የጎባ ደሎ በር ሰፈር ልጆችiiiiii

የጎባ ደሎ በር ሰፈር ልጆችiiiiii የጎባን ታሪክ እንዘክርበታለን ገጠመኝ እናወራበታለን ትንግ?

~በአሜሪካ ሀገር በሚገኝ አንድ ዩኒቨርስቲ በሞባይል ሱሰኝነት ዙሪያ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በአለም ስማርት ስልክን ከሚጠቀሙ 1.5 ቢሊዮን ሰዎች፦◽️ አንድ ሰው በየቀኑ በአማካይ 110...
18/05/2025

~በአሜሪካ ሀገር በሚገኝ አንድ ዩኒቨርስቲ በሞባይል ሱሰኝነት ዙሪያ ያደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በአለም ስማርት ስልክን ከሚጠቀሙ 1.5 ቢሊዮን ሰዎች፦

◽️ አንድ ሰው በየቀኑ በአማካይ 110 ጊዜ ስልኩን ይከፍታል።

◽️ 40% የሞባይል ተጠቃሚዎች ሽንት ቤት ውስጥ ስልካቸውን ይጠቀማሉ።

◽️ 50% የሞባይል ተጠቃሚዎች በሌሊት ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ስልካቸውን ያለ ምንም ምክንያት Check ያረጋሉ።

◽️ 65% የሚሆኑት የሞባይል ተጠቃሚዎች እየበሉ ስልካቸውን ይጎሮጉራሉ።

◽️ 55% የሚሆኑት የሞባይል ተጠቃሚዎች ስልካቸውን እየተጠቀሙ በተመሳሳይ ሰዓት ቴሌቪዥን ይመለከታሉ።

◽️ 30% የሞባይል ተጠቃሚዎች በስራ ሰአት እና በስብሰባ ወቅት ስልካቸውን ይጎረጉራሉ።

◽️ 38% የሚሆኑት መንገድ ላይ ሲጓዙ ስልካቸውን እየነካኩ ነው።

◽️ 7% የሚሆኑት በስልክዎቻቸው ላይ ብዙ ጊዜ በማሳለፋቸው ምክንያት ሥራ እንዳጡ ይናገራሉ።

◽️ በመጨረሻም 60% የሚሆኑት የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች በእውነት የስልካቸው ሱሰኛ እንደሆኑ አምነዋል።
|

🔺እናንተስ ከተጠቀሱት መሀል በምን
ሱስ ነው የተያዛችሁት
👉source social Media

በአንድ ፓርክ ሺ ተፈጥሮ *************'አንድ ቦታ ብዙ ዓለም' በመባል ይታወቃል የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፡፡በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበባቸው ምክንያቶች አንዱ በአጭር ርቀ...
18/05/2025

በአንድ ፓርክ ሺ ተፈጥሮ
*************

'አንድ ቦታ ብዙ ዓለም' በመባል ይታወቃል የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፡፡

በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት ከተመዘገበባቸው ምክንያቶች አንዱ በአጭር ርቀት ውስጥ የተለያየ የመሬት ሥነ-ምህዳር እና የአየር ንብረት ባለቤት በመሆኑም ጭምር ነው፡፡

44 ለሚሆኑ ወንዞች መነሻ የሆነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተመሰረተው በ1962 ዓ.ም ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱም 1250 ኪ.ሜ ስኩዌር ነው፡፡

በውስጡ በርካ እፅዋቶችን፣የዱር እንስሳትን እና አዕዋፋትን አቅፎ የያዘው ፓርኩ፣ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ 177 የሚደርሱ እፅዋቶችን ይገኙበታል፡፡ በዚህ ስፍራ የሚገኙ እፅዋቶች የተለየ አስደናቂ አበቃቀል እንዳላቸውም ይነገራል፡፡

የተራራው ወታደር በመባል የሚታወቀው እፅዋት በዓለም ላይ ከሚገኝባቸው ጥቂት ስፍራዎች መካከል የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አንዱ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ የሆኑ 22 የሚደርሱ አጥቢ የዱር እንስሳቶች በፓርኩ የሚገኙ ሲሆን የደጋ አጋዘን፣ ቀይ ቀበሮ፣ ሚኒሊክ ቡሽ ባክ፣ የባሌ ጦጣ እና የመሳሰሉት በዚሁ ስፍራ ይገኛሉ፡፡

በመሬት ውስጥ ለውስጥ በመቆፈር ቤቱን የሚገነባው 'መሐንዲሱ' ተብሎ የሚጠራው የአይጥ ዝርያም በዚህ ስፍራ በብዛት ይገኛል፡፡

የባሌ ብሔራዊ ፓርክ በአንድ ፓርክ ሺ ተፈጥሮ የምንመለከትበት ስፍራ ከመሆኑም ባሻገር ለበርካታ ሰዎችም የመተዳደሪያ ምንጭ በመሆን ይታወቃል፡፡

ይህ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ተፈጥሮዎችን በውስጡ አቅፎ የያዘው የባሌ ተራሮች ከብዙ ሚሊዮን ዓመት በፊት በእሳተጎሞራ ምክንያት እንደተፈጠረ ይነገራል፡፡

ስዕል በቃኝ የሚያስብሉ Comments
15/05/2025

ስዕል በቃኝ የሚያስብሉ Comments

አንስታይን ያለ መነፅሩ ማንበብ ይቸግረዋል። አንድ ጊዜ ወደ ምግብ ቤት ገብቶ እንደተቀመጠ መነፅሩ እንዳልያዘ ይረዳል። በመሃል አስተናጋጁ የሚያነብበትን ሜኑ አምጥቶ የፈለገውን እንዲመርጥ ነገ...
11/05/2025

አንስታይን ያለ መነፅሩ ማንበብ ይቸግረዋል። አንድ ጊዜ ወደ ምግብ ቤት ገብቶ እንደተቀመጠ መነፅሩ እንዳልያዘ ይረዳል። በመሃል አስተናጋጁ የሚያነብበትን ሜኑ አምጥቶ የፈለገውን እንዲመርጥ ነገረው። አንስታይን ግን ለአስተናጋጁ መልሶ አንተ አንብብልኝ በማለት ይሰጠዋል። ይሄኔ አስተናጋጁ አንስታይን ላይ እየሳቀ “ይቅርታ ጌታዬ እኔም እንዳንተ መሀይም ነኝ!” 🤭 ............😱🙆አንዳንድ ሰው አድርግልኝ ሲልህ እሱ ማድረግ አቅቶት አደለም።

ውቢቷ ምድር ባሌ ጎባ...ሪራ...ደሎ
09/05/2025

ውቢቷ ምድር ባሌ ጎባ...ሪራ...ደሎ

 የነገሩ መጀመሪያ ቢራው ውስጥ የገባችው ትንኝ ጉዳይ ነው።አሜሪካኑ ቢራው ውስጥ ትንኝ ስትገባ አየ። እና ቢራውን ደፋው። (አሜሪካውያን አይቋጥሩም ለማለት ይመስላል)ይህችው ትንኝ አሁን ደግሞ...
04/05/2025



የነገሩ መጀመሪያ ቢራው ውስጥ የገባችው ትንኝ ጉዳይ ነው።

አሜሪካኑ ቢራው ውስጥ ትንኝ ስትገባ አየ። እና ቢራውን ደፋው። (አሜሪካውያን አይቋጥሩም ለማለት ይመስላል)

ይህችው ትንኝ አሁን ደግሞ እንግሊዛዊው ሰው የሚጠጣው ቢራ ውስጥ ገባች አሉ። ብር ላይ እጃቸውን ያዝ ያደርጋቸዋል ይባላል እና አንዲት ትንኝ ስለገባችበት ብርጭቆ ሙሉ ቢራ መድፋት አልፈለገም። እና ትንኟን አውጥቶ ጥሎ ቢራውን ጠጣው።

አሁን ደግሞ ትንኟ የገባችው ቻይናዊው ይጠጣ የነበረው ቢራ ውስጥ ነው። እና ልክ ስትገባ ሲያያት ምንም አላለም ትንኟን አውጥቶ በላትና ቢራውን ጠጣው።

ችግሩ የሚመጣው አሁን ነው ትንኟ የህንዳዊው የቢራ ብርጭቆ ውስጥ ገባች። ህንዳዊው ልክ ይህን እንዳየ ይህች ትንኝ ያለፓኪስታን አይዞሽ ባይነት እዚህ ውስጥ አትገባም ብለው ፀብ ፈጠረ በዚህ ምክንያትም የሁለቱ ሀገራት ወታደሮቻቸውን በተጠንቀቅ እንዲቆሙ ትእዛዝ ሰጡ። የሚል የፈረንጅ ቀልድ አለ።

አወዛጋቢ በሆነውና ሁለቱም በሚቆጣጠሩት የካሽሚር ግዛት ምክንያት የቆየ ፀብ ያላቸው ህንድና ፓኪስታን በተለይ ባለፉት አመታት በየሰበቡ ጦራቸውን ዝግጁ ያደርጉ ነበርና ያንን መሰረት አድርጎ የተነገረ የፈረንጅ ቀልድ ነው።

ወደ እውነቱ ስንመጣ ደግሞ ባለፈው ሳምንት ህንድ በምትቆጣጠረው የካሽሚር ግዛት ቱሪስቶች ከተገደሉ በኋላ በመሀከላቸው ያለው አለመግባባት ብሶ ካሁን አሁን ይፋ ወደሆነ ጦርነት እንዳይገቡ ተሰግቷል።

ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለመላው የአለም ህዝቦች።

በ1902 አንድ ፕሮፌሰር ተማሪውን"ይህችን ዓለም ወይም ዮኒቨርስ የፈጠራት ፈጣሪ መሆን አለመሆኑን ማን ነው የሚነግረን?" ሲል ጠይቆ ነበር።ተማሪውም "አዎ ይኽችን ምድር የፈጠራት ፈጣሪ ነው"...
04/05/2025

በ1902 አንድ ፕሮፌሰር ተማሪውን
"ይህችን ዓለም ወይም ዮኒቨርስ የፈጠራት ፈጣሪ መሆን አለመሆኑን ማን ነው የሚነግረን?" ሲል ጠይቆ ነበር።

ተማሪውም "አዎ ይኽችን ምድር የፈጠራት ፈጣሪ ነው" ሲል መልስ ሰጠ።
መልሶ መምህሩ ሌላ ጥያቄ አቀረበ፤ "መልካም ሲዖልንስ የፈጠረው ማነው?"።

ተማሪው ለአፍታ በዝምታ ማዕበል ተዋጠ፤ መልሶ ተማሪው አስተማሪውን ጠየቀ " ውድ መምህር እኔ ደግሞ መልሼ ልጠይቅዎት ፤ ቀዝቃዛ ነገር እዚህ ምድር ላይ አለ ብለው ያምናሉ ?"።

"ይሄማ ምን ያጠያይቃል የብርድ ስሜት መኖሩ አይታወቅህም ?!" ሲሉ መምህር መልስ ሰጡ።

ተማሪውም "መምህሬ ይቅርታ አድርጉልኝና ተሳስተዋል ፤ ቀዝቃዛ የሚባል ነገር የለም ፤ ብርድ ማለት የሙቀት እጥረት ነው ፤ ቅዝቃዜ ብሎ ነገር የለም "። ሲል ተማሪው ምላሽ ሰጠ።

በድጋሚ ተማሪው ጥያቄ ማቅረቡ አልቀረም "ለመሆኑ መምህር ጨለማ አለ ብለው ያምናሉ?"።

ፕሮፌሰርም "አዎ ጨለማ አለ" የሚል መልስ ሰጡ ።

ተማሪውም "ፕሮፌሰር በትልቁ ተሳስተዋል ፤ ጨለማ የሚባል ነገር የለም ፤ የብርሃን አለመኖር እንጂ፤
ሁልጊዜ የምንማረው ስለ ብርሃንና ስለ ሙቀት እንጂ ስለ ቅዝቃዜና ስለ ጨለማ አይደለም፤ ስለዚህም ሲዖል የለም። በመሰረቱ ሲዖል ማለት የፍቅር፣ የእምነት፣ በፈጣሪ የማመን እጥረት ማለት ነው" ብሎ ነበር ።

ያ ተማሪ እውቁ ሳይንቲስት አልበርት አነስታይን ነው ።
ፈላስፋው ነኝ

 #ባሏን  #የገደለው  #መርዝ ////ይነበብ////ከእለታት በአንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በሁለተኛ ዓመቷ ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።ይህች ቆንጆ ልጅም ...
27/04/2025

#ባሏን #የገደለው #መርዝ ////ይነበብ////

ከእለታት በአንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በሁለተኛ ዓመቷ ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።
ይህች ቆንጆ ልጅም ወደ እናቷ ቤት በመሄድ "እናቴ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው ነገሮች ሰልቺተውኛል፣ለእኔ አያስብልኝም፣ዞር ብሎ እንኳን አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት
ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል እፈልጋለሁ በአንድ በኩል ደግሞ ህግ ያስረኛል ብየ እፈራለሁ እና እባክሽ እርጅኝ?አለቻት።

እናቷም:-እሺ እረዳሻለሁ የእኔ ውድ ልጅ ግን መጀመሪያ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ አለቻት።

ልጅቷም:አንቺ ያልሽኝን ነገሮች በሙሉ እፈጽማለሁ አለች።
እናትየዋም:-ባልሽ ሞቶ አስከሬኑ ከቤት እስኪወጣ ድረስ ከዚህ በታች ያሉትን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሜያቸው አለች።

1.የገደለችው እርሶ ናት ብለው እንዳይጠረጥሩሽ ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ፍጠሪ።
2.ሁልጊዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ውብ ሁነሽ ታይ።
3.በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኝለት አበርችው።
4.ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ፣ብዙ ጊዜ አድማጭ ሁኚ በማክበር ታዘዥው።
5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ አንዲችም በለሽ ሳታስቀሪ እርሱን ለማስደሰት አውይው።
6.ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳያስብ የጭቅጭቅ ድምፅ ከአፍሽ እንዳይወጣ ሰላም እና የፍቅር ቃል ከአፍሽ ይውጣ እስክትገላገይው ድረስ ብቻ።

እናትዮዋ:-በድጋሚ ያልኩሽን ነገሮች ሳታዛንፊ ታደርጊለሽ አለቻት?
ልጅቷም እርሱ ሞቶ ይውጣልኝ እንጂ አንድም ሳላስቀር አደርገዋለሁ ብላ መለሰች።

እናትየዋም አንድ ብልቃጥ አውጥታ ይህን መርዝ ያዥውና ሁሌም ከሚበላው ምግብ ጋር እየጨመርሽ ስጭው መርዙም አመንምኖ ይገድለዋል።

ልጅቷም ደስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።

ልጅቷ:-ከአንድ ወር በኋላ ተመልሳ ወይ ጉድ ሰውየው ወሬውን ሳይሰማ አይቀርም መሰለኝ ድሮ አድርጎት የማያውቀውን "ማሬ፣ፍቅሬ፣ወለላዬ፣
ህይወቴ፣ንግስቴ፣በዓለም ላይ አንቺን የምታክል ሴት የለችም ይለኛል እኔ እንጂ ፀባዩ ልውጥውጥ ብሎብኛል።

እናትየዋም:-መርዙን እየሰጠሽው ነው አለቻት?ልጅቷም አይኗ እንባ እያቀረረ
አዎ ግን አሁን ፀባዩ ሸጋ፣አፍቃሪ ባል ኋኖል እና እንዲሞትብኝ አልፈልግም እባክሽ ማርከሻ መድሀኒት ፈልጊልኝ ፀፀቱ ሊገለኝ ነው እማዬ???

እናትየዋም:-ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው።ነገር ግን ቀስ በቀስ ፀባዩ መጥፎ ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ"ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣መታዘዝ ፣መንከባከብ ፣መታገስ
እና ውብ ሁነሽ ስትገኝ ባልሽን መቀየር ትችያለሽ።

አንቺ ያልሰጠሽውን ነገር እንዴት ከሌላ ሰው ትጠብቂያለሽ?ፍቅር ማለት ሰጥቷ መቀበል ነው።

አስተማሪ ሆኖ ካገኙት 👍

ስንሞት፣ ሁሉም  #ሀብታችን ባንክ ውስጥ ይቀመጣል... በሕይወት ስንኖር ግን፣ የምናወጣው በቂ ገንዘብ የለንም። በእውነቱ፣ እኛ ስናልፍ፣ ብዙ ገንዘብ ጥቅም ላይ ሳይውል ይቀራል።አንድ ቻይናዊ...
27/04/2025

ስንሞት፣ ሁሉም #ሀብታችን ባንክ ውስጥ ይቀመጣል... በሕይወት ስንኖር ግን፣ የምናወጣው በቂ ገንዘብ የለንም። በእውነቱ፣ እኛ ስናልፍ፣ ብዙ ገንዘብ ጥቅም ላይ ሳይውል ይቀራል።

አንድ ቻይናዊ የንግድ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ባለቤቱ፣ በባንክ 1.9 ቢሊዮን ዶላር ይዛ፣ የባሏን ሾፌር አገባች። ሾፌሩ እንዲህ አለ፦ “በህይወቴ ሙሉ፣ ለአለቃዬ እየሰራሁ መስሎኝ ነበር... አሁን ግን አለቃዬ ሁልጊዜ ለእኔ ይሰራ እንደነበር ገባኝ!!!”

#እውነታው በ #ህይወት ውስጥ፣ ብዙ #ሀብት ከማግኘት ይልቅ ረጅም ዕድሜ መኖር የበለጠ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ፣ ለጠንካራ እና ጤናማ አካል መጣር አለብን። ማን ለማን እንደሚሰራ በእርግጥ ምንም ለውጥ የለውም።

* በጣም ውድ በሆነ ስልክ ውስጥ፣ 70% የሚሆኑት ገፅታዎች (features) ጥቅም የላቸውም!
*ውድ በሆነ መኪና ውስጥ፣ 70% የሚሆነው ፍጥነት እና ተጨማሪ መገልገያዎች (gadgets) አላስፈላጊ ናቸው።
*ትልቅ መኖሪያ ቤት ካለዎት፣ 70% የሚሆነው ቦታ አብዛኛውን ጊዜ ጥቅም ላይ አይውልም።
*በቁምሳጥንዎ ውስጥ ያሉት ልብሶችስ? 70% የሚሆኑት በጭራሽ አይለበሱም!
*የህይወት ዘመን ልፋትዎ እና ገቢዎ ሁሉ... 70% የሚሆነው ለሌሎች ነው።
*ስለዚህ፣ 30%ችንን በአግባቡ መጠቀም እና ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ መሆን አለብን።

👉 ባይታመሙም እንኳ #የህክምና ምርመራ ያድርጉ።
👉 ባይጠማዎም እንኳ ብዙ ውሃ ይጠጡ።
👉 ከባድ ችግሮች ሲያጋጥሙዎትም እንኳ ነገሮችን የመተው ጥበብን ይማሩ።
👉 ትክክል ቢሆኑም እንኳ ለመስማማት ( #ለመደራደር ) ይሞክሩ።
👉 #ሀብታም እና #ኃያል ቢሆኑም እንኳ ትሁት ይሁኑ።
👉 ሀብታም ባይሆኑም እንኳ ባለዎት የመርካት ( #የመብቃቃት ) ልማድ ያዳብሩ።
👉 በጣም ስራ ቢበዛብዎትም እንኳ ሰውነትዎን እና አእምሮዎን ያንቀሳቅሱ (የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ)።
👉 ለሚያስቡላቸው ሰዎች ጊዜ ይስጡ።

ህይወት አጭር ናት... ሙሉ በሙሉ በመኖር ይደሰቱባት!!!

🔹 እግዚአብሔርን እና ቅዱሳትን የበለጠ ውደዱ!
🔹 ለመጸለይ እና የእግዚአብሔርን ቃል ለማንበብ ጊዜ ይውሰዱ!
🔹 ብዙ ውሃ ይጠጡ።
🔹 ምግብ፦

ቁርስን እንደ ንጉስ፣
ምሳን እንደ ልዑል፣
እራትን ደግሞ እንደ ድሃ ይመገቡ።

🔹 በ #ህይወት ውስጥ ሶስቱን ‘ኢ’ዎች ይከተሉ፦
ጉልበት (Energy)፣
መነቃቃት (Enthusiasm)፣
እና የሌሎችን ስሜት መረዳት (Empathy)።

🔹 ጥሩ ስፖርቶችን ይጫወቱ።
🔹 በ2017 ዓ.ም. (2025 G.C.) ብዙ መጽሐፍትን ያንብቡ።
🔹 በየቀኑ ቢያንስ ለ10 ደቂቃዎች በጸጥታ ይቀመጡ።
🔹 ለ 7 ሰዓታት ይተኙ።
🔹 በየቀኑ ለ10-30 ደቂቃዎች ይራመዱ እና ሲራመዱ... 😊 ፈገግ ይበሉ።
🔹 ነገሮችን አያካብዱ። ገደብዎን ያስታውሱ።
🔹 እራስዎን ከልክ በላይ በቁም ነገር አይውሰዱ። ማንም ሰው አያደርገውም።
🔹 ውድ ጉልበትዎን በሀሜት አያባክኑ።
🔹 ነቅተው ሳሉ የበለጠ አልሙ።
🔹 በሌሎች መቀናት ጊዜ ማባከን ነው። የሚያስፈልግዎት ሁሉ አስቀድመው አልዎት።
🔹 ያለፉ ችግሮችን ይርሱ። የትዳር አጋርዎን ያለፉ ስህተቶቻቸውን አያስታውሱ። የአሁኑን ደስታዎን ሊያበላሽ ይችላል።
🔹 ማንንም በመጥላት ለማባከን ህይወት በጣም አጭር ናት። ሌሎችን አይጥሉ።
🔹 የአሁኑን ጊዜዎን እንዳያበላሽ ካለፈው ጋር ሰላም ይፍጠሩ።
🔹 ከእርስዎ በስተቀር ማንም ለደስታዎ ተጠያቂ አይደለም።
🔹 የበለጠ ፈገግ ይበሉ እና ይሳቁ።
🔹 እያንዳንዱን ክርክር ማሸነፍ አያስፈልግዎትም፤ ላለመስማማት ይስማሙ።
🔹 ከቤተሰብዎ ጋር አዘውትረው ይገናኙ።
🔹 በየቀኑ ለሌሎች አንድ ጥሩ ነገር

"ዊሊያም ሼክስፒር"☞ "ሲዖል ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ዲያብሎሶች ያሉት እዚህ ምድር ላይ ነው፡፡"☞ "ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ ቅንና መልካም ስትሆን ደግሞ ከጭንቀትና ከጸጸት...
27/04/2025

"ዊሊያም ሼክስፒር"

☞ "ሲዖል ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ዲያብሎሶች ያሉት እዚህ ምድር ላይ ነው፡፡"
☞ "ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ ቅንና መልካም ስትሆን ደግሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።"
☞ "ለማንኛውም ሠው ጆሮህን ስጥ፤ ድምፅህን ግን ቀንስ፤ ሁሉንም ውደድ፤ ጥቂቶቹን እመን፤ ማንንም ግን አትበድል፡፡"
☞ "የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።"
☞ "ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን መቀየር አይችልም።"
☞ "የቀንን ውበት አይቶ ለማድነቅ የግድ ጨለማን መጠበቅ ያስፈልጋል።"
☞ "መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ቀንዲል ናት።"
☞ "ማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው።

አሞራው የህመም ስሜት ሲሰማው ወደ ጉንዳን ይሄዳል****Crow የሚባለው አሞራ የህምም ስሜት ሲሰማው የጉንዳን መንጋ አጠገብ ይሄድና ክንፉን ይዘረጋል ጉንዳኖች ጠላት መጣ ብለው ጥቃት ይፈጽሙ...
26/04/2025

አሞራው የህመም ስሜት ሲሰማው ወደ ጉንዳን ይሄዳል
****
Crow የሚባለው አሞራ የህምም ስሜት ሲሰማው የጉንዳን መንጋ አጠገብ ይሄድና ክንፉን ይዘረጋል ጉንዳኖች ጠላት መጣ ብለው ጥቃት ይፈጽሙበታል።

ይሄን የሚያደርግበት በቂ ምክንያት አለው።ጉንዳን ሲነክሰው ሰውነቱ ውስጥ ፎርሚክ አሲድ ይገባል ይሄ ንጥረ ነገር ደግሞ በሽታን በተፈጥሮ መንገድ ያክምበታል።ፎርሚክ አሲዱ አሞራው በሰውነቱ ውስጥ ያሉ እንደ ባክቴሪያ፣ፈንገስ፣ ትላትል፣.......ያስወግድበታል።
ተፈጥሮ ለሁሉም ፍጥረት ተመርምሮ የማያልቅ ጥበብ ሰጥቷል

ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመ...
26/04/2025

ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው። አንዱ አጠገቡ ላለው ጓደኛው እንዲህ አለው። "ቄሱ ቆንጆ ሚስት አለቻቸው። እንዋደዳለን። አሁን እሷ ጋ ልሄድ ነው። አንተ ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን በወሬ ያዝልኝ። ከመምጣትህ በፊት አስቀድመህ ደውልልኝ አደራ" አለው።

ጓደኛው ከቅዳሴ በኋላ ቄሱን አስቁሞ የባጥ የቆጡን ያወራላቸው ጀመር። ቄሱም በሰውዬው የተዘበራረቀ ንግግር ግራ ገባቸውና ምን እንደፈለገ በቁጣ ጠየቁት።

ሰውዬም የሃጢአተኝነት ስሜት ተሰማውና ዕውነቱን ነገራቸው "ይቅር ይበሉኝ አባቴ! ጓደኛዬ ከእርስዎ ሚስት ጋር ሊተኛ ሄዶ እኔ እርስዎን በወሬ እንድይዝሎት ነግሮኝ ነው" ብሎ እግራቸው ላይ ወደቀ።

ቄሱም ፈጥነው አነሱትና እንዲህ አሉት "አንተ ሞኝ! አሁኑኑ ወደ ሚስትህ ፈጥነህ ሂድ! እኔ ሚስቴ ከሞተች 5 ዓመት አልፏታል"....... !🙆‍♂️

ምን ልልክ ፈልጌ ነው ላጤነት ይለምልም 🖐

Address

Goba

Telephone

+251922327488

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጎባ ደሎ በር ሰፈር ልጆችiiiiii posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የጎባ ደሎ በር ሰፈር ልጆችiiiiii:

Share

Category