30/05/2023
በምዕራብ በለሳ ወረዳ "ፈተናወችን ወደ መልካም ዕድል በመቀየር ህዝባችን እናሻግራለን" በሚል መሪ ቃል ለሁለት ተከታታይ ቀን ሲካሄድ የቆየው ኮንፈረስ ተጠናቀቀ!!! የለውጡ ምዕራፍ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በሀገራችን ፣በክልላችን፣በዞናችንና በወረዳችን ብዙ ውጤታማ ድሎችን የተጎናፀፍን መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው በዚህም በወረዳችን አስተማማኝ ሰላምና ደንነት ለማምጣት ፣ በግብርና ባልተለመደ የበጋ መስኖ ስንዴ አብዮት ፣ለውጡን በተገቢው ምንገድ ማስቀጠል፣ፕሮጀክቶችን ማስጀመርና ማስጨረስ፣የደባሪ መስኖ ካናል፣የአ/ተራራ መስኖ ካናል፣የአይሰግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዋና ዋናወቹ ናቸው የአማራ ህዝብ የወሰንና ማንነት ጥያቄወች ከ30ዓመት በኋላ በህጋዊ መንገድ ምላሽ የሚያገኝበት ዕድል መፈጠሩና የክልላችን ህዝብ ለዘመናት ጥያቄ የሆነውን የወልቃይት፣ጠገዴ፣የማንነትና የወሰን ጥያቄ በህጋዊ ጥያቄው እንዲመለስ እየሰራ መሆኑና እንዲሁም ለውጡ እንዳይቀለበስ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ተብሎ በኮንፈረሱ መግባባት ላይ ተደርሶ የለውጡን ጉዞ በማፋጠን ህዝባችን ወደ ላቀ ብልፅግና ለማሻገር በመረዳዳትና በቅንጅት ለመስራት ለተሳለጠ ጉዟችን እንቅፋት የሚሆኑ መሰናክሎችን ለማስወገድ ባለ5 የአቋም መግለጫ ነጥቦች አውጥቷል። 1ኛ ,በወረዳችን እየተከሰተ ያለውን የእርስ -በእርስ ግድያ ፣ጥይት ተኩስ፣ህገ ወጥ መሳሪያ ዝውውርና ስርቆትን ለማስቀረት ህዝቡን ያሳተፈ ትግል ፣የመፍትሔ አቅጣጫወች ላይ ጥልቀት ያለው ውይይት በማካሄድ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ወንድማማችነትንና እህትማማችነትን ለማፅናት ቃል እንገባለን!!! 2ኛ, በማንኛውም የሀገራችን አካባቢወች የሚስተዋሉ ግጭቶችን በሰላማዊ አማራጮች ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት እየገለፅን ሌሎች ሰላም ወዳድ ሀይሎች ሁሉ በማንኛውንም አይነት ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ብቻ የመፍታት አማራጭ እንዲከተሉ ጥሪያችን እናቀርባለን!!! 3ኛ ,ፈተናወችን ዕንደ መልካም እድል በመውሰድ ህዝባችን አበክሮ የሚፈልጋቸውን እውነተኛ ሰላም ፣የዴሞክራሲና የልማት ፍላጎት እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ዳር እንዲደርስ መላ የምዕ/በ/ወረዳና የቀበሌ አመራሮች ሌት ተቀን ለመስራትና ሁሉንም አይነት ዋጋ ለመክፈል ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን!!! 4ኛ ,ችግሮችን ይፈቱልናል፣ያስተዳድሩኛል ብሎ በምርጫ ድምፅ ለሰጠን ለወረዳችን ህዝብ እኛ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች ሙሉ አቅማችን ተጠቅመን ለህዝባችን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቃል እንገባለን!!!! 5ኛ ,የምዕራብ በለሳ ወረዳ ኮንፈረስ ተሳታፊወች እንደወሰነው የችግሮቻችን መውጫ መንገዶች የአመራርና አባላት አንድነት መፍጠር፣ከህዝባችን ጋር መተማመን መፍጠር ፣ሀይል የማሰባሰብና የሀገር አንድነት በመፍጠር ፅንፈኝነትን የሚታገል ስልት በመንደፍ ሰላምና ልማትን ቅድሚያ በመስጠት የመንግስትን የመፈፀም አቅም በማጎልበት ህዝባችን ለማሻገር ቃል እንገባለን!!! ግንቦት22/2015 ዓ.ም አርባያ