Gondar City Education Department/ጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • Gondar City Education Department/ጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ

Gondar City Education Department/ጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ It's all about Gondar, Amhara, Ethiopia Education. ስለ ጎንደር-አማራ-ኢትዮጲያ ትምህርት እናወራለን።
(3)

በአማራ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ከሰኔ 08-12/2018 ዓ.ም ይሰጣል።የ6ኛ ክፍል ፈተና➫ ሰኔ 8 እና 09/2018 ዓ.ም ይሰጣል።የ8ኛ ክፍል ፈተ...
02/06/2026

በአማራ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ከሰኔ 08-12/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የ6ኛ ክፍል ፈተና
➫ ሰኔ 8 እና 09/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና
➫ ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የሚሰጥባቸው ቀናት ይፋ ሆኑ።በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን ክልል አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠና...
02/06/2026

የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና የሚሰጥባቸው ቀናት ይፋ ሆኑ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን ክልል አቀፍ የ6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ይፋ ሆናል፡፡

በዚህ መሰረት የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 8 እና 9 /2018 ዓ.ም እንዲሁም የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

27/05/2026

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ኃላፊው እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል-አድሀ/አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

በአሉ የሰላም፥ የፍቅር፥ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆን ከልብ ተመኝተዋል።

በአማራ ክልል 100 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እንደሚወስዱ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ። የፊታችን ሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በስኬት ...
25/05/2026

በአማራ ክልል 100 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እንደሚወስዱ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የፊታችን ሰኔ ወር መገባደጃ ላይ የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በስኬት ለማስኬድ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኀላፊ እየሩስ መንግሥቱ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቢሮው ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው ብለዋል።

በዚህ የትምህርት ዘመን ላይም 99 ሺህ 897 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ነው ያሉት።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን ተማሪዎችን በበይነ መረብ የመፈተን ዕቅድ በክልሉ ለመተግበር ርብርብ እየተደረገ ስለመኾኑም አስረድተዋል።

በክልሉ የሚገኙ 539 ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚያስፈትኑም ምክትል ኀላፊዋ ገልጸዋል።

ከእነዚህ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 315ቱ በበይነ መረብ አማካኝነት ለተማሪዎቻቸው ፈተናውን ይሰጣሉም ብለዋል። በበይነ መረብ ተማሪዎቻቸውን ከሚያስፈትኑት መካከልም 215 ትምህርት ቤቶች በክልሉ በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚያስፈትኑ ይኾናል ነው ያሉት።

ቀሪ 100 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ማዕከላት እና በአይ ሲ ቲ ማዕከላት እንደሚያስፈትኑ ነው የተናገሩት።

ቀሪዎቹ ትምህረት ቤቶች ደግሞ በተለመደው የወረቀት ፈተና አሰጣጥ ሂደት ፈተናውን እንደሚያካሂዱ ገልጸዋል።

በበይነ መረብ አማካኝነት ተማሪዎችን በስኬት ለማስፈተን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ስለመኾኑም ምክትል ኀላፊዋ አንስተዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎቹ ቴክኖሎጅውን እንዲለማመዱት የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል ነው ያሉት።

የበይነ መረብ ፈተና ሥርዓት ኩረጃን በማስቀረት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል።


#ትምህርትለትውልድ

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የ...
22/05/2026

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ለመውሰድ የተመዘገባቹ በአስቸኳይ የማረጋገጥ ሥራ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

የማረጋገጥ ሥራው (Self Verification) ከ2-3 ደቂቃዎች ብቻ የሚወስድና የተፈታኞችን የትምህርት ሰነዶች ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ለማስተሳሰር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

ተከታዩን ሊንክ (https://verify.ethernet.edu.et/) ከተጫኑ በኋላ Remedial Examination የሚለውን ይጫኑ፣ Start Verification የሚለውን በመጫንና የሚያስፈልገውን በመሙላት ያረጋግጡ።

የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጥባቸው የጊዜ መርሐግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገበዚህም፦➫ የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም ➫ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ...
21/05/2026

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጥባቸው የጊዜ መርሐግብር ላይ ማሻሻያ ተደረገ

በዚህም፦
➫ የሪሚዲያል ፈተና ከግንቦት 27/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም

➫ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የሚሰጡ መሆኑ ተገልጿል።

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በቀሪ ቀናት በልዩ ስልት በተቀናጀ አግባብ ለማብቃት በተዘጋጀ ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት...
20/05/2026

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በቀሪ ቀናት በልዩ ስልት በተቀናጀ አግባብ ለማብቃት በተዘጋጀ ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ በሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ተግባራት ግምገማ የመምሪያ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ነጋሽ፣ የመምሪያው ማኔጅመንት እና ባለሙያዎች፣ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የመምህራን እና የተማሪ ወላጅ ማህበራት አመራሮች በተገኙበት ተካሄደ።

የግምገማ መድረኩን ቁልፍ መልዕክት በማስተላለፍ ያስጀመሩት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ነጋሽ የትምህርት ተቋማት ትውልድን የማነጽ ተልዕኮን ለማሳካት ትኩረት የሚያደርጉ እንደመሆናቸው ዘመኑን የዋጀ ትምህርት ለመስጠት የተቋማቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮችም የመማር ማስተማር ስርዓትን በማሳደግ የተማሪ ውጤትና ስነምግባር መሻሻል ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ስንታየሁ አክለውም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ ልዩ፣ የተቀናጀ እና ስልታዊ የሆነ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው በቀሩት ጥቂት ቀናት ተማሪዎችን በዕውቀት፣ በቴክኒክ እና በሥነ-ልቦና በማዘጋጀት ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

በመድረኩ ያለፉት ወራት ሪፖርት በተመረጡ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና በመምሪያ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ በአቶ አዱኛ ቸኮል እንዲሁም የማጠናከሪያ ትምህርት ስትራቴጂ በስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪ በአቶ በላይነህ አባት ቀርቧል።

በግምገማ መድረኩ በቀረቡ ሪፖርቶች እንደተገለጸው ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና በአግባቡ ዝግጁ መሆን እንዲችሉ እየተሰጡ የሚገኙ የማጠናከሪያ ትምህርትና የስነ ልቦና ስልጠና ተጠናክሮ እንደቀጠለ የተገለጸ ሲሆን እስከፈተናው ዋዜማ ተማሪዎችን በቀለምና በስነ ልቦና ዝግጁ የማድረግ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆን ወላጆችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ተቀይሰው እየተሰሩ የሚገኙ ስለመሆኑ ተጠቅሷል።

Arsenal are officially Premier League champions 🏆አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒየን ሆነ🏆
19/05/2026

Arsenal are officially Premier League champions 🏆
አርሰናል የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒየን ሆነ🏆

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በ667 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በ97 ዩ...
19/05/2026

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በ667 የፈተና ማዕከላት ይሰጣል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2018 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን በ97 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ570 የክልል ማዕከላት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፋና ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ በተፈጥሮ ሳይንስ 306,964 እንዲሁም በማኅበራዊ ሳይንስ 257,255 በድምሩ 564,219 ተማሪዎች መመዝገባቸውን ገልፀዋል፡፡

ፈተናውን በሙሉ አቅም በበይነ መረብ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎች በወረቀት የሚፈተኑ እንደሚኖሩም ጠቁመዋል።

ፈተናው በስድስት ዙር (ማኅበራዊ ሳይንስ በሦስት ዙር እና ተፈጥሮ ሳይንስ በሦስት ዙር) ሚሰጥ መሆኑ ገልፀዋል፡፡

የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡በመሆኑም...
17/05/2026

የቅድመ-ምረቃ ትምህርት የመውጫ ፈተና በድጋሚ በግል ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ የምትገኙ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ግንቦት 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሔዳል፡፡

በመሆኑም የመመዝገቢያ ሊንኩን https://exam.ethernet.edu.et በመጠቀምና የተዘረዘሩ መስፈርቶችን በማሟላት ከግንቦት 08-12/2018 ዓ.ም መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በቴሌብር በኩል መክፈል የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ የሚያስፈልግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል፡፡

Address

Gondar

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 11:30
13:30 - 17:30

Telephone

+251581110123

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gondar City Education Department/ጎንደር ከተማ ትምህርት መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share