11/09/2026
እንኳን ለ2019 ኢዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
==============================
የድሬደዋ አስተዳደር ነዋሪ በጋራ ካፈራቸውና ከገነባቸው ጠቃሚ ማህበራዊ እሴቶች ውስጥ ሀይማኖታዊና ሀገራዊ/ብሔራዊ በዓላትን በጋራ በመሰባሰብ ፣ በመጠያየቅ በመረዳዳትና ቤት ያፈራውን በመቋደስ በድምቀት ማክበሩ አንዱና ዋንኛው መሆኑ ይታወቃል ፡፡
በመሆኑም የሀገራችን ጸጋ በሆነችው የጳጉሜ ወር 5 ቀናቱንም በማክበር እነሆ አዱሱ አመት በደማቁ በማክበር ላይ እንገኛለን።
እነሆ አሮጌውን 2018 ሸኝተን አዲሱን 2019 አመት እንደወትሮው ከአመት አመት የምንሻገርበት ብቻ ሳይሆን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ባካሄድንበትና በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባት መፍጠር በተቻለበት ማግስት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ፡፡
ስለሆነም በድሬደዋ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኦንቨስትመንት ቢሮ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለመላው ነዋሪ ለአዲሱ የ2019 የዘመን መለወጫ በአል እንኳን አደረሳችሁ እያለ አዲሱ አመት በ2018 በባህልና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላስመዘገብናቸው ሁሉን አቀፍ ውጤቶችና ድሎች ለነበራችሁ የነቃ ተሳትፎ እያመሰገነኩ በአዲሱ አመትም ድሎቻችንና ውጤቶቻችንን ለማስቀጠልና ለማበልጸግ እንዲሁም የጋራና የወል ትርክትን በሀገራዊ አብሮነት ለማጽናት በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅበትን አስተዋጾ እንደሚያበረክትና ሀላፊነቱን እንደሚወጣ ያለኝን ጽኑ እምነት እየገለጽኩ አዲሱ አመት የሠላም፣የደስታ፣የፍቅር፣የብልጽግና አመት እንዲሆንልን መልካም ምኞቴን እያስተላለፍኩ በድጋሚ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ አደረሰን እላለሁ፡፡
አቶ ወንደሰን አባይ
=======የድሬዳዋ አስተዳደር የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት===