18/01/2023
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!- የኦፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደማ ኃይሌ
ከሁሉ አስቀድሜ ዉድ የኦፋ ወረዳ ማህበረሰብ በሙሉ በአንድነት ፣ በመተሳሰብ በጋራ ሆነን በደስታና በጨዋታ እየተደሰትን ለምናከብረዉ አንዱ ለሆነዉ ለብርሃነ ጥምቀቱ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን በድጋሜ ለማለት ለማለት እወዳለሁ።
ጥምቀት በዓል ከሐይማኖታዊ ሥርዓቱ በተጨማሪ በልዩ ልዩ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀትና በጋራ በማክበራችን ዓለም ተረክቦናል፡፡ በጋራና በትጋት ከሠራን፥ አገራችን ለዓለም ልታበረክተው የምትችለው በርካታ ያልተነኩ ሀብቶች አሏት።
ይህንኑ ትልቁን የጥምቀት በዓል በወረዳችን በሁሉም አከባቢዎች ላይ ከሚያስደስቱ በአሎቻችን አንዱ በመሆኑ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር፣ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋዩ፣ ጨዋዉና ሰላም ወዳዱ የወረዳችን ህዝብ ወትሮም እንደምናደርገው ሁሉ በትብብርና በአብሮነት አካባቢያችንን በንቃት በመጠበቅ፤ ከፀጥታ ሃይሎቻችን ጋር በትብብር በመስራት፤ እንድናሳልፍ ዘንድ ጥሪ አስተላልፈዋል !!
እንዲሁም ጥምቀቱን ስናከብር ቅንነትን ተላብሰን፣ በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች የተጎዱ ወገኖቻችንን በቸርነት ዓይናችን እያየን፣ የተቸገሩትን በድጋፍ እጃችን እየጎበኘን መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
መልካም የጥምቀት በዓል!!!
፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥፥
ጥር 10 ቀን 2015ዓ.ም