Federal Ethics and Anti-Corruption Commission Dire Dawa Branch

Federal Ethics and Anti-Corruption Commission Dire Dawa Branch Let's Fight Corruption Together

ለሀገር መከላከያ ክብር ሁሌም እንቆማለን
17/11/2020

ለሀገር መከላከያ ክብር ሁሌም እንቆማለን

ኮሚሽኑ የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሃብት ሊመዘግብ ነው--------------------------------------------------------ፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ...
11/08/2020

ኮሚሽኑ የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሃብት ሊመዘግብ ነው
--------------------------------------------------------
ፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የሁሉንም መንግስት ሰራተኞች ሀብት ሊመዘግብ ነው፡፡ የሀብት ምዝገባ ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል ሥልጠና ከሐምሌ 30-ነሃሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ለ 40 የሥነምግባር መኮንኖች ተሰጥቷል፡፡
ሀብትን ማሳወቅና ማስመዝገብ የመንግሥት አሠራርን በግልጽነትና በተጠያቂነት ላይ ለመመስረት፤ ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል፤ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነትና የግል ጥቅም ሳይቀላቀሉ በየራሳቸው መንገድ የሚመሩበትን ግልጽ ሥርዓት በመዘርጋት ሊፈጠር የሚችለውን የጥቅም ግጭት ለማስወገድ እንደሚረዳ ይታወቃል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የሁሉንም የመንግስት ሰራተኞች ሀብት መመዝገብ ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያቶች እያደገ ከመጣው የመንግስት በጀትና ሀገራዊ ዕድገት ጋር የተጣጣመ የፀረ-ሙስና ትግል ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱና ለዚህ ደግሞ የሀብት ምዝገባ ሥራ ዋነኛ ከሚባሉት የሙስናና ብልሹ አሰራሮች መከላከያ መንገዶች ውስጥ አንዱ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኮሚሽኑ በሀብት ምዝገባው ዘርፍ ልምድ እየቀሰመና አቅሙን እያሳደገ በመምጣቱ የሀብት ምዝገባው ሥራ በተሟላ መንገድ ማስኬድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

የመንግስት ባለስልጣናት እስከ ሰኔ 30 ሀብታቸውን እንዲያሳውቁ ተጠየቁ  የፌደራል እና የድሬዳዋ አስተዳደር ተመራጮች፣ተሿሚዎችና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እስከ 30 ቀን 2012 ድረስ እን...
27/06/2020

የመንግስት ባለስልጣናት እስከ ሰኔ 30 ሀብታቸውን እንዲያሳውቁ ተጠየቁ

የፌደራል እና የድሬዳዋ አስተዳደር ተመራጮች፣ተሿሚዎችና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች እስከ 30 ቀን 2012 ድረስ እንዲያሳውቁ የፌደራል ስነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሸን ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ጠይቋል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ የሀብት ምዝገባ ያላከናወኑ ባለስልጣናት እና አመራሮች ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ኮምሽኑ አስታውቋል። የሀብት ማሳወቅና ማስመዝገብ አዋጅ አንቀፅ 4 ንዑስ አንቀፅ 1 ማንኛውም ተሿሚ በራሱና በቤተሰቡ፣ባለቤትነት ወይም ይዞታ ሥር የሚገኝ ሀብትና የገቢ ምንጮች የማሳወቅና የማስመዝገብ ግዴታ አለበት ይላል።

09/06/2020

የመንግስት ተሿሚዎችና የህዝበ ተመራጮችን ሃብት መዝግቦ ለህዝብ ክፍት የሚሆንበትን አሰራር እየዘረጋ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመንግስት ተሿሚዎችና የህዝበ ተመራጮችን ሃብት መዝግቦ ያለ ገደብ ለህዝብ ክፍት የሚሆንበትን አሰራር እየዘረጋ መሆኑን የፌዴራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ፥ የዘመናዊ ሃብት ምዝገባ መረጃ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረጉን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

ስርዓቱ ከዚህ ቀደም በማኑዋል የነበረውን አሰራር ወደ ዲጂታል የሚቀይር መሆኑም ተነግሯል።

እንዲሁም ከዚህ ቀደም እስከ ሁለት ወር ይፈጅ የነበረን የምዝገባ ሂደት ተመዝጋቢው ባለበት ሆኖ በሁለት ደቂቃ ማከናወን የሚያሰችለው መሆኑ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የሃበት ማሳወቅ እና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይ እንደተናገሩት፥ የተዘረጋው ስርአት ኮሚሽኑ የተመዘገበውን መረጃ ለሀብረተሰብ ለማሳወቅና ተደራሽ ለማድረግ ከጊዜና ከወጪ እንዲሁም ከርቀት አንጻር የነበረበትን በርካታ ችግር ይፈታል።

እስካሁን ባለው ከሱማሌ እና አፋር ክልል ውጪ 500 ሺህ የሚደርሱ ተሿሚ፣ ተመራጭና የሚመለከታቸው አካላት ሃብታቸውን ያስመዘገቡ ሲሆን ወደ መረጃቸው አዲሱ ስርዓት እንዲገባ እየተደረገ ነው መሆኑንም በመግለጫው ተነስቷል።

አዲሱ አሰራር የምዝገባ ሂደትን ከማቅለል በተጨማሪ የመንግስት ተሿሚዎችና የህዝበ ተመራጮችን ሃብት ለህዝብ ክፍት የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል።

በሀይለኢየሱስ ስዩም



የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው

06/06/2020

የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከሀሮማያ Fm 94.8 ጋር በመተባበር የሚያስተላልፈው የትምህርት ፕሮግራም በአማርኛ ስኞ/10:10 - 10:35 ሰዓት በአፋን ኦሮሞ እሮብ/ 5:00 - 5:20 ሰዓት ይከታተሉ

Address

Dire Dawa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251251125268

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Federal Ethics and Anti-Corruption Commission Dire Dawa Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Federal Ethics and Anti-Corruption Commission Dire Dawa Branch:

Share