23/12/2025
ለፃልቄ ሁለገብ መሠረታዊ ህብረት ሥራ ማህበር አባላት በሙሉ፤
ማህበራችን ለሣውላ ከተማ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ በዋጋ ንረት ምክንያት የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ችግር ለማረጋጋት ሰፊ ሥራ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በቀጣይ ከልኳንዳ ሥራ በተጨማሪ የፍጆታ ዕቃዎችን (Palm oil የምግብ ዘይት፣ ስኳር፣ ዱቄት፣ ፓስታ ማካሮኒ እና ሩዝ) ምርቶችን ለአባላትና ለዞኑ ማህበረሰብ ወደ ማቅረብ እንደሚገባ በሥራ አመራር ኮሚቴ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በመሆኑም ለዚሁ ሥራ ዋና የሀብት ምንጫችን የማህበሩ አባላት ስለሆኑ ዝቅተኛ የዕጣ ግዥ የፈፀማችሁ አባላት እስከ ጥር 30/2018 ዓ.ም ድረስ የዕጣ መጠናችሁን ወደ አምስት(5) እና ወደ አስር (10) ዕጣ እንድታሳድጉ እንጠይቃለን፡፡
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም
ሣውላ፣