09/09/2022
የኛ የጦር ግንባር የያዝነውን ሀገራዊ የገቢ ዕቅድ ማሸነፍ ነው!
ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ (የገቢዎች ሚኒስትር)
ነሐሴ 26፣ 2014 (ገቢዎች ሚኒስቴር)
ከዋናው መስሪያ ቤት አመራርና ሰራተኞች ጋር ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ከተናገሩት
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እንዳሉት ሀገራችን በብዙ ውጥረቶች ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ጊዜ በመንግስትና በህዝብ የተሰጠንን ታላቅ አደራ በብቃት መወጣት ከሁሉም አመራርና ሰራተኛ ይጠበቃል፡፡
ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ጉዳይ ስራዎችን በመግባባትና በመልካም የስራ ግንኙነት መምራት ነው ያሉት ሚኒስትሯ ለ3ኛ ጊዜ የተቃጣብንን ጥቃት ለመከላከል መላው ሰራተኛና አመራር ከመንግስት ጎን እንዲቆም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ተቋሙ መንግስት ለሚሰራቸው ሰፋፊ የልማት ስራዎች ዋነኛ የፋይናንስ ምንጭ እንደመሆኑ የገቢ ዕቅዱን ለማሳካት ሰፊ ሰራ እንደሚጠበቅ የጠቆሙ ሲሆን በዋነኛነትም ከመጥፎ እሳቤና ውዥንብሮች በመውጣት እንደዜጋ በጋራ ልንቆም ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡