አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ

አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት  የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ this website was created to show every activities that are working in our livestock sector at adagn ager chako district

የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በነጋዴ ባህር ቀበሌ በንብ ሃብት ልማት  ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።🤝ታህሳስ 21/2...
30/12/2025

የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ በነጋዴ ባህር ቀበሌ በንብ ሃብት ልማት ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።
🤝ታህሳስ 21/2018.ዓ.ም🤝
በ አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ የማር ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል የተጀመረው ዘመናዊ የንብ ቀፎ ሽግግር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በነጋዴ ባህር ቀበሌ አርሶ አደሮችን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለሚደረገው ሽግግር የኬንያ ሽግግር ቀፎ ለተጠቃሚ አ/አደሮች በመስራት እና ልምድ ልውውጥ በማሳደግ በማር ምርት ውጤታማ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙ ጽ/ቤቱ ገልፆልናል ።

የወረዳው የንብና ሃር ልማት ባለሙያ የሆነው አቶ ፀሃይነህ ባረከ በዚህ የኬንያ ሽግግር ቀፎ ስራ ለ 35 አ/አደሮች፣ ለ 3 የቀበሌ ባለሙያዎችና ለ 3 የወረዳ ባለሙያዎች በተግባር የተደገፈ ልምድ ስለ ተቀናጀ የንብ ሃብት ልማት ማሻሻያ ዘዴዎችና አያያዝ፣ እንዲሁም አ/አደሩ በአካባቢ በቀላሉ በሚያገኛቸዉ ቁሳቁሶች ስለ ሽግግር ቀፎ አሰራር ለተከታታይ 2 ቀን የአሰራር ልምድ ልውውጥ ተሰጥቷል፡፡

ታህሳስ 21/2018.ዓ.ም
ምንጭ- (የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት )

😭ዜና እረፍት:በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት ስር  የእንሰሳት እርባታ ባለሙያ የነበረው ወንድማችን አቶ ስጦታው አልቃድር አደም  በደረሰበት ድንገተኛ ህመም ምክንያ...
24/12/2025

😭ዜና እረፍት:
በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት ስር የእንሰሳት እርባታ ባለሙያ የነበረው ወንድማችን አቶ ስጦታው አልቃድር አደም በደረሰበት ድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚች አለም ተለይቷል።

አቶ ስጦታው አልቃድር አደም በእንሰሳት እርባታ መደብ ተመርቆ ወደ መከላከያ ተቋም በመግባት 4 ዓመት ሀገሩን አገልግሏል። የ '10' አለቃ ማእረግንም ተቀብሏል። ከመከላከያ ተቋም መልስ በተመረቀበት የእንሰሳት እርባታ መደብ ከ2005 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በጭልጋ ወረዳ እና በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ከ13 ዓመት በላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ማህበረሰቡን፣ ሀገሩን ለ17 ዓመታት ያህል በቅንነት እስከ ህይወተ እልፈቱ ድረስ ያገለገለ ወንድማችን ነበረ።

የቀብር ሥነሥርዓቱ ቤተሰቦቹ ባሉበት በጭልጋ ወረዳ የተፈፀመ ሲሆን ለቤተሰቡ፣ ለስራ ባልደረቦቹ እና ለወዳጅ ጓደኞቹ መፅናናትን እየተመኘን ነፍሱን በጀነት ያኖርልን ዘንድ ፈጣሪን እንለምናለን😭😭

Condolences,RIP😭😭

"የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት"

ቀን:15-04-2018 ዓ/ም

18/11/2025
🤝Blood groups in animals
18/11/2025

🤝Blood groups in animals

18/11/2025
🐮💥 የከብቶች የብረት በሽታ / ትራውማቲክ ሬቲኩሎፔሪቶናይትስ (TRP) 💥🐮የከብቶች የብረት በሽታ (Traumatic Reticuloperitonitis)፡የብረት በሽታ (Hardware disease...
14/11/2025

🐮💥 የከብቶች የብረት በሽታ / ትራውማቲክ ሬቲኩሎፔሪቶናይትስ (TRP) 💥🐮

የከብቶች የብረት በሽታ (Traumatic Reticuloperitonitis)፡

የብረት በሽታ (Hardware disease) በከብቶች በተለይም በወተት እና በስጋ ከብት እርባታ ውስጥ ከሚታዩት የተለመዱ እና ሊከላከሉ ከሚችሉ የጤና ችግሮች አንዱ ነው። የሚከሰተው ከብቶች ከምግብ ወይም ከደረቅ ሳር ጋር የተቀላቀሉ ስለታም የሆኑ የብረት ነገሮችን እንደ ምስማር፣ ሽቦ ወይም የብረት ቁርጥራጮች በአጋጣሚ ሲውጡ ነው።

ዝርዝሩን እንመልከት 👇

🧩 የብረት በሽታ (Hardware Disease) ምንድን ነው?

የብረት በሽታ (ትራውማቲክ ሬቲኩሎፔሪቶናይተስ ተብሎም ይጠራል) ላም ስለታም የውጭ አካል (እንደ ሽቦ ቁራጭ ወይም ምስማር) ስትውጥ የሚፈጠር ነው። የብረት ነገር በሬቲኩለም (ከላም ሆድ ክፍሎች አንዱ) ውስጥ ይቀመጣል እና የሆዱን ግድግዳ በመበሳት ኢንፌክሽን ሊያስከትል አልፎ ተርፎም እንደ ልብ ወይም ጉበት ያሉ በአቅራቢያ ያሉ አካላትን ሊወጋ ይችላል።

⚠️ መንስኤዎች

በምስማር፣ በሽቦ ወይም በቆሻሻ ብረት የተበከለ ድርቆሽ ወይም ሳይሌጅ መመገብ።

ግንባታ በተካሄደባቸው ቦታዎች ወይም በተበላሹ አጥሮች አጠገብ የግጦሽ መስክ መጠቀም።

በመኖ ማከማቻ ስፍራዎች ዙሪያ ማሽነሪዎችን መጠቀም፣ ይህም አነስተኛ የብረት ብክለትን ያስከትላል።

🔍 ቀደምት ምልክቶች እና ምልክቶች

ገበሬዎች የሚከተሉትን ሊያስተውሉ ይችላሉ፦

🐄 የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም ሙሉ በሙሉ መጥፋት

🐄 የወተት ምርት መቀነስ

🐄 ጀርባን መጎንበስ እና ለመንቀሳቀስ መቸገር (ህመም)

🐄 ማቃተት ወይም ማልቀስ፣ በተለይም ሲነሱ ወይም ሲተኙ

🐄 ትኩሳት እና ደብዘዝ ማለት

🐄 የሆድ ዕቃ እንቅስቃሴ መቀነስ

🐄 የክርን አጥንቶችን ወደ ውጭ አዙሮ መቆም (የህመም አቋም)

ብረቱ የበለጠ ወግቶ የልብ ከረጢቱን (ፔሪካርዲየም) የሚነካ ከሆነ የሚከተሉትን ሊያዩ ይችላሉ፦

💧 ከደረት በታች እብጠት

💓 የመተንፈስ ችግር

💧 ፈሳሽ መከማቸት (ትራውማቲክ ፔሪካርዳይተስ በመባል ይታወቃል)

🩺 ምርመራ

አንድ የእንስሳት ሐኪም የሚከተሉትን ሊጠቀም ይችላል፦

🔹 አካላዊ ምርመራ (ህመም መፈለግ፣ የሆድ ድምጾችን ማዳመጥ)

🔹 የብረት መመርመሪያ (Metal detector) ወይም ማግኔቲክ መጠይቅ (Magnetic probe)

🔹 ኤክስሬይ ወይም አልትራሳውንድ (የብረት ነገር የት እንዳለ ለማወቅ)

💊 ሕክምና

ሕክምናው እንደ ደረጃው ይወሰናል፦ ✅ ቀደምት ደረጃዎች:

ብረቱን ለመሳብ እና ለመያዝ ማግኔት በአፍ መስጠት።

ኢንፌክሽን እና እብጠትን ለመቆጣጠር አንቲባዮቲኮች።

እረፍት እና ደጋፊ እንክብካቤ።

🚨 ከባድ ጉዳዮች:

የብረት ነገር በቀዶ ጥገና መወገድ (ሩመኖቶሚ)።

ለሞት የሚዳርጉ ችግሮችን ለመከላከል የእንስሳት ሐኪም ትኩረት በጣም አስፈላጊ ነው።

🛡️ መከላከል ከሕክምና ይበልጣል

🧲 የመኖ ማግኔቶች – መኖ ከብቶቹ ከመድረሱ በፊት ብረትን ለመያዝ በማሽነሪዎች ላይ ማግኔቶችን ማስቀመጥ።

🐄 የከብት ማግኔቶች – ጉዳትን ለመከላከል እያንዳንዱ ላም በወጣትነቷ ጊዜ የሆድ ማግኔት በአፏ መውሰድ።

🚜 የንጹህ መኖ ስፍራዎች – የግጦሽ መስኮችን፣ ሳይሌጅን እና መኖ ገንዳዎችን ከብረት ነገሮች ነጻ ማድረግ።

🏗️ የአጥር እና የህንጻ ምርመራ – አካባቢዎችን በመደበኛነት ለብረት ቆሻሻ መፈተሽ።

❗ የብረት በሽታ ላምን ሊገድል ይችላል?

አዎ 😢 — ካልታከመ ኢንፌክሽንን፣ የልብ ጉዳትን እና ሞትን ሊያስከትል ይችላል። ቀደም ብሎ ማወቅ እና መከላከል ህይወትን❗ የብረት በሽታ ላምን ሊገድል ይችላል?
አዎ 😢 — ካልታከመ ኢንፌክሽንን፣ የልብ ጉዳትን እና ሞትን ሊያስከትል ይችላል። ቀደም ብሎ ማወቅ እና መከላከል ህይወትን እና ገንዘብን ይቆጥባል።
🌾 ለገበሬዎች የሚቀርብ ጥሪ
👨‍🌾 ጊዜው እስኪያልፍ ድረስ አይጠብቁ!
✅ በጊዜ ለከብትዎ ማግኔት ያስገቡ።
✅ የመኖ ቦታዎችን በመደበኛነት ይመርምሩ።
✅ ህመም፣ የወተት መቀነስ ወይም የምግብ ፍላጎት ማጣት ካዩ ወዲያውኑ የእንስሳት ሐኪምዎን ያነጋግሩ።
የናይል መኖና እህሎች አቅርቦት 🌾 “ጥራት የሚረጋገጥበት” 💚 ጥራት ያለው መኖ በማቅረብ እና ገበሬዎችን ለጤናማ ከብት ማስተማር!

12/11/2025
ከክረምት መውጣት ወቅት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ የእንሰሳት በሽታዎችን ለመከላከል የቅድመ መከላከል ክትባት እየተሰጠ መሆኑን  የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳትና ዓሳ ሀብት ጽ/...
12/11/2025

ከክረምት መውጣት ወቅት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ የእንሰሳት በሽታዎችን ለመከላከል የቅድመ መከላከል ክትባት እየተሰጠ መሆኑን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳትና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት አስታወቀ ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ከክረምት መውጣት ወቅት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ የእንስሳት በሽታዎች ማለትም የእብድ ውሻ በሽታ ( RabiesVaccine) የቅድመ መከላከልና ክትባት በነጋዴ ባህር ከተማና በወረዳችን ባሉ በሁሉም ቀበሌዎች እየተሰጠ መሆኑን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳትና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት ኃላፊ ደ/ርጌታቸው ራራ ገልፀዋል።

በሽታው ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍና ገዳይ በሽታ በመሆኑ በአንድ ወር ውስጥ የክትባት ዘመቻውን በማከናወን በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ለሁሉም እንሰሳት አገልግሎት እንዲያገኙ ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

አክለውም ኃላፊው ህብረተሰቡ ይህን በሽታ ተገንዝቦ እንስሳት ያለው በሁሉም ቦታዎች የክትባት ዘመቻ አገልግሎት ስለሚሰጥ ቅድመ ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበው በዛሬው እለት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የክትባት አገልግሎት 3500 በላይ በወረዳው ላሉ ውሾች የክትባት አገልግሎት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ገልፀዋል ።

ህዳር 03/2018 ዓ.ም
@ Adagn Ager Chako Werda Communication Office

Address

Gondar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ እንሰሳት ሃብት ልማት ፅ/ቤት የፌስ-ቡክ ድህረ-ገፅ:

Share