Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau

Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau page
(21)

Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau is a Government office Established in Dire Dawa. የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በድሬዳዋ የተቋቋመ መንግስታዊ ቢሮ ነው.

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!ግንቦት 25 2018 ዓ.ምየመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

ግንቦት 25 2018 ዓ.ም

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

01/06/2026

7ኛው አገራዊ ምርጫ በድሬዳዋ

በኤደን ሳሙኤል
ምስል:-ዳዊት መስፍን

01/06/2026

7 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ ።

ምስል :- በያብስራ ተክሌ ።

01/06/2026

qaar ka mid ah bulshada ismaamulka dir dhaba oo aan la kulanay galinki danbe ee wakhtiga doorashada ayaa inoo sheegay in ay ka faa`idaysteen wakhtigooda oo ay doorashada ka qayb qaateen.

 #ዜና | በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ሴቶች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም በምርጫ ሂደቱ የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገለጹ  | ግንቦት 24/2018 የምርጫውን የድምፅ መስጠት ሂደት አስመ...
01/06/2026

#ዜና | በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ሴቶች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም በምርጫ ሂደቱ የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገለጹ

| ግንቦት 24/2018

የምርጫውን የድምፅ መስጠት ሂደት አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ የተለያዩ የምርጫ ክልል ነዋሪዎች፣ በተለይም ሴቶች ያሳዩት ከፍተኛ መነሳሳት የዜጎችን በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል የመወሰን መብት በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል ።

በምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፃቸውን የሰጡ ሴት ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ ምርጫው የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን የሚወስንበት ትልቅ አጋጣሚ በመሆኑ በንቃት መሳተፋቸውን ጠቁመዋል።

ሴቶች በፖለቲካዊና ማኅበራዊ ውሳኔዎች ላይ ያላቸው ድምፅ ይበልጥ እንዲሰማና ፍትሐዊ ውክልና እንዲረጋገጥ ይህ ምርጫ መልካም አጋጣሚ መሆኑንም አክለዋል።

ምርጫ ለሴቶች የተለየ የዲሞክራሲ ትርጉም እንዳለው የጠቀሱት አስተያየት ሰጭዎቹ፤ ነገን የተሻለ ለማድረግ፣ መብቶቻቸውን ለማስከበር በነፃነትና በሰላም መምረጣቸውን ተናግረዋል።

በኤደን ሳሙኤል
ምስል፦ ዳዊት መስፍን

01/06/2026

የወረዳ 2 አስተዳደር ነዋሪዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በየምርጫ ጣቢያዎቻቸው በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥቷል።

  | Dire Dawa Residents Express That the 7th General Election Voting Process Was Conducted in a Completely Peaceful and ...
01/06/2026

| Dire Dawa Residents Express That the 7th General Election Voting Process Was Conducted in a Completely Peaceful and Democratic Manner

| May 24/2018 E.C

The voting process of the 7th general election in the Dire Dawa Administration was conducted in a completely peaceful, free, and democratic environment, residents announced.

Sharing their observations regarding the voting process, residents stated that they arrived early at the designated polling stations starting from 6:00 AM and were able to properly exercise their democratic rights without any delays, pressure, or security concerns.

Female residents who cast their ballots noted that this general election is a major milestone that determines their future and fair representation, which is why they turned out in mass early in the morning to actively participate.

The commentators emphasized that general elections are the ultimate foundation for building a democratic system and ensuring the rule of law.

They further indicated that they voted in total freedom and peace to secure a better tomorrow and to safeguard their rights.

By Eden Samuel
Image:- Dawit Mesfin

01/06/2026

በድሬዳዋ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት ፍጹም ሰላማዊና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ መከናወኑን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ገለጹ

 #ዜና | 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ ።  | ግንቦት 24/2018     በዛሬው እለት ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመላው ሀገራችን 7 ተ...
01/06/2026

#ዜና | 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ ።

| ግንቦት 24/2018

በዛሬው እለት ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመላው ሀገራችን 7 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ እየተካሄደ ይገኛል ። ይህንን ታሪካዊ ዕለት ተከትሎ በድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 04 ስር በሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ፍፁም በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እየተከናወነም ይገኛል ።

​በወረዳው 04 በሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተን ያነጋገርናቸው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች በበኩላቸው ሀገር የሚገነባው በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመሆኑ ምርጫ ለሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀው ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ አግባብ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ።

በአለማየሁ አበበ ።
ፎቶ :- በያብስራ ተክሌ ።

Address

Dire Dawa
3000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Government Communication Affairs Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share