የሥራና ክህሎት ቢሮ-ድሬዳዋ

የሥራና ክህሎት ቢሮ-ድሬዳዋ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ

🌏✈️ የውጪ ሀገር የስራ ማስታወቂያ🚀 በህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በተለያዩ ዘርፎች የሰው ኃይል ይፈለጋል። የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ...
04/06/2026

🌏✈️ የውጪ ሀገር የስራ ማስታወቂያ
🚀 በህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ፕሮግራም በተለያዩ ዘርፎች የሰው ኃይል ይፈለጋል። የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም በማስጠበቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ውጪ ሀገር ለመስራት የሚፈልጉ አመልካቾች እንዲያመለክቱ እናሳውቃለን።
🚧 የሞያ ዘርፎች፦
🔹የጥበቃ ሰራተኛ
🔹ፅዳት ሰራተኛ
🔹አጠቃላይ ረዳት
🔹የሲቪል ግንባታ ረዳት
🔹የኮንስትራክሽን ዕለታዊ ሰራተኛ / ረዳት
🔹ኤሌክትሪሻን / የኤሌክትሪክ ባለሙያ
🔹ቧንቧ ሰራተኛ / የቧንቧ ባለሙያ
🔹የኤር ኮንዲሽነር ባለሙያ
🔹ብየዳ ሰራተኛ / የብየዳ ባለሙያ
🔹የእሳት አደጋ መከላከያ ባለሙያ
🔹ግንብ ሰራተኛ / የድንጋይና ጡብ ግንባታ ባለሙያ
🔹ቀለም ቀቢ
🔹ምርጋትና ልስን ሰራተኛ
🔹የጂፕሰም ባለሙያ
🔹የፎርምወርክ አናጺ / የማገር አናጺ
🔹የአሉሚኒየም ስራ ባለሙያ
🔹ላሚኔተር / የላሜራ ስራ ባለሙያ
🔹ማጠናቀቂያ ስራ ባለሙያ
🔹የብረት መዋቅር ሰራተኛ
🔹ስካፎልዲንግ ሰራተኛ
🔹ሪገር እና ምልክት ሰጪ
🔹የመጋዘን እቃ አሰናጅ
🔹የፋብሪካ ሰራተኛ
🔹የጭነት አውራጅና ጫኝ ሰራተኛ
🔹የሞተር/ሳይክል አሽከርካሪ
🔹የሲቪል ፎርማን / የሳይት ተቆጣጣሪ
🔹የሲቪል ረዳት ፎርማን / የቡድን መሪ
✅ ለመመዝገብ
Labor ID ካሎት ይህን https://forms.lmis.gov.et/uae-new-2/ ማስፈንጠሪያ ተጠቅመው መመዝገብ። Labor ID ከሌሎት የሚከተሉትን ሂደቶች ይከተሉ፦
1. በ lmis.gov.et ይመዝገቡ።
2. በአቅራቢያዎ ባለ የአንድ ማዕከል (ወረዳ ወይም ቀበሌ) በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ ይስጡ እና የሰራተኛነት መለያ ቁጥር (Labor ID) ይያዙ።
3. Labor ID ካገኙ በኋላ በተሰጠው የማመልከቻ ማስፈንጠሪያ ገብተው መረጃዎትን በትክክል ሞልተው ያመልክቱ።

E-LMIS የርቀት (Remote) የሥራ ዕድሎችን የሚያገኙበትን ዕድል አመቻችቶልዎታል። የዲጂታሉ ዓለም የሥራ ዕድሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየደጉ ነው። አሁን ላይ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ከሀገር...
02/06/2026

E-LMIS የርቀት (Remote) የሥራ ዕድሎችን የሚያገኙበትን ዕድል አመቻችቶልዎታል።

የዲጂታሉ ዓለም የሥራ ዕድሎች በከፍተኛ ሁኔታ እየደጉ ነው። አሁን ላይ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ከሀገር ሳይወጡና ድንበር ሳይገድባቸው ዓለም አቀፍ የሥራ አማራጮችን E-LMIS ላይ ማግኘት ይችላሉ።

እንደ Data entry, IT support ያሉ ክህሎቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሙያዎች ባለቤት ከሆኑ ቤትዎ ሆነው ዶላር ለመሥራት ብሎም አለም አቀፍ ተከፋይ ለመሆን ላፕቶፕዎ(Laptop) ብቻ በቂ ነው።

ዛሬውኑ ይጀምሩ፦ ወደ E-LMIS ፖርታል በመግባት የርቀት(Remote) እና የፍሪላንስ (Freelance) የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ ይሁኑ !

We can/ይቻላል !

#ይቻላል

30/05/2026
28/05/2026
E-LMIS  ሥራ ፈላጊዎችን ለመመዝገብ ብቻ ሳይሆን ከምዝገባ ባለፈ የበርካታ  ተጨባጭ  ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ታልሞ የተነደፈ ሰፊ መድረክ ነው ። በE-LMIS ከሚያገኟቸው ዕድሎች መካከል...
28/05/2026

E-LMIS ሥራ ፈላጊዎችን ለመመዝገብ ብቻ ሳይሆን ከምዝገባ ባለፈ የበርካታ ተጨባጭ ዕድሎች ተጠቃሚ ለማድረግ ታልሞ የተነደፈ ሰፊ መድረክ ነው ።

በE-LMIS ከሚያገኟቸው ዕድሎች መካከል ፦
📍 የሀገር ውስጥ ሥራዎችን ፦ በሀገር ውስጥ ያሉ ክፍት የስራ ቦታዎችን በቀላሉ ለማግኘት
✈️ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድሎች፦ ህጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የውጭ ሀገር ሥራ ለማመልከት
🏠 የርቀት (Remote) ሥራዎች፦ ከቤት ወይም ካሉበት ሆነው የሚሰሩባቸውን የስራ ዕድሎች ለማግኘት
🆔 የሰራተኛ መለያ (Labor ID)፦ የራስዎን ይፋዊ የዲጂታል የሥራ መለያ ለመያዝ
🤝 ታማኝ አሰሪዎች፦ በመንግስት ከተረጋገጡ ድርጅቶች ጋር በቀጥታ ለመገናኘት
🔔 የሥራ ጥቆማዎች፦ አዲስ የሥራ ማስታወቂያ ሲወጣ ወዲያውኑ በስልክዎ መልዕክት ለመቀበል

የእነዚህን እና የሌሎች በርካታ ዕድሎች ተጠቃሚ ለመሆን ዛሬውኑ ይመዝገቡ ሁሉንም በአንድ ቦታ ያግኙ !

We can/ይቻላል !

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1447ኛ ዓመተ ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው...
26/05/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ለ1447ኛ ዓመተ ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዓሉ የፍቅር፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆንም ተመኝተዋል!

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ!!

በአስተዳደሩ ለሚገኙ አምስት የግል እና ሶስት የመንግስት ኮሌጆች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የድጋፍና ክትትል እና ጥራት ቁጥጥር አደረጃጀቶችን የሚያጠናክር የአቅም ግንባታ መድረክ ተዘጋጀ፡፡ይህም...
25/05/2026

በአስተዳደሩ ለሚገኙ አምስት የግል እና ሶስት የመንግስት ኮሌጆች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የድጋፍና ክትትል እና ጥራት ቁጥጥር አደረጃጀቶችን የሚያጠናክር የአቅም ግንባታ መድረክ ተዘጋጀ፡፡

ይህም የአቅም ግንባታ መድረክ ኮሌጆች በድጋፍና ክትትል እና በጥራት ቁጥጥር ቡድን ተዋቅረው እያካሄዱ የሚገኝ ሲሆን በይበልጥ በቀጣይነትም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅና ለማረጋገጥ ውስጣዊ አቅም የሚያጎለብት መሆኑም ታውቋል፡፡

በዚህም በየተቋማቱ የሚካሄደው የስልጠና ፕሮግራም ሁሉም አሰልጣኝ መምህራን የሚሰጡት ስልጠና በዕቅድ ላይ ተመስርተው ስለመስጠታቸው፤ እያንዳንዱ የስልጠና ፕሮግራም በተቀመጠው መመሪያና አላማ መሰረት እየተሰጠ ስለመሆኑ በተያያዘም ለስልጠና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች መሟላታቸውንና የስልጠና ቦታዎች አመቺነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሚደረግ ይሆናል፡፡

የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ

‘ፈልጉልኝ’፤ ብቁ ባለሙያዎችን ለአሠሪዎች፣ ፍትሃዊ የሥራ ዕድል ለሁሉም ዜጎች!የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አካል የሆነና አሠሪና ሠራተኞችን በቀላሉ ማገናኘት የሚያስችል ‘ፈልጉልኝ’...
25/05/2026

‘ፈልጉልኝ’፤ ብቁ ባለሙያዎችን ለአሠሪዎች፣ ፍትሃዊ የሥራ ዕድል ለሁሉም ዜጎች!

የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አካል የሆነና አሠሪና ሠራተኞችን በቀላሉ ማገናኘት የሚያስችል ‘ፈልጉልኝ’ የተሰኘ ሀገራዊ ዲጂታል መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስመርቀን ወደ ሥራ አስገብተናል።

በመርሃ ግብሩ ‘ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030’ ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ የመጪውን ዘመን የሥራ ገበያ መልክ እና የሰው ሠራሽ አስተውሎትን መሰረት ያደረጉ ዲጂታል መተግበሪያዎች በሀገራዊ ልማት ውስጥ ያለውን ሚና በጥልቀት ያየንበት ውጤታማ የፓናል ውይይትም አካሂደናል።

ወደ ሥራ የገባው ይህ ዲጂታል መተግበሪያ፤ በሀገራችን ምጣኔ-ሀብት ውስጥ በሥራ ገበያው ውስጥ ያለውን የመረጃ ክፍተት በመቅረፍ ሥራ ፈላጊ ዜጎችንና አሠሪዎችን ካሉበት ሆነው በቀጥታ የሚያገናኝ ዘመናዊ የሥራ ሥነ-ምህዳር ነው።

መተግበሪያው መደበኛ ያልሆነውን የሥራ ዘርፍ ወደ መደበኛ የኢኮኖሚ ሥርዓት ከማሸጋገሩም በላይ፣ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ ቀረጻን በማገዝ እና አስተማማኝ የመረጃ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ አኳያም ሚናው የላቀ ነው። ከሁሉ በላይ በቴክኖሎጂ አማካኝነት የሥራ ገበያውን ትክክለኛ ፍላጎት በማሳየት፣ የትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የሥራ ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል እንዲያፈሩ ስልታዊ አስተዋጽኦም ያበረክታል።

ይህንን ዘመናዊ መተግበሪያ እውን በማድረግ ሂደት ሚና ለነበራችሁ አካላት በሙሉ ያለኝ ልባዊ ምስጋና የላቀ ነው።

የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!

Address

Close By Triangle Hotel
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሥራና ክህሎት ቢሮ-ድሬዳዋ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share