የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን Gondar City Administration Roads Authority

  • Home
  • Ethiopia
  • Gondar
  • የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን Gondar City Administration Roads Authority

የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን Gondar City Administration Roads Authority ይህ ገጽ ትክክለኛው የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የፌስቡክ ገጽ ነው።

በጎንደር ጃንተከል ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገናኛ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጭቃ ሰፈር  የኮብል ንጣፍ  ስራ ተጀመረ።በክፍለ ከተማችን በዋነኛነት ለረጅም ጊዜያት ሊፈቱ ያልቻሉ የህብረተሰባችን ጥያቄዎ...
14/06/2023

በጎንደር ጃንተከል ክፍለ ከተማ አስተዳደር በመገናኛ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጭቃ ሰፈር የኮብል ንጣፍ ስራ ተጀመረ።

በክፍለ ከተማችን በዋነኛነት ለረጅም ጊዜያት ሊፈቱ ያልቻሉ የህብረተሰባችን ጥያቄዎች መካከል አንዱ የሆነውን የመሰረተ ልማት ስራዎች በተለይም የመንገድ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ታሰቦ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በአፍጠኛ የኮብል መንገዶችን በመገንባት የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች መሰረታዊ ጥያቄ የሆነውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ታስቦ እየተሰራ ይገኛል።

ይህ የኮል መንገድ የጃንተከል ክፍለ ከተማ የመገናኛ ቀበሌ ነዋሪዎች በዋነኝነት ከሚያነሳቸውን የልማት ጥያቄዎች መካከል አንዱ በመሆኑ ይህንን ጥያቄ መፍት መቻል የህዝባችን አገልጋይ መሆናችንን በተግባር የምናሳይበት አንዱ ስራችን ነዉ ።

የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ዘላቂ የልማት ግቦችን ከማሳካት ባሻገር ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ድህነትን ለማስወገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር በማራኪ ክፍለ ከተማ  በብላጅግ ዳብርቃ የገጠር ቀበሌ በክቡር ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ የተመራ የልዑካን ቡድን የብላጅግ ዳብርቃ የገጠር ቀበሌ የመሬት ጠረጋ ያለበ...
09/06/2023

በጎንደር ከተማ አስተዳደር በማራኪ ክፍለ ከተማ በብላጅግ ዳብርቃ የገጠር ቀበሌ በክቡር ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ የተመራ የልዑካን ቡድን የብላጅግ ዳብርቃ የገጠር ቀበሌ የመሬት ጠረጋ ያለበት ሁኔታ ተጎበኘ።

በፕሮግራሙ ላይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አንዱአለም ሙሉ፤ የጎንደር ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሀላፊ ዲያቆን ቢኒያም ፀጋየ፤ የማራኪ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋሲል አብዩ፤ የማራኪ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ሳምሶን ገብሩ እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል።

መሰረተ ልማት ዘላቂ የልማት ግቦችን ከማሳካት ባሻገር ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ድህነትን ለማስወገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ተብሏል።

መንግስት የህብረተሰብን ችግር ብቻውን ይፈታል ተብሎ ከመጠበቅ፤ ህብረተሰብ በነቃ ተሳትፎ የመሰረተ ልማት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ ለክፍለከተማው ሁለንተናዊ ዕድገት የህብረተሰብ ተሳትፎ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እጅግ የጎላ እንደሆነ ይታወቃል።

ህብረተሰብን መሠረት ያደረገ ልማት ዘላቂነት ይኖረዋል፤ የክፍለ ከተማው ልማት በሚፈለገው ልክ እንዲከናወን የህብረተሰቡ ተሳትፎ በማጠናከር ማስቀጠል ይገባል።

በተያዘው በጀት ዓመት የክፍለ ከተማው መሠረተ ልማት ኮሚቴ ተወያይቶ ባሳለፈው ውሳኔ በማራኪ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎች ከሶስተኛ ወገን በማፅዳት ስራው ተከናዉኖ የመሠረተ ልማት ግንቦታ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የመሠረተ ልማት ሥራውን ለማከናወን ከጎንደር ከተማ አስተዳደርና ከዓለም ባንክ በጀት የተመደበ ሲሆን 10% ያህሉ ደግሞ ከአካባቢው ማኅበረሰብ የተሰበሰበ ነው፤ በዚህ ፕሮጀክት ስራም የነዋሪዎችን ጥያቄ ከመመለስ በተጨማሪ ለበርካታ አመታት በህብረተሰቡ ዘንድ ሲነሳ የነበረው የመሰረተ ልማት ጥያቄ መፈታት ተችሏል።

እነዚህ የመሠረተ ልማት ስራዎች ቀበሌውን ብሎም ክፍለከተማውን ውብ የሚያደርጉ ከመሆናቸውም በላይ ለሰዎች ለኑሮ የሚመርጧት አካባቢን ከምፍጠር አንፃር አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው።

ከህብረተሰብም በጉልበት የሚያስፈልጉ ስራዎችንም ደግሞ በጉልበት መስራት ያስፈልጋል። የእኛ የድርሻችን ሰንወጣ እናንተም የድርሻችሁን እንዲወጡ ተገልጿል።

በመጨረሻም የአካባቢው ማህብረሰብ ለ40 አመታት የህብረተሰቡ ጥያቄ የነበረው የመሬት ጠረጋ ጥራትን ባረጋገጠ መልኩ መሰረተ ልማት ዘላቂ የልማት ግቦችን ከማሳካት ባሻገር ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዝገብ ድህነትን ለማስወገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል ስለሆነም መንግስት ከጎናችን መቆሙን አረጋግጠናል ብለዋል።

ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ ' ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻመድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰውገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤የአድዋ ድ...
26/02/2023

ምኒሊክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ '
ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ፤

ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻለብቻ፤

የአድዋ ሥላሴን ጠላት አረከሰው
ገበየሁ በሞቴ ግባና ቀድሰው፤

የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኅተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው፡፡ የመላው ዓለም ተፈጥሮአዊ ግብር እና ሰብአዊ ክብር የታደሠው፤ በእውነትና በፍትህ ህልውናና ምልዓት ላይ የተሰካ ትልቅ ጥርስ የተነቀለው … በአድዋ የታላቅ ህዝቦች ታላቅ ድል ነው፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ስንሄድ 1066 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ታላቁ ጦርነት የተደረገበትና ታላቁ ድል የተገኘበት ሥፍራ አድዋ ከተማና የከተማው ግድም ገመገሞች ይገኛሉ፡፡ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ለጦርነቱ መነሻ የሆነው ውል የተፈፀመው በዚሁ ዘመን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 468 ኪሎ ሜትር ርቀት ግድም ከውጫሌ ከተማ ግርጌ ከአምባሰል ተራራ ሥር ወሎ ውስጥ ንጉሥ ይስማ እየተባለ በሚጠራ ሥፍራ ነው፡፡

ሸልዶ ተራራ ወይም (ሶሎዳ ተራራ) በመሠኘት የሚታወቁት እነዚህ ገመገሞችና ተራራማ ሥፍራዎች ዋነኞቹ የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡

በመቶ ሺህ የሚሠላ የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ከአንድ ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የአውሮጳ ቅኝ ገዢ ወራሪዎችን ድባቅ ከመታና ረግጦ ካስወጣ በኋላ ከምሽቱ አራት ሰዓት ግድም (የካቲት 23 ቀን) እንዳማርያም ላይ ተሰባስቦ በአንድ እግሩ ቆሞ ድሉን ለሰጠው አምላክ ምሥጋና አቅርቧል፡፡

አባት ሆይ፤ ንቀውን የመጡ የአገራችንን ድንበርና ልዕልና የደፈሩ የአውሮጳ ኮሎኒያሊስት ወራሪዎችን ድል እንድናደርግ ስለረዳኸን እናመሰግንሃለን።

ሃያ ዘጠኝ ሺህ ፈረሰኞችን ጨምሮ ከመቶ ሺህ እስከ መቶ ሃያ ሺህ የሚገመት አንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በባዶ እግሩ የተጓዘ የኢትዮጵያ የገበሬ ሠራዊት በወታደራዊ አካዳሚ የሠለጠነውን የአውሮጳ ወራሪ ጦር የካቲት 23 ማለዳ አሥራ አንድ ሰዓት ግድም ገጥሞ ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ማሸነፉን አረጋግጧል ይለናል የታሪክ ተመራማሪው ጆርጅ በርክሌይ የአድዋ ጦርነትና ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ በተሰኘና ዳኘው ኃይለሥላሴ ወደ አማርኛ በተረጐሙት መጽሐፉ ላይ፡፡

የኢትዮጵያ ገበሬ ሠራዊት ፈረሱ ላይ ሆኖ የጋሻውን እምብርት መሬት ላይ እያጠቀሰ ጐራዴውን አየር ውስጥ እየቀዘፈ በተቆጣና በቆረጠ መንፈስ በጀግንነት ተዋግቷል፡፡

ጦርነቱ በተጀመረ ከአምስት ሰዓት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሃምሣ ስድስቱም የኢጣሊያ መድፎች ሙሉ ለሙሉ ተማርከዋል፤ የቅኝ ገዢውን ወራሪ ሠራዊት ከመሩት ጀኔራሎች ጄኔራል አልቤርቶኒ ሲማረክ የሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጄኔራል ባራቴሪ ከጥቂት አጃቢዎቹና በሽንፈት ከተበታተኑ የኢጣሊያ ወታደሮች ጋር ሸሽቷል፡፡

በዚህ ድብልቅልቅ ያለ ውጊያ ከሃምሣ ስድስቱ የኢጣሊያ መድፎች በተጨማሪ ብዙ ሺህ ቀላልና ከባድ መትረየሶች እንዲሁም የነፍስ ወከፍ ጠመንጃዎች በአሥር ሺሆችና በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ መሰል ጥይቶቻቸው ጋር ተማርከዋል፡፡

በማግስቱ የካቲት 24 ቀን 1888 ዓ.ም ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ የኢጣሊያ ምርኮኞች በምኒሊክ ድንኳን ፊት ሲያልፉ የኢትዮጵያ ጀግና የገበሬ ሠራዊት እየፎከረ እየሸለለ አሳልፉዋቸዋል።

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
06/01/2023

እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

ጎንደር ብልኮ አርበኞች አደባባይ መሠረታዊ የአስፓልት ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።ብልኮ አርበኞች አደባባይ የተጀመረው ጥገና ለተከታታይ ቀናት በመስራት አሁን የአስፋልት ማንጠ...
26/12/2022

ጎንደር ብልኮ አርበኞች አደባባይ መሠረታዊ የአስፓልት ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።

ብልኮ አርበኞች አደባባይ የተጀመረው ጥገና ለተከታታይ ቀናት በመስራት አሁን የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ እየተጠናቀቀ ይገኛል። በዚህም ህብረተሰቡ ላሳየው ድጋፍ በእጅጉ የሚመስገን ነው በቀጣይም የህብረተሰቡ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

በቀጣይም ፒያሳ፣ አራዳ እና ኮሌጅ ማራኪ ያሉ መንገዶች ጥገና የሚደረግላቸው ይሆናል።

በ30 ሚሊየን ብር የአስፓልት መንገድ ጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ፡፡የከተማ አስተዳደሩ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዲያቆን ...
24/12/2022

በ30 ሚሊየን ብር የአስፓልት መንገድ ጥገና ስራ እያከናወነ መሆኑን የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ዲያቆን ቢኒያም ፀጋዬ እንደገለፁት በከተማዋ በተመረጡ አካባቢዎች መሰረታዊ ሊባል የሚችል የአስፓልት መንገዶች የጥገና ስራ እየተከናወነ ነው፡፡

የአስፓልት መንገድ ጥገና ስራው የከተማ አስተዳደሩ በመደበው 30 ሚሊየን ብር እየተከናወነ ሲሆን ኢራ የቴክኒካል ድጋፍ እያደረገ በመሆኑ ገልፀዋል።

ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ አስመላሽ ዘሪሁን በሰጡት አስተያት እየተሰራ ያለው የአስፓልት ጥገና ስራ በጥራት እየተከናወነ ነው፡፡

ስራው በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተወል፡፡

ሌላው የአካባቢው ነዋሪ አቶ ታዬ መላኩ ድግሞ ካሁን ቀደም የስፓልት መንገዶች ጥገና በጥራት ይሰራ እንዳልነበር ጠቁመው በዚህ ዓመት እየተሰራ ያለው የአስፓልት ጥገና ስራ ደረጃውን የጠበቀ ነው፡፡

ለህብረተሰቡም አገልግሎቱ ካፍ ያለ ይሆናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከተማዋ የቱሪስት ከተማ በመሆንዋ ጥራት ያለው የአስፓልት ጥገና ስራዎች እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የመንገድ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ባለሙያ አቶ አብዮት ጥላሁን ደግሞ አስፓልቱ በመጠገኑ በተሸከርካሪዎችና በግለሰቦች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።

የመንገድ ደህንነት ለማረጋገጥም የራሱን ድርሻ ያበረክታል ብለዋል።

መረጃው የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

ጎንደር ብልኮ አርበኞች አደባባይ መሠረታዊ የአስፓልት ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።ብልኮ አርበኞች አደባባይ ላይ የተጀመረው ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል። በቀጣ...
24/12/2022

ጎንደር ብልኮ አርበኞች አደባባይ መሠረታዊ የአስፓልት ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።

ብልኮ አርበኞች አደባባይ ላይ የተጀመረው ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።

በቀጣይም አራዳ እና ኮሌጅ ማራኪ ያሉ መንገዶች ጥገና የሚደረግላቸው ይሆናል።

የጎንደር ከተማ መሠረታዊ የአስፓልት ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።ብልኮ አርበኞች አደባባይ ላይ የተጀመረው ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል። በቀጣይም አራዳ እና ኮ...
17/12/2022

የጎንደር ከተማ መሠረታዊ የአስፓልት ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል።

ብልኮ አርበኞች አደባባይ ላይ የተጀመረው ጥገና በፍጥነት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል። በቀጣይም አራዳ እና ኮሌጅ ማራኪ ያሉ መንገዶች ጥገና የሚደረግላቸው ይሆናል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከባጃጅ ተሽከርካሪዎች ጋር ተያይዞ  የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ከተማ አስተዳደሩ ከባጃጅ ጋር ተያይዞ ያገጠሙ ፣ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በ...
25/11/2022

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከባጃጅ ተሽከርካሪዎች ጋር ተያይዞ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከባጃጅ ጋር ተያይዞ ያገጠሙ ፣ እያጋጠሙ ያሉና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በጥናት እንዲለዩ አድርጓል።

በጥናቱም ቀላል የማይባሉ የአሰራር ግድፈቶች ስለመኖራቸው አረጋግጧል።

ከተማ አስተዳደሩ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ባጃጅ ወደ ከተማው እንዳይገባ ክልከላ ቢያደርግም የተለያዩ አካላት ቅንጅት ፈጥረው በሰሩት ኃላፊነት የጎደለው ተግባር በሽ የሚቆጠሩ የወረዳ ባጃጆች ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ ህጋዊ የከተማ ባጃጆች ክፉኛ እንዲጎዱ ማድረጋቸውን ጥናቱ አመላክቷል።

እነዚህንና ሌሎችንም ግኝቶች መሰረት በማድረግ ከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ ውሳኔዎችን ለመወሰን የተገደደ ሲሆን ወሳኔዎችን ተግባራዊ ለማድረግም የተለያዩ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።

ውሳኔውን ለማደናቀፍና የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣት የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የሚያጋጥሙ ከሆነም ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በሚያመች መንገድ ልዩ የምርመራ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጓል።
ውሳኔዎች

✔አዲስ ባጃጅ ወደ ከተማው ለማስገባት 70,000 (ሰባ ሽ ብር) ለከተማ አስተዳደሩ የገቢዎች ተቋም ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
✔የከተማ ፍቃድ ባይኖራቸውም የነዳጅ ድጎማውን እንዲጠቀሙ የተፈቀደላቸው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 50,000 (ሃምሳ ሽ ብር) ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
✔ከሰው እጅ ያለ ባጃጅ ወደ ከተማው በማስገባት የከተማ ፍቃድ ለማግኘት 100,000 (መቶ ሽ ብር) ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
✔ከጉሙሩክ በጨረታ አሸንፈው የከተማ ፍቃድ ለማግኘት ለሚመጡ ባጃጆች 100,000 (
ሽ ብር ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
✔ከኮ ድ ሁለት ወደ ኮድ አንድ ለመቀየር ለሚፈልጉ =30,000 (ሰላሳ ሽብር) ለገቢዎች ተቋም ስለመክፈላቸው መረጋገጥ አለበት፡፡
✔እስከ ህዳር 30 ባለው ቀነ-ገደብ ውስጥ የሚጠበቅበትን አሟልቶ የከተማ ፍቃድ ሳይኖረው ከተማው ላይ አገልግሎት ሲሰጥ የተገኘ ባጃጅ=30,000 ብር ተቀጥቶ ከከተማው እንዲወጣ የሚደረግ ሲሆን ተግባሩም ከህዳር 19 ቀን 2015 እስከ ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም ብቻ የሚፈፀም ይሆናል።

ተግባሩን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችም እንዲጠናቀቁ ተደርጓል።

ጎን በጎንም የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም በማሳጣትና ተግባሩን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ለማጣራት የሚያስችል ስራ ተሰርቷል።

የከተማ ፍቃድ ሳይኖራቸው አላቸው የሚል መረጃ በመስጠት ግለሰቦችን ላልተፈለገ ወጭ የዳረጉ አካላትን ለይቶና ከግለሰቦች የሚመጣን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ምርመራ የሚካሄድ ይሆናል።

ውሳኔው ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አስፈላጊውን እገዛ ከማድረግ ይልቅ ለማደናቀፍ የሚሞክሩና ያለከተማ አስተዳደሩ እውቅና በራሳቸው ስልጣን የወረዳ ባጃጅ አስገብተው በተገኙ አካላት ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃም ለመውሰድ የምንገደድ ይሆናል።

ህጋዊ ሆነው ሳለ ኮምፒዩተር ያልገባላቸው ካሉ በጥንቃቄና በጥልቀት በማጣራትና እውነታውን ፈልገን በማግኘት መፍትሄ የምንሰጥ ሲሆን የተሳሳተ መረጃ በመያዝ ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ ሰንዶችን ይዘን የምርመራ አካል የምናደርግ ይሆናል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር

በመንገድና ድሬኔጅ ዲዛይንና ክትትል በውጭ ተቋራጮች የሚያወጣውን ወጭ ለመቀነስለተቋሙ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ እየሰጠ መሆኑን የጎንደር መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ፡፡የባለስልጣኑ ዋና ስራ አ...
25/11/2022

በመንገድና ድሬኔጅ ዲዛይንና ክትትል በውጭ ተቋራጮች የሚያወጣውን ወጭ ለመቀነስለተቋሙ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ እየሰጠ መሆኑን የጎንደር መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዲያቆን ቢኒያም ፀጋዬ እንደገለፁት ተቋሙ የዲዛይን ቡድን ያለው ቢሆንም እስካሁን የመንገድና ድሬኔጅ ዲዛይንና ክትትል ስራዎች የሚከናወኑት በዘርፉ የልማት ድርጅቶ የሚሰጥ በመሆኑ ተቋሙ ላልተገባ ወጭ ተዳርጎ ቆየይቷል፡፡

ተቋሙ ለውጭ የልማት ድርጅቶች የሚያሰራውን ስራ በተቋሙ ሰራተኞች ቢያሰራ በዓመት ከ10 ሚሊየን ብር ከወጭ መታደግ ይቻላል ሲሉ ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡

ይህን ችግር በመረዳትም ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለተቋሙ ለባለሙያዎ ለአንድ ወር የሚሰጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑንተናግረዋል፡፡

የቋሙ የመንገድ ልማት ባለስልጣን ልማት አስተዳደር የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ጌትነት ቢሰጥ ደግሞ የተቋሙን ሰራዎች በተገቢው ለመወጣት ስልጠናው አቅም ይፈጥርልናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ተቋሙ በወር እስከ 450ሽ ብር ለልማት ድርጅቶች የሚከፈለውን ወጭ በተ ቀቋሙ ባለሙያዎች አቅም ለመፈፀም ያስችላል ብለዋል፡፡

ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የሲቪል ምህንድስና ክፍል የኢኒጅነረንግ ባለሙያ አቶ ወርቁ መላኩ ደግሞ የጎንደር የኒቨርስቲ ከመማር ማስተማር ፣ከምርምር ስራዎች ባሻገር በማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎች የከተማ አስተዳደሩን እያገዘ በመሆኑ ስልጠናውን መስጠት አስፈልጓል ብለዋል፡፡

ሰልጣጮች በስልጠናው በመንገድና ድሬኔጅ ዲዛይንና ክትትል ዘርፍ ተገቢውን ክህሎት ያዳብራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

ስልጠናው ዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ ሲሆን በፅንስ ሀሳበና በተግባር የታገዘ የመንገድና የድሬኔጅ ዲዛይንና ክትትል በተመለከተ ለዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

26/10/2022
ሰራዊታችን በየተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ የፈጸማቸውን ገድሎች  በሙሉ አንስቶ መጨረስ  አይቻልም፡፡ ሰራዊታችን ችግር የማይበግረው፤ ፈተና ከኢትዮጵያዊነቱ ፈቀቅ የማያደርገው ከ...
25/10/2022

ሰራዊታችን በየተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ግዳጆች ላይ የፈጸማቸውን ገድሎች በሙሉ አንስቶ መጨረስ አይቻልም፡፡ ሰራዊታችን ችግር የማይበግረው፤ ፈተና ከኢትዮጵያዊነቱ ፈቀቅ የማያደርገው ከህዝብ ወጥቶ ለህዝብ የሚኖር ዕንቁ የሀገር ሀብት ነው፡፡

ጠላት ሀገርን ሊወር ከሩቅ ሲመጣ ከህዝብ ቀድሞ ግንባሩን ለጥይት የሚሰጥ፣ ለሀገር ኖሮ፣ ለህይወቱ ሳይሳሳ ግንባር ተሰልፎ፣ ለሀገር ተዋግቶ፣ ለሀገር ቆስሎ ለሀገር የሚሞት የኢትዮጵያዊነት መሰረት ነው፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት፡፡

በሰላሙም ጊዜ ህዝብን መስሎ የሚኖር፣ ህዝብ ሲቸገር ቆሞ ማየት የማይችል እንስፍስፍ ልብ ያለው፣ ዜጎች በደም እጦት ምክንያት ህይወታቸው እንዳያልፍ ዳር ድንበሩን እየጠበቀ ደሙን ሳይሰስት የሚሰጥ የህዝባዊነት ምልክት ነው፡፡

ሰራዊታችን በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያልቻሉ ድልድዮችንና መንገዶችን ጉልበቱን፣ ገንዘቡንና ዕውቀቱን አጣምሮ ለህዝብ ጥቅም የሚያውል ከራሱ በላይ ለህዝብ የሚኖር የመልካም ስብዕና ባለቤት ነው፡፡

Address

Gondar

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጎንደር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን Gondar City Administration Roads Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share