Ethiopian Institution of the Ombudsman Dire Dawa Branch

Ethiopian Institution of the Ombudsman Dire Dawa Branch we striving for good governance

31/05/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል-አድሃ በዓል አደረሳችሁ!መልካም በዓል!
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል-አድሃ በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞቹ ስልጠና ሰጠየኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሰራተኞቹን እውቀትና ክህሎት ለማሳደግና በስራቸው የሚጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በ...
25/05/2026

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሠራተኞቹ ስልጠና ሰጠ
የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሰራተኞቹን እውቀትና ክህሎት ለማሳደግና በስራቸው የሚጋጥማቸውን ተግዳሮቶች በዕውቀትና በምክንያታዊነት እንዲፈጽሙ ለማድረግ ተከታታይ ስልጠናዎችን ይሰጣል ፡፡በሳለፍነው ሳምንትም ይህኑኑ ለማጠናከር በአዳማ ከተማ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕንባ ጠባቂ ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ዉቤ ለሰልጣኞቹ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸው የተቋሙ ሰራተኞች ጊዜው የሚፈቅደውን አቅምና ችሎታ ማዳበራቸው ተቋሙ በህግ የተሰጠውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት የሚስችል መሆኑን ጠቅሰው ሰራተኞቹ በንቃትና ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ ስልጠናውን እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡
በስልጠናው ሰራተኞቹ ልብ ሊሎቸው የሚገቡ የተቋሙ ስልጣንና ተግባራትን በተመለከተ በምክትል ዋና ዕንባ ጠባቂ በክቡር ዶ/ር የኔነህ ስመኝ በስራ ላይ ያሚጋጥሙ ችግሮችን በመንቀስ ተግባራዊ የሆነ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ሰልጣኞቹም ለስራቸው አጋዥ የሆነ ጠቃሚ ትምህርት እንደወሰዱ ገልጸዋል፡፡

21/05/2026
ማስታወቂያ
20/05/2026

ማስታወቂያ

10/05/2026

Ahadu TV / አሐዱ ቴሌቪዥን's Post
Ahadu TV / አሐዱ ቴሌቪዥን
April 23 at 5:30 PM
·
መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችል ሕግ ተዘጋጀ
አዲሱ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ የግል ተቋማት ጭምር መረጃ እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ በማካተት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል።
ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. (አሐዱ ሬዲዮ) - የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነት የየራሳቸው ባህሪ ቢኖራቸውም እስካሁን የመገናኛ ብዙሃን እና መረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 በሚል በአንድ ላይ ተጣምረው ቆይተዋል።
ይህ ደግሞ ግልጽ የአሰራር ስርዓት እንዳይዘረጋ ማድረጉን የተናገሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፤ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ለብቻው ተረቅቆ መቅረቡን ገልጸዋል።
ሰባት ክፍሎች እና 60 አንቀጾችን የያዘው ይህ የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ፤ በዋናነት አዋጁን የማስፈጸም ሙሉ ስልጣን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ይሰጣል። ማንኛውም ዜጋ መረጃ በሚጠይቅበት ወቅት መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ ተጠያቂነትን የሚያስከትል መሆኑም ተገልጿል።
ረቂቅ አዋጁ የመንግስት ተቋማትን ብቻ ሳይሆን ከህዝብ አገልግሎት ጋር በቀጥታ የሚገናኙ የግል ድርጅቶችንም ጭምር መረጃ እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ ማካተቱ በጥንካሬ ተነስቷል። ይህም ጥሩ ድንጋጌ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ረቂቅ አዋጁ ይፋ የማይደረጉ መረጃዎች በማለት በአንቀጽ 18 ላይ በዝርዝር ያስቀመጠው ድንጋጌ የክርክር መነሻ ሆኗል። በዚህም መሰረት የመከላከያ እና የሀገር ደህንነት መረጃዎች ፣ የፍርድ ቤት ምርመራ ሂደቶች እና የድርጅት ሚስጥሮች የህግ ጥበቃ እንደሚያገኙና ይፋ እንደማይደረጉ ይገልጻል።
የምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ይህ አንቀጽ ለተለያየ ትርጉም የተጋለጠ በመሆኑ እና ለብልሹ አሰራር ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር ስለሚችል በዝርዝር እንዲታይ ምክረ ሃሳብ አቅርበዋል።
አሐዱ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡበት ጠበቃ እና የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ ዳንኤል ፍቃዱን አነጋግሯል። የህግ ባለሙያው የረቂቅ አዋጁ ዋነኛ አላማ ሁለቱን አዋጆች መለያየት መሆኑን አብራርተዋል።
በአዋጁ ከተካተቱ መሰረታዊ ድንጋጌዎች መካከል የመንግስት ኃላፊዎች ተጠያቂ የሚሆኑበት እና መረጃ የሚሰጡበት ጊዜ ገደብ መወሰኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም ጋዜጠኞች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳይታሰሩ የሚያግድ ድንጋጌ መካተቱንም ገልጸዋል።
አዋጁን የማስፈጸም ስልጣን ለህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም መሰጠቱን የገለጹት የህግ ባለሙያው ትችት በቀረበበት የደህንነት መረጃዎች አያያዝ ዙሪያም አስተያየታቸውን ሲሰጡ አዋጁ ወደ ፊት ሲጸድቅ የትኛው መረጃ በሚስጥርነት እንደሚፈረጅ ግልጽና በማያሻማ መንገድ ሊቀመጥ ይገባል ብለዋል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይህንን መረጃ የመጠየቅ ፣ የማግኘት እና የማስተላለፍ ጉዳዮችን የሚመለከተውን የመረጃ ነፃነት ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 10/2018 ሆኖ ለተጨማሪ ምርመራ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ/ም ለዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱ ይታወሳል።
በፋሲል አረጋይ

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞቸችና አመራሮች ውይይት አካሄዱየኢትዮጲያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞቸችና አመራሮች ውይይት  ያደረጉባቸው ጉዳችም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን የዘጠኝ...
10/05/2026

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞቸችና አመራሮች ውይይት አካሄዱ

የኢትዮጲያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞቸችና አመራሮች ውይይት ያደረጉባቸው ጉዳችም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን የዘጠኝ ወር አፈጻጸም አስመልክቶ የተከናወኑ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ላይ በተሰጠው ግብረ መልስ ሲሆን የተሰጠውን ግብረ መልስ አስመልክቶ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባኔ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በገለጻው በግብረ ምላሹ የተሰጡ ጠንካራ አፈጻጸሞችና የተለዩ ክፍተተቶችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን ሰራተኞች በቀረበው ገለጻ ላይ ሰፊ ውይይት አደርጓል ፡፡
በመቀጠል ሰራተኛው የ2019 በጀት መነሻ እቅድ ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን እቅዱንም አቶ ሚሊዮን ከበደ የእቅድ ዝግጅት ከፍተኛ ባለሙያ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰራተኛው መስተካከልና መሻሻል በሚገባቸው ላይ አስተያያቶችን ያቀረቡ ሲሆን በሰፊውም ውይይት ተደርጎበታል፡፡በመጨረሻም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባኔ በቀሪ የ2 ወራትም ስራዎች አሁን በተያዘው አካሄድ ተግባራዊ ሊደረጉ እንደሚገባ እና የታዩ ውስንነቶችም ትኩረት ተሠጥቶት እንዲሠራ በማድረግ ቅ/ፅ/ቤቱ የበለጠ አበረታች እና ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን መቀጠል እንዳለበት በማሰሳብ የማጠቃለያ ሀሳብ በመስጠት አጠናቀዋል።

አንኳን ለ85ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል አደረሰዎ!
05/05/2026

አንኳን ለ85ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል አደረሰዎ!

ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ለ51ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ137ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ደግሞ “የሠራተኛ መብት መከበር ለኢንዱስትሪ ሰላምና ለምርታማነት መሠረ...
01/05/2026

ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በኢትዮጵያ ለ51ኛ ጊዜ በመከበር ላይ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ137ኛ ጊዜ፣ በሀገራችን ደግሞ “የሠራተኛ መብት መከበር ለኢንዱስትሪ ሰላምና ለምርታማነት መሠረት ነው!” በሚል መሪ ቃል ለ51ኛ ጊዜ ይከበራል።
የሰራተኞችን መብት ማክበር ለሀገር እድገት እና ለምርታማነት መጨመር ያለው አበርክቶ ከፍተኛ ነው፡፡

Address

Dire Dawa
2112

Telephone

+251251110859

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Institution of the Ombudsman Dire Dawa Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Institution of the Ombudsman Dire Dawa Branch:

Share