Central Ethiopia Region Bureau of Agriculture

Central Ethiopia  Region Bureau of Agriculture This is official page Central Ethiopia Region Bureau of agriculture
(1)

02/06/2026

ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተመላከተ ********************ግንቦት 25/2018የማዕከላዊ ኢተዮጵያ ክልል የፖለ...
02/06/2026

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተመላከተ
********************
ግንቦት 25/2018

የማዕከላዊ ኢተዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ላይ ያለውን ተሳትፎ ያሳየበት እንደነበር ተናግረዋል።

ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በመሳተፍ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ሲመርጥ መዋሉን ተናግረዋል ።

በክልሉ ትላንት በተካሔደው ጠቅላላ ምርጫ ላይ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎች መሳተፋቸውን የገለጹት አቶ ደምስ ምርጫው ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ የጋራ ምክር ቤቱ የላቀ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል።

ምርጫ ለሀገረ መንግስት ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት ሰብሳቢው ለዚህም የጋራ ምክር ቤቱ ምርጫው ሰላማዊ፣ዴሞክራሲያዊ እና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት ሲሰራ እንደነበር አስታውሰዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሀገሪቱን እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን ህግ እየተከተሉ መሄድ ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን በውይይት እየፈታ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በትላንትናው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ህዝቡ በነጻነት ወጥቶ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ድምጽ ሲሰጥ መዋሉን አቶ ደምስ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ምርጫ ሊያደናቅፍ የሚችል ችግር አለመግጠሙን የተናገሩት ሰብሳቢው ይህ ደግሞ ህዝቡ የሚፈልገውን ፓርቲ በነጻነት እንዲመርጥ አስችሎታል ሲሉም አብራርተዋል።

ህዝቡ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ላደረገው የላቀ ጥረት አቶ ደምስ ምስጋና አቅርበዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በረከት ከድር በበኩላቸው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዋና ዋና መመዘኛዎች ሲታይ ሰላማዊ፣ፍትሀዊ እና ተአማኒነት ያለው ምርጫ ነው ብለዋል።

በክልሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሔደ ምርጫ ነው ያሉት አቶ በረከት በገዢው ፓርቲ ፣በተፎካካሪ ፓርቲዎች እንዲሁም በመንግስት በኩል ምርጫውን ለማካሔድ የነበረው ዝግጅት ውጤታማ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እንደነበር የተናገሩት አቶ በረከት በክልሉ 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች እና 5 የግል እጩዎች መሳተፋቸውን አስረድተዋል።

ምርጫ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው ዜጎች በመረጡት መንግስት የመተዳደር መብትን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ዜጎች በምርጫ የሚያደርጉት ንቁ ተሳትፎ ለሰላም፣ ለልማት እና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን አቶ በረከት በመግለጫቸው አብራርተዋል።

ክልሉን የተሞክሮ ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ውጤታማ ነው ያሉት ምክትል ሰብሳቢው የሰላም እና የተረጋጋ የፖለቲካ ባህል ግንባታ ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች በ35 የምርጫ ክልሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ማቋቋም በመቻሉ ለምርጫው ስኬታማነት የጎላ አበርክቶ እንደነበረው ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!ግንቦት 25 2018 ዓ.ምየመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

ግንቦት 25 2018 ዓ.ም

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክትየኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ...
01/06/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስደናቂም ተአምረኛም ሕዝብ ነው። ከፈጣሪ በቀር ሕዝባችንን አሟልቶ ሊያውቅና ሊገመግም የሚችል ማን ነው? የዳበረ ባህል፣ ሀገር ወዳድና የወል መሻቱን መጠበቅ የሚችል ሕዝብ መሆኑን በዘንድሮው ምርጫ ዳግም ለዓለም አሳይቷል። በዛሬው ታሪካዊ ዕለት፡-
• የሌሊቱ ብርድና ጨለማ ያላስፈራቸው፣
• የቀትሩ ፀሐይና ድንገተኛ ዝናብ ያልበገራቸው
• ሠርግ፣ ኀዘን፣ ወሊድና ሌሎች ማኅበራዊ ሁነቶች ያላገዳቸው፣
• ረጃጅም ሰልፎች ያላታከታቸው፣
• የአካል ጉዳት ድምጽ ለመስጠት ያልገደባቸው፣
• ሕመም እና እርጅና የሀገር ተስፋን ከማየት ያላገዳቸው፣
• የነገ ሀገር ተረካቢ ጨቅላ ልጃቸውን ማዘል ያላደከማቸው፣
• ከምንም በላይ የጠላት ጩኸትና ማስፈራሪያ ያላስቆማቸው ዜጎች፤
በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል (against all odds) ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡

ይሄንን ሕዝብ ማገልገል መታደል ነውና ተመራጮች ያከበራችሁን አክብራችሁ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ዋጋ የከፈለውን ይሄንን ሕዝብ በንጽሕና ለማገልገል ያብቃችሁ።

ድምፄን በመስጠቴ እድለኛ ነኝ የዛሬው ምርጫ የኢትዮጵያን ነገ የሚወስን ታሪካዊ ሂደት ነው፦ አቶ ኡስማን ሱሩር7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የደምጽ አሰጣጥ ስነ ስርአት ከማለዳው 12:00 ሰዓት በስልጤ...
01/06/2026

ድምፄን በመስጠቴ እድለኛ ነኝ የዛሬው ምርጫ የኢትዮጵያን ነገ የሚወስን ታሪካዊ ሂደት ነው፦ አቶ ኡስማን ሱሩር

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የደምጽ አሰጣጥ ስነ ስርአት ከማለዳው 12:00 ሰዓት በስልጤ ዞን የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች እየተካሔደ ይገኛል።

በላንፉሮ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ኡስማን ሱሩር ሌሊቱን ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

የዘንድሮው ምርጫ በፍትሃዊ፣ሰላማዊና አካታች መንገድ እየተካሄደ መሆኑ የዴሞክራሲ ጉዞውን የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

ዛሬ ድምፄን በመስጠቴ እጅግ ደስተኛና እድለኛ ነኝ ያሉት ሀላፊው በምርጫ ጣቢያዎች የተፈጠረው ድባብ በጣም አስደሳች ነውም ብለዋል።

ዜጎች በከፍተኛ ንቃትና ተሳትፎ ወጥተው ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፤ ይህም የህዝባችንን የዴሞክራሲ ግንዛቤና የፖለቲካ ተሳትፎ ባህል ከፍ ማለቱን እንደሚያሳይ አቶ ኡስማን አብራርተዋል።

የዛሬው ምርጫ የኢትዮጵያን የወደፊት አቅጣጫና እጣ ፈንታ የሚወስን ታሪካዊ ሂደት እንደሆነም ገልፀዋል።

በሀገሪቱ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ምህዳር እየሰፋ መምጣቱ ለተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶች ዕድል በመፍጠር ዜጎች የፈለጉትን አማራጭ በነጻነት እንዲመርጡ አስችሏል ብለዋል።

ቀደም ተብሎ የተሰሩ የምህዳር ማስፋት ሥራዎች ውጤታማ ሆነው እየታዩ ነው፤ ይህም ለአፍሪካ አገራት ጭምር ምሳሌ ሊሆን የሚችል ተሞክሮ ነው ሲሉም አክለዋል።

ኢትዮጵያ ሰፊ አቅምና የበለጸገ የሰው ኃይል ያላት ሀገር መሆኗን የጠቆሙት አቶ ኡስማን፣ ሀገሪቱ የማደግና የመበልፀግ ብሩህ ተስፋ እንዳላት ገልጸዋል።

በመጨረሻም ለተፎካካሪ ፓርቲዎችና እጩዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ የህዝብን ውሳኔና ድምፅ ማክበር የዴሞክራሲ መሠረታዊ መርህ መሆኑን ጠቅሰው፣ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን በፀጋ ተቀብሎ ለሀገር ሰላምና መረጋጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምርጫው ለኢትዮጵያ የተሻለ የዴሞክራሲ ባህልና ለጋራ ለውጥ መሠረት የሚጥል ታሪካዊ እርምጃ ነው" ብለዋል።

01/06/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
01/06/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።

በስልጤ ዞን ላንፉሮ ምርጫ ክልል በርካታ ዜጎች በወሰዱት ካርድ የሚመራቸውን ፓርቲ ለመምረጥ በምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ድምፅ በመስጠት ላይ ናቸው።
01/06/2026

በስልጤ ዞን ላንፉሮ ምርጫ ክልል በርካታ ዜጎች በወሰዱት ካርድ የሚመራቸውን ፓርቲ ለመምረጥ በምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ድምፅ በመስጠት ላይ ናቸው።

01/06/2026

Address

Durame

Telephone

+251935490375

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region Bureau of Agriculture posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share