15/12/2020
የከምባታ ጠምባሮ ዞን እንስሳትና ዓሳ ሃብት መምሪያ የ5 ወር ዕቅድ ከንዉን አፈፃፀም
በወተት ሀብት ልማት ከፍተኛ ድርሻ ያላዉ የዳልጋ ከብት ሲሆን ከ812,175 ዳልጋ ከብቶች ውስጥ የተሻሻሉ የውጭ ደም ያላቸው ዳልጋ ከብቶች ብዛት ከ29.2% በላይ ነው፡፡ የወተት ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግና ዝርያን ከማሻሻል አንጻር የሀገረሰብ ላሞችንና ጊደሮችን በሰው ሰራሽ ዘዴ ፣ በሆርሞን ማድራት ቴክኖሎጂና በተፈጥሮ የውጭ ደም ባላቸው ኮርማዎች በማዳቀል ዳልጋ ከብት ዝርያን ከማሻሻል በተጨማሪ የወተት ምርት በመጨመር አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ የወተት ምርት በቀን ከሀገረሰብ ዝርያ በአማካይ 1ሊትር ከነበረበት 2.5 ሊትር ፣ ከዲቃላ ዳልጋ ከብቶች በአማካይ አ/አደሮች በቀን 16-18 ሊትር እና በሞዴሎች 27-36 ሊ/ር ወተት እየተመረተ ይገኛል፡፡
ይህንን ሀብት ለማልማት የሚያስችሉ የተለያዩ ጥረቶች በመደረጋቸው ውጤት እየተገኘ ይገኛል፣ አብዛኛው ህብረተሰብም በእንስሳት እርባታው ዘርፍ ከፍተኛ ጥቅም እያገኘ ይገኛል፣ቢሆንም የተገኙ ውጤቶች ሲመዘኑ አ/አደሩ ሆነ ዞኑ ከዘርፉ ማግኘት ከሚገባው ዝቅተኛ ነው፤ሰለሆነም በበጄት ዓመቱ የአፈጻጸም አቅጣጫዎችን በመለየት ወደ ትግበራ ገብተናል፤በበጀት ዓመቱ የታቀዱ ዋና ዋና የዕቅድ ግቦች እና የአፈጻጸም አቅጣጫዎች
1. የማስፈጸም አቅም ግንባታ ማጠናከር፣
2. የተጠናከረ የኤክስቴንሽን አገልግሎት እንዲኖር ማስቻል፣
3.የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፣
4.የእንስሳት ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ፣
5.የእንስሳት መኖ ልማት ማሳደግና አጠቃቀም ማሻሻል፣
6.የእንስሳት ጤና ሽፋንና አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣
7.የእንስሳትና ዓሣ ግብዓት አቅርቦት ማሳደግ፣
የማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎች
በእንስሳት ሀብት ልማት የአርሶ አደሩን የአመለካከት እና የግንዛቤ ደረጃውን ለማሻሻል ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን በቂ ክህሎት ኖሮት እንዲፈፅም ለማድረግ የሚያስችል ተደራሽና ብቃትያለው የኤክስቴንሽን አገልግሎት ለመስጠት ስርዓት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፡፡ ለዚህም ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ አደረጃጀት በመዘርጋት ፣አገልግሎቱን የሚሰጡ በተለያየየ ሙያ ስብጥርና ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በመመደብና በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከል ሠርቶ ማሳያ ፣ የክህሎት ስልጠናና የቤት ለቤት የሙያ ድጋፍና የምክር አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
በዓመቱ የተያዙ ግቦችን ባለሙያው በሙሉ ዕውቀትና ክህሎት በማሳካት የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስመዘገብ ከማስቻል አንጻር የአስፈጻሚውንም ሆነ የፈጻሚ ባለሙያ አቅም ማሳደግ ተገቢ ነው፡፡በዚህ መሰረት የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሥራዎችን በሕዝብ ንቅናቄ በማካሄድ እስከ ቀበሌ የንቅናቄ መድረኮች ተዘጋጅተዋል፡፡
በ2013 ዓ.ም የተደረጉ የንቅናቄ መድረክ
የ2012 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ሪፖርት ለ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙርያ ከባለድርሻ አከላትና ከህብርተሰቡ የጋረ መድርክ ተፈጥሮል፡፡
በወረደ በ2012 በጅት ዓመት የነበራዉን የአዳቃዮች የዕቅድ ክንዉን የግምገማ መድራክ በማዘጋጀት ግምገማ በመከሄድ ማሻሻል የሚገባቸዉን ጉዳዮች ላይ አቅጠጫ በማሳየት የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ ለዝርያ ማሻሻል ሥራዎች ከአዳቃይ በላሙያዎች የጋረ መግባበት በመፍጠር የግል ዕቅድ እንድተቀድ ተድርጓል፡፡ ዞናዊ ስንክሮነይዜሽን ንቀናቄ በሀደሮ ጡንጦ ዙርያ ወረደ ተሳታፊዎች ወ 170 ሴ 40 ድ 210 ስሆኑ በዞኑ ዉስጥ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የስንክሮነይዜሽ ዘመቻ በንቅናቄ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የፌዴራል እና የክልላዊ የበለድርሻ አከላት የመስክ ጉቡኝት በእንስሳት ዘርፊ እና የእንስሳት ሴክተር ፕሮጀክት ሥረዎች በቀ/ጋሜላ ወረዳ ተደርጎል ፡፡
የ2012 በጀት ዓመት የ4ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ ክንዉን ግምገማ ከበላድርሻ አካለት ጋር በመገምገም የሉ ክፍታቶችችን በማለየት በቀጠይ በ2013 ዓመት የዕቅድ አካል ሆኖ የለተፈጽሙ ተግባራት እንዲፋጻሙ በመወያያት ተመምናናል፡፡
የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ አፈጸጻም የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በወተት ምርት ምርታማነታቸው ዝቅተኛ የሆኑ የሀገርሰብ ዝርያ ላሞችን/ጊደሮችን የተሻለ ምርታማነት ካላቸው የውጭ ዝርያዎች ጋር የማዳቀል ሥራ በዓመቱ 30794 በሰው ሠራሽ ዘዴ፤6584 ለሆርሞን ምላሽ ስጥታዉ በሲንክሮናይዜሺን እና 2204 በተፈጥሮ ኮርማ ፍላጎት አሳይታዉ የተደቀሉ 10994 በተሻሻሉ የውጭ ደም ካላቸው ኮርማዎች በድምሩ 50576 ላሞችንና ጊደሮችን ለማዳቀል ታቅዶ በመደበኛ ሰው ሰራሽ ዘዴ እስከዚህ ወር ድረስ 8781 (52.2)፤ በሲንክሮናይዜሽን ለሆርሞን ምለሽ ሰጥተው የተደቀሉእስከዚህ ወር ድረስ 2860(46%) ፤ቀጥታ የተደቀሉእስከዚህ ወር ድረስ 1144(62%) በተሻሻለ ኮርማ እስከዚህ ወር ድረስ 4605 በድምሩ በሦስቱም ዝርያ ማሻሻያ ዘዴ 17390 (34%) ላሞችና ጊደሮችን ለማዳቀል ተችሏል፡፡በ2012 በጀት ዓመት ከሁለተኛው ሩብ ዓመት ጀምሮ እስከዚህ ሩብ ዓመት በመደበኛ የሰው ሰራሽ ማዳቀል አገልግሎት ከተዳቀሉ ላሞችና ጊደሮች 16385፣በተሻሻሉ ኮርማ ዝርያዎች ከተዳቀሉት 6627 በስንክሮናይዜሽን 4912 በድምሩ 27924 ዲቃላ ጥጆችን ለማግኘት ታቅዶ በመደበኛ ሰው ሰራሽ ማዳቀል አገልግሎትእስከዚህ ወር ድረስ 4348፣ በተሻሻሉ ኮርማ ዝርያዎች ከተዳቀሉትእስከዚህ ወር ድረስ 2228 በድምሩ 6576 ዲቃላ ጥጆችን ለማግኘት ተችሏል፡፡በዝርያ ማሻሻል ስራም ወ 8518 ሴ 4864 አርሶ አደሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የወተት ምርትን ከተሻሻሉ ላሞች 95171 ቶን ታቅዶ፣ከሀገረሰብ ላሞች 47560.14 ቶን በድምሩ142731.14 ቶን ለመምረት ታቅዶ ከተሻሻሉ ላሞች 65254.45 ሲከናወን ከሀገረሰብ ላሞች 21694.94 ለመከናወን ተችሏል፡፡
የዶሮ ሥጋና እንቁላል ምርት ማሻሻያ ተግባራት
በዶሮ እርባታ የአ/አደሩን ግንዛቤ በማሳደግና ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በአጭር ጊዜ ዉጤታማ የሚያደርጉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እንዲቀርቡና አ/አደሩም ተግባራዊ እንዲያደርግ በማድረግ የዶሮ ዝሪያዎችን ለማሻሻል ለአ/አደሮች ክህሎት ሥልጠና በመስጠት በዓመቱ 315684 የ48 ቀን ዕድሜ ቄብና ኮክኔ ለማሰራጨት ታቅዶ 105222 (33%) የ48 ቀን ዕድሜ ቄብና ኮክኔ እስከዚህ ወር ድረስ የተሰራጨ ሲሆን እንዲሁም 325960 የአንድ ቀን ዕድሜ ጫጩት ለማሠራጨት ታቅዶ 117742 (36%) የአንድ ቀን ዕድሜ ጫጩት እስከዚህ ወር ተሰራጭቷል፡፡ የዶሮ እንቁላል ምርት በሚመለከት 2,280 ቶን እንቁላል ምርት ለማምረት ታቅዶ 597.75 (26%) ቶን እንቁላል ተመርቷል፡፡
የዶሮ አያያዝን የተሻለ ለማድረግና ዶሮዎችን ከተለያዩ ጥቃቶች ለመከላከል ይቻል ዘንድ ከዚህ በፊት በተሰሩ ዶሮ ቤት በተጨማሪ እስከዚህ ወር 4,044 የዶሮ ቤት ለመስራት ታቅዶ እስከዚህ ወር 611 ተሠርቷል፡፡
በዶሮና እንቁላል ሀብት ልማት በአጠቃላይ ወ 4839 ሴ 2053 አ/አደሮች መሳተፍ ተችሏል፡፡
የበግና ፍየል ምርታማነት ከማሻሻል አንፃር ከምርምር ማዕከላት ምርታማነታቸው የተረጋገጠ እሰከዚህ ወር1023 የበግ (ዶዮገና) ታቅዶ208 በግ ለማቅረብ ተችሏል፡፡
የአነስተኛ አመንዣኪ እንስሳት ዝርያ የማሻሻል ስራም በተለያዩ ጊዜያት በቀረቡ የሀገረሰብና የዉጭ አዉራ በጎችና ፍየሎች ድቀላ በዓመቱ 78,028 የበግ ግልገሎችና 12140 የፍየል ግልገሎች ለማግኘት ታቅዶ 23440 (30%) የበግ እና የፍየል 4280 (35%) የፍየል ግልገሎች ተወልደዋል፡፡
የሥጋ ምርት ማሻሻያ አፈጸጻም
በእንስሳት የማድለብና የማሞከት ሥራዎች አ/አደሩን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ከድለባ ከብቶች አመራረጥ ጀምሮ በመኖ አጠቃቀም፣ በመጠለያ አዘገጃጀትና በጤና አጠባበቅ ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ለአ/አደሩ ክህሎት ሥልጠና በመስጠት በዓመቱ 90123 የዳልጋ ከብት፣75432 በጎችን እና 63211 ፍየሎችን በድምሩ 228766 ለማድለብና ለማሞከት ታቅዶ ዳልጋ ከብት 37920፣ በጎችን ማሞከት 23618፣ እና ፍየሎችን ማሞከት14470 በድምሩ 76008 ማድለብና ማሞከት ተችሏል፡፡ የሥጋ ምርት በሚመለከት ከዳ/ከብት 15581 ቶን ፣ ከበግ 1134ቶን፣ ከፍየል 962 ቶንና ከዶሮ 509 ቶን ስጋ ለማምረት በድምሩ 18186 ታቅዶ ከዳ/ከብት 6967ቶን ፣ ከበግ 369ቶን፣ ከፍየል 247.43 ቶንና ከዶሮ 114 ቶን በድምሩ 7588.15 ቶን ስጋ ለማምረት ተችሏል:: በአጠቃላይ በስጋ ምርት ማሻሻያ በተከናወኑ ተግባራት በድምሩ 4,425 (,765 ሴቶች) አ/አደሮች ተሳታፊ ሆኗል፡፡
ማርና ሰም ምርት ማሻሻያ ተግባራት አፈጸጻም
የማርና ሰም ምርታማነትን የሚያሰድጉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም አርሶ አደሩ ከዘርፉ የሚገኘዉን ምርት ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ያለ ሲሆን በቴክኖሎጂ አቅርቦት በዓመቱ 4324 ጨፈቃ ፣ 888 የሽግግር ፤654 ባለፍሬም ቀፎ ለማሰራጨት ታቅዶ ጨፈቃ ቀፎ 170 ፣የሽግግር 14 ቀፎ፤ ባለፍሬም ቀፎ 65 የተሰራጨ ሲሆን የማር ምርትንና ምርታማነት 691 ቶን ማር ለማምረት ታቅዶ177.5 ቶን ለማምረት የተቸለ ሲሆን የሰም ምርት 55.2 ለመምረት ታቅዶ 5.6 የሰም ምርት ለመግኘት ተችሏል፡፡የተባዛ ንግስት የእስከዝህ ዕቅድ 911 የእስከዚህ ክንዉን 53 በንብ ፣በማርና ሰም ምርት የማሻሻያ ስራ 1050 (59 ሴቶች) አርሶ አደሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡:
የ2012/13 ዓ/ም የህደር ወር የእንስሳት መኖ ልማትና አጠቃቀም ሥራዎች ሪፖሪት
የእንስሳትን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም በመኖ ዕጥረት የሚከሰቱትን የእንስሳት በሽታዎችን ለመከላከል የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በብዛትና በጥራት ለማሳደግ የተሻሻሉ የመኖ ዕጽዋትና ዛፎችን ማልማት፣ የሰብል ተረፈ ምርት ንጥረ ነገር ይዘት ለማሻሻል በዩሪያ ማበልፀግ ፣ የተጎዱ መሬቶችን ከልሎ በመኖ ዕጸዋት ማልማት ፣ ድርቅን የሚቋቋሙና በትንሽ መሬት ብዙ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ የተሻሻሉ ዕጽዋት አ/አደሩ እንዲያለማ እየተደረገ ሲሆን እስከዚህ ወር ድረስ9530 ሄ/ር በተሻሻለ የመኖ ዕጽዋት ለመሸፈን ታቅዶ እስከዚህ ወር 5789.6 ሄ/ር የለማ ሲሆን ከዚህም ከደልጋ ከብቶች ዝርያ ማሻሻል ጋር ተቀናጅቶ 3515 ሄ/ር ሲለማ ለተከላ የሚውል የመኖ ሣር ቁርጥራጭና ግንጣይ ተደራሽ እንዲሆን በመኖ ማበዣ፣በችግኝ ጣቢያና በአርሶ አደር ማሠልጠኛ ማዕከላት ላይ የብዜት ሥራዎች በማካሄድ አርሶ አደሩ በቅርበት እንዲያገኝ በማድረግ 173 ሚ/ን የመኖ ግጣይና ቁርጥራጭ፣5.55 ሚ/ን ችግኝ ለተከለ ውሏል፡፡ የዝናቡ ሥርጭት የተሸለ በመሆኑ መኖ ተከለ ስራ አሁንም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ጥቅም ላይ የዋለ የተመጣጠነ መኖ ስርጭት በሚመለከት በዞናችን መኖ ማቀነባበር ከተሰማረው አምበርቾየገበሬዎች ኀብረት ሥራ ጋር አ/አደሩ እንዲጠቀም የግንዘቤና የገበያ ትስስር በመፍጠር2633 ቶን ታቅዶ 418.99 ቶን የወተት 9 ቶን የድለባና 269.98 ቶን ደሮ በድምሩ 697.97 ቶን ተሰራጭቷል፡፡
እንስሳት ጤና 5 ወር ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም፡-
ስለ እንስሳት ጤና ግንዛቤ ማስጨበጥ፡- በበጀት ዓመቱ በመከላከያ ክትባት ካላንደር አጠቃቀምና የበሽታ መከላከያ ዘዴዎችና እንዲሁም ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ምንነትና መከላከል ላይ ለ170067 አርሶ አደሮች ግንዛቤ ለማስጨበጥ የታቀደ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ለ54644 አርሶ አደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ የተሰራ ሲሆን አፈጻጸሙ ከ55% ተፈጽሟል፡፡
የክትባት አገልግሎት አፈጻጸም፡- የእንስሳት በሽታ ክስተት ካላንደርን ታሳቢ ያደረገና ቅድመ መከላከልን መሠረት ያደረገ የክትባት አገልግሎት የዘርፉ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ሲሆን በበጀት ዓመቱ ዕቅድ 2,042,900 ዶዝ የተለያዩ ክትባቶችን ለመስጠት ታቅዶ እስካሁን 886,641ዶዝ የተለያዩ ክትባቶች አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን አፈጻጸሙ 43% ደርሷል፡፡
የህክምና አገልግሎት አፈጻጸም፡- ለልዩ ልዩ ተዛማችና ተላላፊ፣ ለውስጥና ለውጭ ጥገኛ፣ ለጡትና ለገንዲ በሽታዎች የህክምና አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን በዚህም በበጀት ዓመቱ ዕቅድ 351,200 የተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች ለመስጠት ታቅዶ 116,399(33%) እንስሳትን ለማከም ተችሏል፡፡
የክሊኒክ አገልግሎት አፈጻጸም፡- በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የክሊኒክ አገልግሎቶች የተሰጡ ሲሆን እስካሁን 100,349 በቁጥር ታቅዶ የእስካሁኑ ክንውን 36,283(36%) ለማከናወን ሲቻል፣
የበሽታ ፍንዳታ ሪፖርት፡- በእንስሳት ጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት የሚሰጠውና እስከ ዓለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት የሚደርስ የበሽታ ፍንዳታ ሪፖርት ሲሆን እንደዞን በ2ቱም ወር መላክ ከሚገባው 40 ሪፖርቶች ሁሉም ተልከዋል፡፡