኘ የአባላትና አደረጃጀቶች ተልዕኮ በየደረጃው አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ማዘጋጀትና በተቀናጀ አግባብ መፈጸም በእጅጉ ወሳኝ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የአባላትና አደረጃጀቶች ተልዕኮ አፈጸጻም በየጊዜው እየተገመገመ ውጤታማነቱ ተለይቶ በኢንስፔክሽን ስራ ማረጋገጥና የፓርቲ ቁመና በሚገባ በመለየት በምዘና ስርዓት መለየት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በኮሚሽኑ መመሪያ መሰረት የፓርቲ ተግባራትን በትኩረት መስራት እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን የህብረትና የቤተሰብ አደረጃጀቶችን በማጠናከር አቅማቸውን በማጎልበት ዕለት ዕለት ውጤታማ ስራ ለመስራት የኮሚሽኑ ሚና በእጅጉ የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል።

የበጋ መስኖ ሰንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ  እየተሰራ መሆኑን የጎንደር ከተማ ግብርና መምሪያ ገለፀ።የጎንደር  ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን  ሩብ ዓመት...
25/10/2025

የበጋ መስኖ ሰንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የጎንደር ከተማ ግብርና መምሪያ ገለፀ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማና የበጋ መስኖ ስንዴ ንቅናቄ መድረክ አጋር አካላት በተገኙበት አካሄዷል።

ጥራትና ውጤትን መሰረት በማድረግ በትኩረት በመስራት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰሩ መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ አደባ ገልፀዋል።

በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን የገለፁት መምሪያ ኃላፊው የበጋ መስኖ ስንዴ ምርታማነት ሆነ የአርሶ አደሩ የማምረት ፍላጉቱ በየጊዜው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል ።

ባለፈው ዓመት በበጋ መስኖ ሰንዴ 33 ኩንታል በሄክታር ምርት ለማግኘት ታቅዶ ግብዓቶችን በአግባቡ በመጠቀምና ተገቢው ድጋፍ በማድረግ 34 ኩንታል በሄክታር ማግኘት መቻሉን ገልጸዋል ።

በ2018 በጀት ዓመት የበጋ ሰንዴ የአርሶ አደር በዓል በማካሄድ ከሞዴል አርሶ አደሮችን ልምድ እንዲወስዱ በማድረግ በሄክታር 39 ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ 600 ሄክታር መሬት ለማልማት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል ።

ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ግብዓት አቅርቦት በማሟላት ለውጤታማነት በትኩረት ይሰራ ያሉት ኃላፊው በበጋ መስኖ ስንዴ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ቤንዚል ቅድሚያ እንድያገኙ በቅንጅት እንደሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

በክርምት ያለፈን የሰብል አይነት በበጋ ለማካካስ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል ።

የገጠር ኮሪደር ልማት ሁለት የገጠር ቀበሌዎች ተለይተው በአንዱ የገጠር ቀበሌ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል ።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሀብት ባለሙያ አቶ ጨመረ ተክሌ በበኩላቸው ከመስኖ ልማትና የተፈጥሮ ሀብት ስራዎችን በተገቢው መንገድ መፈጸም ያስፈልጋል ብለዋል።

ሞዴል ቀበሌ መስርታ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ባለሙያው የአፈር ማዳበሪያ ፣የቤንዚን ችግርን ለመፍታት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

የመስኖና የበጋ ሰንዴ እቅድ ለማሳካት ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተፈጠር መሆኑን የመምሪያው የመስኖና አትክልትና ፍራፍሬ ቡድን መሪ ድርስ አንዳርጌ ናቸው ።

በቀጣይ የድጋፍ ክትትል ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ ቡድን መሪው አመላክተዋል ።

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የነዋሪዎችን የኢኖሚያዊና የማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት  የጀመሩትን  ቅንጅታዊ አሰራር  አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለፁ።የአማራ ሴቶች ማህበር ከሄልቤታስ...
25/10/2025

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የነዋሪዎችን የኢኖሚያዊና የማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የጀመሩትን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለፁ።

የአማራ ሴቶች ማህበር ከሄልቤታስ ኢትዮጵያና ከአማራ አካባቢያዊ አስተዳደር ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ጋር በመተባበር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጋራ የምክክር ፎረሞ ተካሂዷል።

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በመንግስትን የማይሸፈኑ የነዋሪዎችን የልማት ጥያቄዎች በመሸፈን ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው በውይይት ፎረሙ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኃላ ገልፀዋል።

በአዲሱ በጀት ዓመት እንደ ከተማ አስተዳደር በርታ ስራዎችን ለማከናወን አቅደናል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በከተማዋ ለሚያከናውኗቸው ስራዎች ለማገዝ ዝግጁ ነን ብለዋል።

መንግስታዊ ተቋማት መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀትና ያሏቸውን ሃብቶች በአግባቡ በመጠቀም የህብረተሰቡን ችግሮች በመቅረፍ ረገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ምክትል ከንቲባዋ አሳስበዋል ።

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለከተማዋ እድገት እውቀታቸውን ፣ተሞክሯቸውንና ፣ሃብታቸውን ለከተማዋ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የጎንደር ከተማ ገንዘብ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሰላማዊት ቦጋለ ደግሞ የአማራ ሴቶች ማህበር ከሄልቤታስ ኢትዮጵያና ከአማራ አካባቢያዊ አስተዳደር ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በስራ ዕድል ፈጠራ ፣የምክር ቤት አባላትን አቅም በመገንባት፣ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ በማድረግ፣ለሴቶች የስራ ዕድል በመፍጠርና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በከተማችን በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ለሚካሄደው የተማሪዎችን የምገባ ፕሮግራም ላይ ሁሉም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።

በአማራ ሴቶች ማህበር ከሄልቤታስ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአማራ አካባቢያዊ አስተዳደር ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ አደባባይ ምህረት ደግሞ ፕሮጀክቱ በዚህ ዓመት ብቻ ፕሮጀት በመቅረጽ 400 ሚሊየን ብር ለክልሉ ልማት አስተዋፅዎ ማበርከቱን ገልፀዋል።

ፕሮጀክቱ በ5 ድህነት ተኮር የመንግስት ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የገለፁት የፕሮጀክት አስተባባሪው ማህበሩ 10 ሚሊየን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ከዚህ ቀደም ተሰጥቶ መቆየቱን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ከተሰጠው 10 ሚሊየነ ብር ብድር በመስጠት ለማስመለስ በተደረገው ጥረት 4 ሚሊየን በመሰብሰብ 6 ሚሊየን ብር እስካሁን አልተመለሰም ያሉት ፕሮጀክት አስተባባሪው ብድሩን ለማስመለስ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ በእውቀት ማስተዳደር ስራዎች(Knowldge management)፣ አቅም ግንባታ ስራዎች በማከናወንና ፣የመራጭ ተመራጭ መድረኮችን ማካሄድ እንዲሁም የምክር ቤት አባላትን አቅም በማሳደግ ሞጋች ማህበረሰብ በመፍጠርና ምክር ቤት አባላትን ማብቃት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የህዝብ ተወካዮች የህዝብ አጀንዳዎችን እንዲያወጡና ምላሽ እንዲሰጣቸው ድጋፍ ማድረግ ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሴቶች ማህበር ፤ ከኤች አይ ቪ ሻይረሱ ጋር የሚኖሩ ወገኖችንና አካል ጉዳተኛ፣የወጣቶች ማህበር አባላት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ሴቶች የምክር ቤት አባላት ደፍረው ሀሳባቸውን እንዲገልፁና ለህዝብ ጥቅም እየሞገቱ የአቅም ግንባታ ስራ መሰራቱን የገለፁት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ከዚህ ቀደም ለሴቶች የተሰጡ ብድሮችን በማስመለስ የብድር ተጠቃሚ ላልሆኑት ሌሎች ወገኖችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በዕለቱ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የብየነ መንግስታት ትብብር አስተዳደር ባለሙያ አቶ አበበ ካሴ ደግሞ ለከተማዋ ልማት ድርሻቸውን እየተወጡ ለሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር 28 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አሉ ያሉት ባለሙያዋ በከተማዋ ከ281 ቢሊየን 847 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ እያዋሉ መሆኑን ደግሞ የመምሪያው የእቅድድ ዝግጅት ባለሙያ ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ገልፀዋል።

በከተማዋ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በጤና ፣በስርዓተ ምግብ ፣ የተማሪዎች የመማሪያ ክፍል ግንባታና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣በተፈጥሮ ሃብት ስራዎች፣በከተማ ግብር፣ በስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች፣ በንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ግንባታ ፤በተፈጥሮ አደጋ ለተጋለጡ የህብረተስብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ ላይ ትኩረት አድርገው እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ደግሞ በከተማዋ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት መሆናቸውን ተናግረዋል።

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቷች በከተማዋ እያከኗቸው ለሚገኙ የልማት ስራዎች ውጤታማነት የከተማ አስተዳደሩ ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መንስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የነዋሪዎቹ ትንፋሽ ሆነው እየሰሩ ነው ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ የከተማውን ነዋሪዎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት እያደረጉት ያለውን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የፋሲል ክፍለ ከተማ 1 ኛ ሩብ አመት 2018 የፓርቲና የመንግስት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ አቅጣጫ ውይይት ተከናወነ።በመድረኩ የፋሲል ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ...
25/10/2025

የፋሲል ክፍለ ከተማ 1 ኛ ሩብ አመት 2018 የፓርቲና የመንግስት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ አቅጣጫ ውይይት ተከናወነ።

በመድረኩ የፋሲል ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው ጀንበር ጨምሮ የክፍለ ከተማና የቀበሌ አመራሮች የተቋማት ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።

በፋሲል ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለባቸው ጀንበር በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ስራዎች በዝግጅት ምዕራፍና ሌሎች በርካታ የፓርቲና የመንግስት ተግባራት እንደተከናወኑ የገለፁ ሲሆን በጥንካሬና በድክመት በመለየትና የፈፃሚ አካላትን አቅም በማጎልበት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በአፈፃፀም ላይ ተመስርቶ እውቅና በመስጠት ማበረታታት አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የተቋማት የፈፀም አቅማቸውን በማጎልበት ሴኬታማ እንዲሆኑ መደገፍና ተግባራትን በቅንጅት መምራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ለላቀ ድል የተጀመረውን ንቅናቄ ለማጠናከርና በተቋማት መነቃቃት ለመፍጠር የሚያስችል የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የውስጠ ፓርቲና መደበኛ የመንግስት ተግባራት ምዘና በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኑ የልየታ ስራ በመስራት መመዘን እንደተቻለ አብራርተዋል።

የፋሲል ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊና ፓርቲ ጽ/ቤት ተወካይ ሀላፊ ወ/ሮ አስካል ተገኘ የበጀት ዓመት የተግባር አፈፃፀም ጅማሮ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም ትምህርት በመውሰድ ተቋማትና ፣ቀበሌዎች አደረጃጀቶች ለበለጠ ውጤት በቀሪ 3 ሩብ ዓመታት እንዲተጉ፤በቀበሌና በተቋማት እንዲሁም አደረጃጀቶች መካከል ያለውን የውድድር መንፈስ ለማጎልበት፤ በውስጠ ፓርቲም ሆነ በመደበኛ የመንግስት ተግባራት የበለጠ ትኩረት የሚሹ ተልዕኮዎችን ለይቶ እንዲፈፅሙ ለማስቻል ዓላማ ያደረገ መርሀ ግብር እንደሆነ ገልፀዋል።

በውስጠ ፓርቲ ተግባራት በሁሉም ቀበሌዎች 20 ህብረቶና 133 ቤተሰብ የለ ሲሆን ከምዘና መመሪያው አኳያ የመንግስት 70% ፣ ፓርቲ 30% ተደምሮ በጣም ከፍተኛ 95% በላይ ፣ ከፍተኛ ከ85 %በላይ – 95% ፣ መካከለኛ ከ65% በላይ – 85% ፣ ዝቅተኛ ከ50% – 65% እና በጣም ዝቅተኛ ከ50% በታች እንደሆነ በግልፅ ተቀምጧል፡፡በዚህ መሰረት ሁሉም ቀበሌዎችና ተቋማት ያሉበትን ደረጃ በመለየት የተሻለ አፈፃፀም ያለቸውን አጠናክሮ በማስቀጠል የውጤት ጉድለት ያለባቸውን በመለየት ፈጥኖ ማረምና ማስተካከል እንደሚገባ ገልፀዋል።

የፋሲል ክፍለ ከተማ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ም/ ሀላፊ አቶ ታደሰ ፈረደ የተቋማት የመፈፀም አቅምን በማጠናከር በበጀት ዓመቱ በአንደኛ ሩብ ዓመት በርካታ ስራዎችን ማከናወን የተቻለበትን አግባብ በማንሳት በተጀመረው አግባብ አጠናክሮ በማስቀጠል ደንብና መመሪያዎችን ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን በማጎልበት በፓርቲ የአሰራር ሥርዓት ላይ የተገነባ ተቋምና አባላት መገንባትና የፓርቲውን የመሪነት ሚና በማሳደግ ሁለተናዊ ብልፅግናን እውን እንዲሆን መትጋት አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን የፓርቲ አደረጃጀቶችና አባላት ወጥና ተቋማዊ አሰራር ጠብቆ የተቀራረበ የተልዕኮ አፈፃፀም ውጤት ላይ ማድረስ እንደሚገባ ገልፀዋል።

የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን አሁን ካለው የበለጠ በማዘመንና ክብልሹ አሰራር በፀዳ ተገልጋይን በማርካት በበጀት ዓመቱ የተቀመጠውን እቅድ በሙሉ አቅም በመፈፀም ማሳካት እንደሚገባ የገለፁ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈፃፀም የነበራቸውን የእውቅና ሽልማት በማበርከት በስኬት ተከናውኗል።

ራዕይ መጋራት፣ እምነትን ማጽናትበእምነት ላይ የተመሠረተው ትብብርና ኅብረት ወደ ኃይል ተቀይሮ ወደ ግቡ እንዲደርስ፣ የሚመራበትና የሚጋራው ራዕይ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ማኅበረሰብ በጋራ የሚስ...
25/10/2025

ራዕይ መጋራት፣ እምነትን ማጽናት

በእምነት ላይ የተመሠረተው ትብብርና ኅብረት ወደ ኃይል ተቀይሮ ወደ ግቡ እንዲደርስ፣ የሚመራበትና የሚጋራው ራዕይ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ማኅበረሰብ በጋራ የሚስማማበት ብሎም አስፈላጊውን ዋጋ የሚከፍልለትና የሚጓጓለት ብሔራዊ ራዕይ ሊኖረው ይገባል።

ያለ ራዕይ የሚወጠን ዕቅድና ተግባር መድረሻ የሌለው ግብ እንደማለት ነው:: በኮምፓስ የሚመራ መርከብ ከወደቡ እንደሚደርስ፤ በራዕይ የሚመራ ተግባርም ዓለምን ይቀይራል።

እንደ ፋና መንገድ ከመምራቱ በላይ፣ የግለሰቦችን ጉጉት በአንድነት በማስተሣሠር የጋራ ዕሴት እንዲኖረው ያደርጋል። ልዩ ልዩ አካላትን ወደ ጋራ ግብ ይወስዳቸዋል፤ አብዛኞቹ ወሳኝ የሆኑ ሽግግሮች የማይሳኩት በተሳትፎ እጥረትና ግልጽ ሆኖ የተቀመጠ ራዕይ ስለሌላቸው ነው፡፡

ከዓለም እጅግ ፈጣን ተለዋዋጭነት ጋር ለመጓዝ ዘመኑን የዋጀ ራዕይ መሰነቅ ግዴታ ነው።

"የጤና አገልግሎት ጥራት እና ፍታዊነትን ለማሻሻል ወቅቱ በሚጠይቀው የአሰራር ስርዓት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል"- ሲስተር ክሽን ወልዴ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ለጎንደር ...
25/10/2025

"የጤና አገልግሎት ጥራት እና ፍታዊነትን ለማሻሻል ወቅቱ በሚጠይቀው የአሰራር ስርዓት ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል"- ሲስተር ክሽን ወልዴ

የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ለጎንደር ቀጠና የጤና ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማነቆዎች በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል የሚያስችል የአገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻያ የአሰራር ስርዓት ትግበራ ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በጎንደር ከተማ እየሰጠ ነው።

በስልጠና መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሲስተር ክሽን ወልዴ፥ በባለፉት ዓመታት ፍትሃዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለማስፉፉት በጤና መሰረተ ልማት፣ በሰው ሀይል፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በበጀት አቅርቦት በተሰራው ከፍተኛ ስራ መሻሻሎች መታየታቸውን አንስተዋል።

ቢሆንም ግን ቀልጣፋና ተደራሽ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የአሰራር ስርዓቱ አለመሻሻሉ ማነቆ ሆኖ እንደቆየ ጠቁመዋል።

በመሆኑም የጤና አግልግሎት የአሰራር ስርዓቱ ማሻሻያ የተገልጋዮችን አገልግሎት አሰጣጥ ግልጽነትትንና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ እንዲሁም የሆስፒታሎችንና ጤና ጣቢያዎችን ጤና የእድገት ደረጃ በሚያሻሽል ሁኔታ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የደንበኞች ምክር ቤትን በማቋቋም ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሚተገበረው የማሻሻያ የአሰራር ስርዓት ጠንካራ የሆነ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ለመገንባትና ወቅቱ የሚጠይቀውን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለመዘርጋትና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉ ያግዛል ነው ያሉት።

በመሆኑም የጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ማነቆዎችን የመፍታት ሂደትን ትኩረት ሰጥቶ መተግበር እንደሚያስፈልግና የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ለሚሰጠው ስልጠና፣ ትግበራና ውጤታማነት ቁርጠኛ ሆኖ ወደ ስራ ማስገባት ተገቢነት አለው ብለዋል።

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ወ/ሮ ደብሬ የኋላ በበኩላቸው በጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና የተገልጋዮችን እርካታ ለመጨመር ተገቢውን የአገልግሎት ማሻሻያ መተግበር እንዳለበት ተናግረዋል። ለዚህም ህዝቡን ባለቤት በማድረግ ተገቢውን እገዛ እናደርጋለን ብለዋል።

በጤና አገልግሎት የአሰራር ስርዓት ማሻሻያ ላይ የሚሰጠው ስልጠና የጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ ማነቆዎችን በመፍታት ጥራት ያለውና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልጸው ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀና ተገቢ እንደሆነ አንስተዋል።

በዚህም የደንበኞች ምክር ቤት መቋቋሙ በተገልጋዮች እና በአገልጋዮች መካከል የሚፈጠሩ ልዩነቶችን የሚቀርፍ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ይህ ስልጠና በጎንደር ከተማ እንዲሰጥ ላመቻቹ ለፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እና ለክልሉ ጤና ቢሮ ምስጋና አቅርበው ሰልጣኞች በቆይታቸው እዬተዋበች ያለችውን ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማን ተዘዋውረው እንዲጎበኙ ጋብዘዋል።

በስልጠናው ላይ የጎንደር ቀጠና የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ባለሙያዎችና አመራሮች፣ የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

‎በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ በማዕከል የነዋሪዎች ምዝገባ የንቅናቄ መርሐግብር በሶስት የከተማ ቀበሌዎች ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎‎"የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ...
25/10/2025

‎በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ በማዕከል የነዋሪዎች ምዝገባ የንቅናቄ መርሐግብር በሶስት የከተማ ቀበሌዎች ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎"የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ” ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ እያንዳንዱ ህብረተሰብ ተጠቃሚ ሊሆን እንደሚገባ እና ፋይዳ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ፣ በአገልግሎት ሰጭ እና ተቀባይ መካከል በሚኖር ግንኙነት ላይ እምነትን ለማዳበር፣ የነዋሪዎችን ሁለንተናዊ ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እና የፍትህ ስርዓቱን ለማጠንከር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ተገልጿል፡፡

‎ዲጅታል መታወቂያ ሀገር በቀል ሪፎርም ከተደረጉት ተግባራቶች አንዱ ሲሆን ፋይዳ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ዘር፣ ቀለም፣ ብሔርና ሐይማኖት ሳይለይ ወጥ በሆነ መንገድ እየተከናወነ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከሚያግዙ ኢኒሼቲቮች የፋይዳ ብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ድርሻው የላቀ መሆኑን ተጠቁሟል።

‎የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ጠቀሜታው የጎላ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ መታወቂያውን መያዝ እንዳለበት እና ሁሉም የክፍለ ከተማዋ ነዋሪዎች በተዘጋጁት ማዕከላት የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ እንዲያወጡ ጥሪ የተላለፈ ሲሆን የንቅናቄ መርሐግብሩ በቀጣይ ቀናት በተለያዩ ቀበሌዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የንቅናቄ ምዝገባ በአራቱም ንዑሳን ቀበሌዎች እየተከናወነ ይገኛል።ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ መሠረት የተደራጀ መ...
25/10/2025

በአራዳ ክፍለ ከተማ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የንቅናቄ ምዝገባ በአራቱም ንዑሳን ቀበሌዎች እየተከናወነ ይገኛል።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ መሠረት የተደራጀ መሠረታዊ የመታወቂያ ስርዓት ሲሆን ማዕከላዊ የመረጃ መሰብሰቢያ ቋትን በማደራጀት የሚሰጡ አገልግሎቶች የተናበቡ እና በጠንካራ የባዮሜቲሪክ መረጃ ላይ መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው።

በማዕከላዊነት የተደራጀ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት አገልግሎት አሰጣጥን የሚያዘምን፣ የዲጂታል ስርዓትቶችን የሚያናብብ፣ ማጭበርበርን የሚቀንስ፣ የመንግስትን ሀብት ከብክነት የሚከላከል ነው።

በጎንደር ከተማ ሀገራዊ የፋይዳ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዘመቻ እየተካሔደ ነው።በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅዳሜና እሁድ ልዩ የፋይዳ መታወቂያ ፕሮግራም ምዝገባ ዘመቻ እንዲደረግ ከመንግስት በወረ...
25/10/2025

በጎንደር ከተማ ሀገራዊ የፋይዳ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዘመቻ እየተካሔደ ነው።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ቅዳሜና እሁድ ልዩ የፋይዳ መታወቂያ ፕሮግራም ምዝገባ ዘመቻ እንዲደረግ ከመንግስት በወረደው አቅጣጫ መሰረት በጎንደር ከተማ ባሉ 6 ክፍለ ከተሞች በ21 ማዕከላት የምዝገባ ዘመቻው እየተከናወነ መሆኑን የጎንደር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምትኩ አንዳርጌ ገልጸዋል ።

የከተማው ነዋሪ በእነዚህ ቀናት የምዘገባ ዘመቻው የሚቀጥል መሆኑን አውቀው ምዝገባ እንዲመዘገቡ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

25/10/2025

ጎንደር ስትገለጥ!
የኢትዮጵያዊነት ህብር ማሳያ - በስሟ ልክ እንደ አዲስ እየተሰራች ያለችው ጥንታዊቷ ጎንደር!

ባለፉት ሶስት ወራት ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞብል ክ/ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ገለጸ።በዞብል ክ/ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ...
25/10/2025

ባለፉት ሶስት ወራት ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የዞብል ክ/ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ገለጸ።

በዞብል ክ/ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ አጋር አካላት በተገኙበት ተደርጓል።

የ2018 በጀት ዓመት አንደኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም በዞብል ክ/ከተማ ገቢዎች ፅ/ቤት ሀላፊ በአቶ ገብሩ አዘነ ቀርቧል።

በሪፖርቱ እንዳቀረቡት የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት የገቢ ግብር ለመሰብሰብ ከተያዘው እቅድ አኳያ አሁን የተሰበሰበው ሲታይ ቀሪ ስራዎች እንዳሉብን ማሳያ ነው ብለዋል አክለውም ሲናገሩ በፅ/ቤታቸው የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጊዜ ሳይሰጥ በመፍታት ደንበኞችን ለማርካት እየሰሩ እንደሆነም ገልፀዋል።

የገቢ ግብር ለመሰብሰብ የአጋር አካላት ድርሻ ከፍ ያለ እንደሆነ በማብራራት እስካሁን ከክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቲ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮችና በጎ ፈቃደኞች ላደረጉት ትብብር በማመስገን በቀጣይም በተለይ ከተማናመሰረተልማት፣ህንፃ ሹም፣አካባቢ ጥበቃ እና ደንብ ማስከበር ጋር በቅንጅት በመስራት እቅዳችን በአጭር ጊዜ ማሳካት ይኖርብናል ብለዋል።

የገቢ ግብርን በወቅቱ መክፈል የሰለጠነ ህዝብ መገለጫ ነው እንዲሁም ፅ/ቤቱ ገቢን አንድ ቀንን እንደአምስት ቀን በመጠቀም በትኩረት በመሰብሰብ በከተማችን የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የበኩላችሁን መውጣት ይኖርባችኋል ያሉት ደግሞ መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የዞብል ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ደሞዝ ሰማኝ ናቸው።

በመጨረሻም ለአጋር ፅ/ቤቶች እና ተጠሪ ፅ/ቤቶች የቀጣይ ወር የገቢ እቅድ ርክክብ በማድረግ መድረኩ ተጠናቋል።

Address

Ethiopia
Gondar
62ዐዐ

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar City Prosperity Party /GPP/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share