Dire Dawa Mayor office management

Dire Dawa Mayor office management Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Dawa Mayor office management, Government Organization, finance, Dire Dawa.

03/12/2024
20/10/2023
20/10/2023

የመደመር ዕሴቶች በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ላይ እንዲገቡ የምንፈልጋቸዉን ዕሴቶች ታሳቢ ያደረጉ ጥልቅ ዕሴቶች ናቸዉ። እነዚህ እሴቶች የመደመር ምሰሶዎች ናቸዉ። ዕሴት ማለት ለነገሮች የምሰጠዉ አንጻራዊ ዋጋና ሁኔታዎችን የምንመዝንበት መስፈርት ማለት ሲሆን ይህም መስፈርት ጥልቅ ወይም ዝርዝር ሊሆን ይችላል።

የመደመር ዕሴቶች ከብቸኝነት ጉድለት ለመዉጣትና ክሡትነትን እያረጋገጡ ለመሄድ እንችል ዘንድ ቅድሚያ የምንሰጣቸዉ ጥልቅ ጉዳዮች ናቸዉ።

ከመደመር ዕሴቶች መካከል አንዱ ሀገራዊ አንድነት ነዉ። ሀገራዊ አንድነት ማንነታችን እንዳይለያይ ሆኖ የተጋመደ፣ የሰናሰለ እና የተዋሐደ መሆኑን አመላካች ነዉ። የሀገራችን ብሔሮች ዕጣ ፋንታ በጋራ ለማደግ የተሠራ ብቻ እንጂ ተለያይተን ወይም ተነጣጥለን ሉዓላዊ ሀገር ሆነን፤ ነጠላ ህልዉናችንን አስጠብቀን በሰላም መቆየት አንችልም።

ሀገራዊ አንድነታችን የምርጫ ብቻ ሳይሆን የህልዉና ማስጠበቂያ ጉዳይ ጭምር ነዉ።
ሌላኛዉ የመደመር ዕሴት የዜጎች ክብር ነዉ። የዜጎች ክብር ኢትዮጵያውያን በሀገር ዉስጥም ይሁን በዉጪ ሀገር ክብራቸዉ ተጠብቆና ሀገራቸዉን መከታ አድርገዉ እንዲኖሩ ቅድሚያ ሰጥቶ የመስራት ፍላጎት ነዉ።

ክብርእና የጋራ ጥቅምን የማስጠበቅ መርሕ ነዉ። ሰዎችን ሁል ጊዜም ወደ ግብ መቅረቢያ መንገድ ሳይሆን ራሳቸዉ ግቦች እንደሆኑ የማመን ዕሴት ነዉ። የሰዎች ክብር በሁሉም ሰብዓዊ ፍጡር፣ በቡድን እና በግለሰብ ደረጃ ሊታይ ይችላል።

ሌሎች ማንኛዉም ዕሴቶች የሰዎችን ክብር የሚያረጋግጡ መሆን አለባቸዉ። በሥራዎቻችን ሁሉ ዜጎችን አክብሮ ማገልገል፣ በማንኛውም ጉዳይ ላይ በክብር ማማከርና መያዝ ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ። መደመር ከዚህ አንጻር ዘረኝነትንና ጎጠኝነት በማስወገድ ሰዉ ሰዉ በመሆኑ ብቻ ክብሩና ነጻነቱ እንዲከበር ዘብ መቆም ማለት ነዉ። መደመር በዚህ ጊዜ ግለሰባዊ ነጻነቱ ማኅበረሰባዊ ድኅንነትን ማቀንቀን ይሆናል።

ከሌሎች ዕሴቶች ጋር እጅግ የተሳሰረዉ ሌላዉ የመደመር ዕሴት ብልጽግና ነዉ። ብልጽግና የዜጎች ሥጋዊ፣ የስምና የነጻነት ፍላጎቶች በቀጣይነት ማሟላት እንዲችሉ አቅማቸዉን ማሳደግ ነዉ። ብልጽግና የሰዉ ልጅ ሥጋዊ ፍላጎቶች የሆኑትን የምግብ፣ የመጠጥ፤ የልብስ፣ መጠለያ፤ የጤና፣ የትምህርትና የንጽሕና አገልግሎቶችን አሟልቶ ማግኘት ነዉ።

በተጨማሪም የሰዉ ልጆችን ቀጣይነትና አስተማማኝነት ያለዉ ነጻ የምርጫ አድማስ በማስፋት የዜጎችን ደስተኝነት ማረጋገጥ ነዉ።

ዶ/ር አብይ አህመድ
መደመር መፅሃፍ ገፅ 47 – 48

20/01/2023

ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ለሀገረ መንግስት ግንባታዉ ከፍተኛ ፋይዳ ኣለዉ።

ህብረ ብሔራዊ ሀገራዊ አንድነት እየተጠናከረ ሊሄድ የሚችለው ደግሞ የብሔር ማንናት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀው ሲጓዙ ነዉ።

የብሔር፣የቋንቋ፣የባህል፣የሃይማኖት፣የፖለቲካ አመለካከት ወዘተ..ብዝሃነት በገነባት ኢትዮጵያ ሚዛናዊነትን ያረጋገጠ ፣ከፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ተግባር የተጠበቀ የፖለቲካ እሳቤን ባህል ማድረግ ኢትዮጵያን ለማፅናት መሠረት ነዉ።

ፅንፈኛ አስተሳሰብ እና ድርጊት ሚዛናዊነትን በማዛባት፣አካታችነትን በማሳሳት ወደ አግላይነት ያሸጋግራል ።

አግላይነት ወደ ጠቅላይነት በማምራት ብዝሃነትን ለመቀበል፣ለማክበር እና ለማስተናገድ ተግዳሮት ይሆናል።በዚህም መነሻ ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባቱን ዕድል ይፈትነዋል።

ብልጽግና ፓርቲ የብሔር ማንነት እና ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያዊ አንድነት ሚዛናቸዉን ጠብቀዉ እንዲራመዱ በማድረግ በሂደቱም ጠንካራ አገረ መንግስት መገንባትን መሠረት አድርጎ እየሠራ ይገኛል ።

ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የምትመች፣ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ያበበባት አገር እንድትሆን ብልጽግና ተግቶ ይሠራል ።

ሚዛናዊ የፖለቲካ እይታ መርህ ሁሉንም ብዝሃነቶች የማስተናገድ የመሀል የፖለቲካ አስተሳሰብና ተግባር ነዉ።

ፅንፈኝነት ኢትዮጵያን ከማዳከም ያለፈ ዉጤት እንደማያስገኝ ከዚህ በፊት የፈተኑንን ችግሮች ዞር ብሎ በማየት መገንዘብ እንችላለን። የዘርፈ ብዙ ፀጋዎች ሀገር ኢትዮጵያ ሚዛናዊ የፖለቲካ እይታ መርህን እና ሙሉዕ እይታን በማጠናከር የለዉጥ ጉዞዋን እንድታፋጥን የዜግነት አደራ አለብንና የየበኩላችንን እናበርክት ።

18/01/2023

''በዋናዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በየደረጃው በሚገኘው አመራራችን መካከል ወጥነት ያለው የአመለካከትና የተግባር አንድነት በመፍጠር የጀመርነውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ከዳር ለማድረስ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጠናክር እንዲሁም ለረጅሙ ጉዞአችን ስኬት እንቅፋት የሚሆንብንን የትኛውንም አይነት የጽንፈኝነት አመለካከት የፓርቲያችን መርሆዎች ላይ በመቆም ከምንጩ ለማድረቅ መትጋት ይኖርብናል " -አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ

በብልፅግና ፓርቲ አዘጋጅነት በድሬ ዳዋ አስተዳደር አና በሀረሪ ክልል ለሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሁለት ቀናት በሀረር ከተማ ሲካሄድ የነበረው የውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

የመድረኩን መጠናቀቅ አስመልክቶ በብልጽግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የፓርቲ ሀላፊው በመግለጫቸውም በተካሄደው የአመራር የውይይት መድረክ በአገር ደረጃ የተጀመረው የሠላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ ሂደት እንዲጠናከር አመራሩ ሚናውን በላቀ ደረጃ አንዲወጣና አሁን ላይ እንደሀገር ያጋጠሙንን ችግሮች በጠንካራ የአመለካትና የተግባር አንድነት እና ቀጣይነት ያለው ውጤት በማስመዝገብ ህዝብንና ሀገርን በጋራ ማሻገር እንደሚጠበቅብን አምነን በትጋት ብቁ አመራር መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል በተለይም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና በሐረሪ ክልል ያለውን ሰላም እንዲጠናከር፤ የህዝቦች ተጠቃሚነት እና ትስስር እንዲጎለብት በቁርጠኝነት በመንቀሳቀስ ስኬታማ መሆን አለብን ብለዋል።

ለሁለት ቀናት በተካሄደው የአመራር ውይይት የሰላምና የጸጥታ ችግሮችን በጋራ ታግሎ በማስወገድ ለዘላቂ ልማትና ብልጽግና በጋራ መቆም የሚያስችል የተሻለ ግንዛቤ መያዙን የገለጹ ሲሆን የጠራ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት በመያዝ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት አመራሩ የወንድማማችነትና እህትማማችነት መንፈስን በማጠናከር ርብርብ በማድረግ ብልሹ አሠራርን እንዲሁም ጽንፈኝነትን በጽናት መታገል እንደሚገባ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

በመጨረሻም አንዳንድ ሀይሎች በፖለቲካ ገበያ ትርፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን እኩይ ተግባር እና የጽንፈኝነት እንቅስቃሴን በመታገል የሀገራችንን የብልጽግና ጉዞ በማስቀጠል የትኞቹም መሰናክሎች ከጀመርነው መንገድ የማያናጥቡን መሆኑን በመረዳት የአመራርነት ሚናችንን በብቃት መዋጣት ተገቢ መሆኑን አሳስበዋል፡፡ተመሳሳይነት ያላቸው የውይይት መድረኮች ወጥነት እና ተከታታይነት ባለው መልኩ ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

18/01/2023

ለመላው የአስተዳደርራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ እያልን በዓሉ የሰላም የፍቅር እንዲሆንልን እየተመኘን በዓሉን ስናከበር ሀይማኖታሚ ስረዓቱን በጠበቀ መልኩ እንድናከብር ጥሪያችን እናስተላልፋለን ...በመረዳዳት በመደጋገፍ አንዳችን ለአንዳችን በመተሳሰብ በዓሉ የደስታ እንዲሆን እንመኛለን።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት

18/01/2023

Address

Finance
Dire Dawa
3000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Mayor office management posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share