Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau

Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau ፆታዊ ጥቃት ይቁም!
(1)

30/05/2026

በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመጠቆምም ሆነ ሲያጋጥምዎ ሪፖርት ለማድረግ የቦርዱ ነፃ የጥሪ ማዕከል ቁጥሮች በሆኑት 7555 እና 6214 በመደወል ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም ከታች የተቀመጡትን ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

Website: https://l1nq.com/n5amd66

X (Twitter): https://t.ly/o2nM9

Telegram: https://t.ly/BmT_4

YouTube: https://t.ly/N80Eo

LinkedIn: https://t.ly/zntYV

WhatsApp: https://t.ly/3Gfih

TikTok: https://surl.li/rrtdog

የአስተዳደራችን ሴቶች፣ አንድ ቀን ብቻ የቀረው ተወካያችሁን ለመምረጥ ዝግጁ ናችሁ!?
30/05/2026

የአስተዳደራችን ሴቶች፣ አንድ ቀን ብቻ የቀረው ተወካያችሁን ለመምረጥ ዝግጁ ናችሁ!?

_በዓላትን በደስታ እና በጋራ ስናከብር፣ ለተቸገሩ እና ብቻቸውን የሚያሳልፉ እንዳሉ እናስታውስ፣ እንርዳ!_ህፃናት የቤተሰብ ፍቅር አግኝተው መልካም ሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ሁላችንም ሃ...
29/05/2026

_በዓላትን በደስታ እና በጋራ ስናከብር፣ ለተቸገሩ እና ብቻቸውን የሚያሳልፉ እንዳሉ እናስታውስ፣ እንርዳ!

_ህፃናት የቤተሰብ ፍቅር አግኝተው መልካም ሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ ሁላችንም ሃላፊነት እንውሰድ - ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ

ህፃናት የቤተሰብ ፍቅር እንዲያገኙና መልካም ሥነ ምግባርን ታንጸው እንዲያድጉ ሁሉም ዜጋ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ ጥሪ አቀረቡ

ወ/ሮ ለሊሴ መልዕክቱን ያስተላለፉት የኢማሙ አል ነዋዊ ኮሌጅ የሴቶች ተማሪዎች የ1447ኛው ዓ.ሕ የዒድ አል አደሃ በዓል ደስታን በጋራ ለማካፈል ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ በመገኘት ነው።

በንግግራቸውም በአስተዳደሩ በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸውን ያጡ፣ ተጥለው የተገኙ ለችግር የተጋለጡ በርካታ ህፃናት እንዳሉና መንግስት በማቆያ ማዕከል እያሳደገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ይሁን እንጂ ብቻቸው የሚያድጉ ህፃናት ለሥነ ልቦናዊ ጥቃቶች ሊጋለጡ እንደሚችሉ እና መንግስት ብቻውን ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚያስቸግር ገልጸዋል።

ስለ ሆነም መንግስት ያመቻቸውን የሀገር ውስጥ አማራጮች እና ባህላችንም የሆነው 'በጉዲፈቻ' ህፃናት ወስዶ ማሳደግ እንዲሁም በአደራ ቤተሰብ (Foster Care) ወስዶ ማንከባከብ የሚቻል መሆኑን አስረድተዋል።

ሁሉም ሰው ህፃናትን እንደ እናት እና አባት አድርጎ ማሳደግ ይችላል፣ ይህም የቤተሰብ ፍቅር እንዲያገኙ እና በጥሩ ባህሪ እንዲያድጉ ይረዳቸዋል ብለዋል።

በዓላትን በደስታ እና በጋራ ስናከብር፣ ለተቸገሩ እና ብቻቸውን የሚያሳልፉ እንዳሉ እናስታውስ፣ እንርዳ። በእስልምና እምነት መሠረት የሃይማኖት ተከታዮች የተቸገሩትን ሁሉ የመርዳት ግዴታ አለባቸው። ለዚህም ደግሞ እኛ ሴቶች እንደ እናትነትም ጭምር ትልቅ ሚና ስላለን የበኩላችንን ሃላፊነት በቀዳሚነት መወጣት አለብን ነው ያሉት።

ብዙዎቻችን እንደዚህ አይነት ልጆች መኖራቸውን አናውቅም። እና የምናውቀውም ምን አስተዋጽዖ አድርገናል? ሲሉም ጠይቀዋል ወ/ሮ ለሊሴ!

እውነት ነው። ስንቶቻችን ነው የምናውቀው?፣ አስተዋጽዖ ያደረግነውስ? እራሳችንን እንጠይቅ!

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

   የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ ባልደረባችን የነበሩ አቶ ኤፍሬም ስዩም ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ግንቦት 19/2018 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ...
28/05/2026


የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የስራ ባልደረባችን የነበሩ አቶ ኤፍሬም ስዩም ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ግንቦት 19/2018 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአቶ ኤፍሬም ስዩም ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን!!

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

የአረፋ በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ መሆን አለበት» - ከንቲባ ከድር ጁሀር​የመላው እስልምና እምነት ተከታዮች የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብሩ የተቸገሩ ወገኖችን...
27/05/2026

የአረፋ በዓልን ስናከብር የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ መሆን አለበት» - ከንቲባ ከድር ጁሀር

​የመላው እስልምና እምነት ተከታዮች የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓልን ሲያከብሩ የተቸገሩ ወገኖችን በመረዳዳት እና በማሰብ መሆን እንዳለበት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ገለጹ።

​ከንቲባው ይህንን ያሉት «ሳፈር ቱሞሮ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን» እና የቂን የበጎ አድራጎት ድርጅት የአረፋ በዓልን በማስመልክት ያዘጋጁትን የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በታደሙበት ወቅት ነው።

​በእስልምና እምነት አስተምህሮ መሠረት ለአረፋ በዓል ከሚታረደው መሥዋዕት ሥጋ ውስጥ አንዱ ሲሶ ለተቸገሩ ወገኖች እንዲሰጥ እንደሚደነግግ ይታወቃል። ይህንን የበዓሉን መንፈስ መነሻ በማድረግ ሁለቱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በጋራ በመሆን ዘንድሮም ለተቸገሩ ወገኖች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አከናውነዋል።

​በማዕድ ማጋራት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንደገለጹት፤ የአረፋ በዓል ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በመረዳዳት፣ በመተሳሰብ እና አብሮነትን በማጠናከር የሚያከብረው ታላቅ በዓል በመሆኑ፣ በበዓሉ ወቅት የተቸገሩ ወገኖችን መርዳትና ከጎናቸው መቆም ይገባል። አክለውም አስተዳደሩ በሚከተለው «ሰው ተኮር» የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ ለሚገኙ የበጎ አድራጎት ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

​የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለሊሴ አሕመድ በበኩላቸው፤ በዓሉ የተቸገሩ ወገኖች የሚደገፉበት መሆኑን ጠቅሰው፣ በቅርቡ የአስተዳደሩ ከንቲባ በሰጡት ልዩ ትኩረትና መመሪያ መሠረት በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በርካታ ችግረኛ ወገኖችን መደገፍ መቻሉን ተናግረዋል።

​የሴቨር ቱሞሮ አሶሴሽን እና የቂን የበጎ አድራጎት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ወይዘሮ ከሪማ ፉአድ እና አቶ አብዱለዚዝ ጀማል በበኩላቸው፤ የአረፋ በዓልን በማስመልክት ያደረጉት ይህ ድጋፍ አቅመ-ደካማ የሕብረተሰብ ክፍሎች በዓሉን በደስታ እና በሰላም እንዲያሳልፉ ለማገዝ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

ኃላፊዎቹ ለፕሮግራሙ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እና ድጋፍ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

በድሬዳዋ አስተዳደር አለም አቀፍ ስታዲየም የተካሄደው የ7ኛው የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሀ ግብር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ ከ...
26/05/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር አለም አቀፍ ስታዲየም የተካሄደው የ7ኛው የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያ መርሀ ግብር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ ከሌሎች የቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ከ500 በላይ የአስተዳደሩ ሴቶችን በማስተባበር ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።

እንኳን ለ1447 ዓ.ሒ. የዒድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን!🙏የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የስኬት እ...
26/05/2026

እንኳን ለ1447 ዓ.ሒ. የዒድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን!🙏

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የስኬት እንዲሆንልን መልካም ምኞቱን እየገለጸ፤

በዓሉን ስናከብር በሰው ሰራሽና በተፈጥሯዊ ክስተቶች ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሴቶች፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት፣ ደጋፊ የሌላቸውና አቅመ ደካማ የሆኑ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያንን በመርዳት እንድናሳልፍ ጥሪውን ያቀርባል።

መልካም በዓል!
Eid Mubarak...! 🕌🕋

26/05/2026
በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ለድሬዳዋ ገጠር ክላስተር ነዋሪዎች የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ድጋፍ ተደረገየድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ማዕቀፍ ...
15/05/2026

በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ለድሬዳዋ ገጠር ክላስተር ነዋሪዎች የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ድጋፍ ተደረገ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሰቆጣ ቃልኪዳን ፕሮግራም ማዕቀፍ ለነብሰ ጡርና አጥቢ እናቶች እንዲሁም ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰብ ክፍሎች የእንቁላል ጣይ ዶሮዎች ድጋፍ አድርጓል

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ለሊሴ አህመድ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የህጻናትን የመቀንጨር ችግር ለመቅረፍና ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ለማስቻል የጀመረችው ሰፊ ጥረት አካል ነው ብለዋል።

በዚህም ቢሮው በሰቆጣ ስምምነት መርሀ ግብር የተያዘውን ሰፊ ስራ ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸው የድጋፉ ተጠቃሚ የሆኑ እናቶች የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽነታቸውን ማሻሻል እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ማህበረሰብ ክፍሎች መጀመሪያ ላይ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን ፕሮግራሙ የህፃናት የመቀንጨር እና የመቀጨጭ ችግርን ለመከላከል እንደሚረዳ የቢሮው የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ ስለሺ ታደሰ ገልጸዋል።

የፕሮግራሙ የማህበራዊ ዝርፍ አስተባባሪ ወ/ሮ ራሄል ደነቀ በበኩላቸው የህብረተሰቡን የተመጣጠነ ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እንዲሁም ኢኮኖሚያቸውን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ እንደዚህ ያሉ ድጋፎች መስፋፋታቸው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ድጋፉ በአስተዳደሩ 4ቱም የገጠር ክላስተሮች በተመረጡ ቀበሌዎች ማለት (ከዋሂል ክላስተር በሀርላ ቀበለለ፣ ከአሰሊሶ በአሰሊሶ ቀበሌ፣ ከቢዮ አዋሌ በቢዮ አዋሌ ቀበሌ እንዲሁም ከጀልዴሳ ክላስተር በቡላሌ ቀበሌ) ለነፍሰጡርና ለሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም ኢኮኖሚያቸው ዝቅተኛ ለሆኑ እናቶች ድጋፍ ተደርጓል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ግንቦት 2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

የማይከፈልባቸው የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ የድሬዳዋ የሴቶች ማህበር ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር ጥምረት ጋር በመተባበር ለሴቶች የማይከፈልባቸው የእንክብካቤ...
13/05/2026

የማይከፈልባቸው የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራዎች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

የድሬዳዋ የሴቶች ማህበር ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበር ጥምረት ጋር በመተባበር ለሴቶች የማይከፈልባቸው የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራዎች ዙሪያ ለተለያዩ አካላት ስልጠና ተሰጠ

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ማህበር ፕሬዝደንት ወ/ሮ አሚና መሀመድ እንደተናገሩት ሴቶች በህይወት ዘመናቸው ተቆጥረው የማያልቅ የማይከፈልባቸው የእንክብካቤ እና የቤት ውስጥ ስራዎች የሚሰሩ ሲሆን እንደ አካባቢያችን ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ ከቤት ውጪም አብዛኛውን ስራ በመስራት ቤተሰብን የሚያስተዳድሩ ሴቶች ናቸው ብለዋል።

ይህንን ሁኔታ ለመለወጥም ሁሉም ከራሱ በመጀመር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝደንት ወ/ሮ ኢፍቱ አባስ በበኩላቸው ሴቶች በቤት ውስጥ የሚያከናውኗቸው የማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ሥራዎች እና እንክብካቤዎች ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ስለሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካል እውቅና መስጠት፣ ስራን በመከፋፈል የሴቶችን የሥራ ጫናም ለመቀነስ የራሱን ኃላፊነት በመወጣት አለበት ብለዋል፡፡

በስልጠናው የሃይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ የሴት አደረጃጀት አባላት፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮ እና ሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ሴቶች ለማይከፈልባቸው የቤት ውስጥ ስራዎች ከወንዶች ሦስት እጥፍ የሚበልጥ ጊዜ እንደሚሰጡና 93 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች በማይከፈልባቸው ሥራዎች ላይ መሆኑ ጥናቶች ይገልጻሉ።

የማይከፈልባቸው ሥራዎች ለዓለም-አቀፉ ኢኮኖሚ (GDP) 40 በመቶ አስተዋጽዖ እንዳላቸው ቢገለጽም፣ ነገር ግን፣ የሴቶች ሥራ በብሔራዊ የጉልበት አተረጓገም ውስጥ ሙሉ በሙሉ እውቅና አልተሰጠውም።

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ግንቦት 5/2018 ዓ.ም
#ድሬዳዋ

Address

Dire Dawa

Telephone

+251251113634

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dire Dawa Women's Children's & Social Affairs Bureau:

Share