29/05/2026
በዳንሻ ከተማ አስተዳደር የሚሊሻ 30ኛው ዓመት የምስረታ ክብረ በአል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ ።
ዳንሻ ፡ግንቦት 21/2018 ዓ/ም በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ ከተማ አስተዳደር የሚሊሻ 30ኛው ዓመት የምስረታ ክብረ በአል በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል ።
የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አብድልዋህብ ማሙ ሚሊሻ ማለት ከህዝብ ለህዝብ የወጣ፤ ሁሌም ከህዝብ እና መንግስት ጎን በመሆን ለህልውናችን መሰረት የሆነ፤
የህዝብ አንድነትን በመጠበቅ ለሀገር ክብር የቆመና ቆርጦ የሚሰራ ሀይል ነው ብለዋል ።
ከንቲባው አክለውም የሚሊሻ ሀይል የሀገራችንን ሆነ የክልላችንን ህዝቦች ህገመግስታዊ መብቶችን በማስከበር ሰላምና ደህንነቱን በመጠበቅ፤
እንዲሁም በውስጣችን ተሰግስጎ የሚገኘው የፅንፈኛው ሀይሎች ጋር ትልቅ መስዋዕት በመክፈል ሀገራዊ ተጋድሎውን እያበረከተ ይገኛል ብለዋል ።
በአማራ ክልል ሚሊሻ መምሪያ የዘመቻ ኃላፊ አቶ ይታገስ አምባቸው የሚሊሻ የ30ኛ አመት የምስረታ በአልን ስናከብር አለማው ሚሊሻ የሰላማችን መሰረት የአድነታችን ደጀን የሆነ እና የሀገራችንን ታሪክ በደምና አጥንቱ የፃፈልን ድንቅ የህዝብ ልጅ መሆኑን ለወዳጆቻችን የምናሳይበት ነው ብለዋል ።
አቶ ይታገስ አክለውም ምንዘጋጀው ለሀገራችን የጭንቅ ቀን ደጀን እና ዘብ ለመሆን እንዲሁም ለሚሰነዝሩብን ጥቃት ለመመለስ ብቻ ሳይሆን ጠላት ሊደፍራት ሲያስብ ስሙ ቀድሞ በህሊናው ሊታወሰው የሚገባው ሀይል ለመመስረት ግድ ነው ብለዋል።
እንዲሁም ኮምሽነር ጋሻው መልካሙ በበኩላቸው የሚሊሻ ሀይላችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ላለፈችበት ውጣ ውረድ እና ሉአላዊነቷ ያበረከተው አስተዋፆ ትልቅ እንደሆነ አስተው ፤
በፊት ከጥንት ነጭ ለባሽ፣ሰላም አስከባሪ እንዲሁም አሁን ላይ ሚሊሻ የሚል ስያሜ ተሰጥቶት በህግ እና በደምብ እየተመራ እስካለበት ድረስ ብዙ ፈተናዎችን አልፎ በጀግንነት ዛሬ ላይ መድረሱ ለፈተናዎች አይበገሬነቱን ማሳያ ነው ብለዋል።
በዕለቱ ስለ ሚሊሻ ታሪካዊ አመጣጥ ጅማሮ እስከ አሁናዊ ቁመናው በፅሁፍ ያቀረቡት የዳንሻ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ማሩ ሲሆኑ በአፍሪካ ጠንካራ እና የተደራጀ የሚሊሻ ሀይል ካላቸው ሀገራት ኢትዮጵያ ግምባር ቀደምት መሆኗን አንስተዋል ።
ሚሊሻችን በህግ እና በጠንካራ ወታደራዊ ስነምግባር የሚመራ የሀገራችንን ሉአላዊነት ለማስከበር ከመደበኛው ሀይላችን ጋር በመሆን ሰላሙን እያስጠበቀ እንደሚገኝ ገልፀው፤
የሚሊሻው ሚና አሰተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት ከመፍጠር እንዲሁም በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ጊዜ ከህዝብ እና መንግስት ጎን በመሆን የህዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል ብለዋል።
በመጨረሻም ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚልሻ አባላት የእውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር በማካሄድ በአሉ ተጠናቋል ።