Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau

Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau, Government Organization, dire dawa mariam sefer, Dire Dawa.

ግንቦት 18/2018                                             ኢድ ሙባረክ!የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች ፣ ሰራተኞችና ተገልጋ...
26/05/2026

ግንቦት 18/2018
ኢድ ሙባረክ!
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች ፣ ሰራተኞችና ተገልጋዮች በሙሉ
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ቢሮ ለመላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎችና ለእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች እንኳን ለ1447 ዓ/ሂ ኢዲ አልአደሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብና ሐይምኖታዊ ተልዕኮዎችን የማታሳኩበትና መልካምተግባራትን የምትፈጽሙበት በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
የቢሯችን ራዕይ በአስተዳደራችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የማስፈፀም አቅም ጎልብቶ ጥራት ያላቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰረተ ልማት ውጤቶች ተስፋፍተው፣ የቤቶች ልማት ውጤቶች አቅርቦት ተደራሽነት ተረጋግጦና ሌሎችም የግንባታ ውጤቶች ለአስተዳደሩ ነዋሪዎች ምቹ ሆነው ማየት ነው፡፡
ይህንም የቢሯችንን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካትም በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን ዕውቀትና ክህሎት ለማዳበር አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተወዳደሪነታቸውን የሚያሳድጉ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመስራት አበራታች ውጤቶችን በማስመዝግብ ላይ ይገኛል፡፡
የ2018 ኢዲ አልአደሃ አረፋ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና ሃይማኖቱ የሚያዘውን መልካም ተግባር ሁሉ የምትፈጽሙበት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችንን በድጋሜ እናስተላልፋለን፡፡ ኢድ ሙባረክ!

18/05/2026

ግንቦት 11/2018
ማስታወቂያ
ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች በሙሉ
በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ጋር በተደረገ ውይይት ከተማ የማደስ ፣ የአረንጓዴ ልማትና የቅድመ መደበኛ ልጅነት ዕድገት ፕሮጀክት ለመተግበር በስምምነት ላይ መድረሳችን ይታወቃል፡፡ ከፕሮጀክቱ ትግበራ ጋር በተያያዘም የተለያዩ ህገ ወጥ ግንባታዎች መኖራቸውንና መፍረስ ያለባቸው መሆኑንም ተነጋግረን በስምምነት ላይ መድረሳችን ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ህገ ወጥ ግንባታዎችን የገነባችሁ ነዋሪዎች ከዛሬ ግንቦት 11/2018 ጀምሮ እስከ ግንቦት 14/2018 ድረስ ግንባታዎቹን እንድታፈርሱ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡ ይህ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ሶስት ቀን ውስጥ ባልፈረሱ የህገ ወጥ ግንባታ ባለቤቶች ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የመንግስት ህንፃዎችና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ግንቦት 10/ 2018የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ህንፃዎችና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከካራማራ ሳይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡የካራማራ ሳይት የጋ...
18/05/2026

ግንቦት 10/ 2018
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ህንፃዎችና ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከካራማራ ሳይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
የካራማራ ሳይት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ነዋሪዎች ጋር የተካሄደውን የውይይት መድረክ በንግግር ያስጀመሩት የመንግስት ህንፃዎችና ቤቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ ሙሳ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሩም የመድረኩንአላማና አስፈላጊነት ከተናገሩ በኋላ ውይይቱ የሚደረገውም በካራማራ የጋራመኖሪ ቤቶች ሳይት ግቢ ውስጥ በሚተገበረው የቅድመ መደበኛ ልጅነት ዕድገት፣ የከታማ ማደስና የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በፕሮጀክቱ አተገባበርና በነዋሪዎች ተሳትፎ ላይ ውይይት ከተካሄደ በኋላም ከካራማራ ሳይት የጋራ መኖሪያ ማህበር አመራሮች ጋር የመግባቢ ሰነድ የፊርማና የሰነድ ርክክብ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡

ግንቦት 7/2018የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለፉት አራት ዓመታት በቤቶች ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶችበ2003ዓ.ም. ጀምሮ የፌደራል መን...
15/05/2026

ግንቦት 7/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባለፉት አራት ዓመታት በቤቶች ልማት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶች
በ2003ዓ.ም. ጀምሮ የፌደራል መንግስት የቤት ልማት ቦንድ ብድር ምችችት ካቋረጠ በኋላ በከተማችን ውስጥ የሚስተዋለውን የመኖሪያ ቤት የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ የድሬዳዋ አስተዳደር ካለው ውስን ካፒታል 203 ሚሊዬን ብር በመመደብ በመጀመሪያ ምዕራፍ በኢንዱስትሪ ቁጥር 2 የተጀመሩ 358 (72 ስቱዲዮ ቤቶች፤ 105 ባለአንድ መኝታ፤ 70 ባለሁለት መኝታ፤ 70 ባለሶስት መኝታእና 41 ሱቅ) የጋራ መኖሪያ ቤቶች የማጠናቀቅና የማስተላለፍ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡ በዚህም 317 አባወራ/እማወራ 20 እና 30 በመቶ የመንግስት ሠራተኞችንና ሴቶችን በቅድመ ተከተል የቤት ባለቤት ባደረገ አሰራር ፍትሐዊ የሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ሶፍትዌር ሲስተም በመጠቀም በማስተላለፍ በድምሩ 1,585 የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል ከተገነቡት የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል 41 ሱቆች በጨረታ ለአሸናፊዎች እንዲተላለፉም ተደርጓል፡፡
በዚህ የ358 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታም 310 አባላት ለ54 ማህበራት፤ 42 አባላት ለ10 ስራ ተቋራጮች እንዲሁም በማህበራቱና በስራ ተቋራጮች ስር ለ1,028(893 ወንድና 135 ሴት) ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ በተመሳሳይ በከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ የሁለተኛው ዙር የኢንዱስትሪ መንደር ቁጥር 2 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን በማስጀመር 548 ቤቶች (48 ስቱዲዮ፤ 211 ባለ አንድ መኝታ፤ 132 ባለ ሁለት መኝታ፤ 141 ባለ ሶስት መኝታ እና 16 ሱቅ) ተገንብተው እንዲጠናቀቁ ተደርጓል፡፡ በዚህም የቅድመ ማስተላለፍ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በዚህ 548 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ 15 ስራ ተቋራጮችና 32 ማህበራት የተሳተፉ ሲሆን በእነዚህ ስር ለወጣቶች ቋሚ(230) እና ጊዜያዊ( ለ1,152) የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
በሌላ በኩል የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ የሚቻለው በመንግስት ብቻ ሳይሆን በሌሎች የቤት ልማት አማራጮች ተግባራዊ እንዲሆኑ በማድረግ በህብረት ስራ ማህበራት ቤት ልማት ለ17 ማህበራት(ከ408 አባላት) ለአስተዳደሩ መምህራን መሬትና ወጪ ቆጣቢ መኖሪያ ቤት ዲዛይን ማዘጋጀትና ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ ስራ ተከናውኗል፤ የግል መኖሪያ ቤት ገንቢዎችን የማበረታታት ስራ ተሰርቷል፤ በሪልስቴት አልሚዎች በባለፉት 4 ዓመታት ከ1,000 በላይ መኖሪያ ቤቶች ተገንብተዋል፡፡ እንዲሁም lአንድ የመንግስትና የግል አጋርነት(PPP) ቤት ልማት ፍቃድ በመስጠት ወደ ቤቶች ግንባታ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በቀጣይ ዓመታት የሚገነቡ የ600 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቦታም ተዘጋጅቶ የግንባታ ቅድመ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

14/05/2026

በድሬዳዋ አስተዳደር የከንሰትራክሽን ዘርፍ የልማት ትሩፋቶች

ግንቦት 2018የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለፉት አራት ዓመታትበኮንስትራክሽን ዘርፍየኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋነኛ ተልዕኮ የዘርፉን ተዋናኞች አቅም በመገንባት ተ...
14/05/2026

ግንቦት 2018
የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለፉት አራት ዓመታት
በኮንስትራክሽን ዘርፍ
የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዋነኛ ተልዕኮ የዘርፉን ተዋናኞች አቅም በመገንባት ተወዳዳሪነታቸውን ባጎልበት ነው፡፡ የህን አላማና ተልዕኮ ለማሳካትም የተዋናዮችን ሙያዊ ብቃት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡
• በዋነኛነትም በህንጻው ዘርፍ የሚሰማራ 2,143 አነስተኛ እና መለስተኛ ባለሙያዎች የቅድመ-ምዘና ምዝገባ፣ በልዩ ልዩ ኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ 680 ባለሙያዎች የስራ ላይ (Training on job) እና በኢንዱስትሪው ስትራቴጂና ፖሊሲውና ቴክኖሎጂ ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ስለዘርፉ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፣ እንደዚሁም 73 መሪ መዛኞችን በማፍራት፤ 1,202 ባለሙያዎች የሙያ ብቃታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ፤ 643 ባለሙያዎች ከፍ ወዳለ ደረጃ በምዘና በማሳደግ፤ ብቃታቸውን በምዘና ላረጋገጡ 1,156 ባለሙያዎች የማረጋገጫ ሰርተፊኬት እንዲወስዱና ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡
• የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ዲዛይኖችን በማዘጋጀት፣ የግንባታ ፕሮጀክቶችን የክትትል፣ ድጋፍ እና ቁጥጥር ስራዎችን በማጎልበት ከዚህ በፊት በኮንስትራካሽን የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ያጋጥሙ የነበሩ ችግሮች እንዲቀረፉ ተደርጓል፡፡ ይህ ውጤት የተመዘገበውም ባለፉት አራት ዓመታት ለግንባታ ጥራት ትኩረት ተሰጥቶ የሚከተሉት ተግባራት ስለተከናወኑ ነው፡፡
1. በመንግስት በጀት ግንባታቸው ለሚከናወን 158 ግንባታ ፕሮጀክቶች እና 126 የጥገና ለሚሹ የመንግስት ተቋማት ዲዛይንና ስፔስፊኬሽን ዝግጅት፣ ለ120 ግንባታ ፕሮጀክቶች የጨረታ ሰነድ ለ114 የውል ሰነድ የማዘጋጀትና የጨረታ ሰነድ ግምገማ በማካሄድ ግንባታዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
2. ባለፉት 4 ዓመት ተኩል በመንግስት በጀት የሚገነቡ 284 ግንባታ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው በጀት፣ ጥራትና ጊዜ እንዲጠናቀቁ ክትትልና ቁጥጥር የተደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም 260 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
3. • የግንባታ ፕሮጀክቶች ምዝገባና የተዋናዮች ስራ አፈፃፀም ምዘና የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ለ139 የመንግስት ፕሮጀክቶች ምዝገና የተካሄደና የስራ ተቋራጮች አፈፃም ምዘና በማካሄድ በውጤት እንዲለዩ ተደርጓል፡፡ በዚህም የላቀ አፈፃፀም ያላቸውን ማበረታታትና ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡትን በአቅም ክፍተት የስራ ላይ ስልጠና እንዲወስዱና የመፈፀም አቅማቸው እንዲያድግ ተደርጓል፡፡

ግንቦት 03/2018የማሪያም ሰፈር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለነዋሪዎች ምቹ ፣ጽዱና ውብ እንዲሁም በቀድመ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮጀክት አተገባበርና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ውይይት ተካ...
11/05/2026

ግንቦት 03/2018
የማሪያም ሰፈር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለነዋሪዎች ምቹ ፣ጽዱና ውብ እንዲሁም በቀድመ ልጅነት እንክብካቤ ፕሮጀክት አተገባበርና የባለድርሻ አካላት ሚና ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
የውይየት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ኡመር ዱአሌ ሲሆኑ የጋራ መግባቢያ ሰነድ የፊርማና የርክክብ ሥነሥርዓትም ተካሄዷል፡፡ ከፕሮጀክቱ አተገባበርና በማሪያም ሰፈር የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎችና ለቀረቡ አስተያየቶችም ምላሽ መሰጠቱ ታውቋል፡፡

ሚያዚያ 30/2018ለድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የፓርቲው የቀጣይ አምስት ዓመታት የምርጫ ማኒፌስቶ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡...
08/05/2026

ሚያዚያ 30/2018
ለድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ አባላት የፓርቲው የቀጣይ አምስት ዓመታት የምርጫ ማኒፌስቶ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ስልጠናውን የሰጡት ምክትል የቢሮ ሃላፊ እና የቢሮው የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢማጅ አብደላ ሲሆኑ እሳቸውም የስልጠናውን አስፈላጊነት አስመልክተው ሲናገሩ ስልጠናው ያስፈለገው የአባላቱን ግንዛቤ በማዳበርና የፓርቲያችንን የምርጫ ማኔፌስቶ በአግባቡ በመረዳት የሚጠበቅብንን ሃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ዝግጁነት እንድንፈጥር ነው ብለዋል፡፡

ሚያዚያ 26/2018እንኳን ለ85ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል አደረሳችሁ፡፡ሚያዚያ 27 የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል ሲሆን ፋሺስት ጣሊያን አገራችንን ለአምስት ዓመታት ወርሮ ከቆየ በ...
04/05/2026

ሚያዚያ 26/2018
እንኳን ለ85ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል አደረሳችሁ፡፡
ሚያዚያ 27 የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል ሲሆን ፋሺስት ጣሊያን አገራችንን ለአምስት ዓመታት ወርሮ ከቆየ በኋላ፣ በጀግኖች አርበኞች ተጋድሎና መስዋዕትነት ድል ተመትቶ የወጣበትና የኢትዮጵያ ነፃነት የተመለሰበት ታላቅ የድል ክብረ በዓል ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነታችንን ስናስከብር የኖረን በጀግኖቻችን በከፈሉት የህይወት መስዋዕትነት ሲሆን የአሁኑ ትውልድ የአገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብረው ግን የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብራችንንና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ብቃታችንን በማሳደግ ስለሆነ ሁላችንም በተሰማራንበት የሥራ ዘርፍ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ የአገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ እንደጥንቶቹ ቅድመ አያቶቻችን ታሪክ መስራት ይኖርብናል፡፡ የአሁኑ ትውልድም ያንን በደም የተጠበቀ ነጻነት የተሟላ ለማድረግ እና ሀገራዊ ሕልውናን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆምና ከጥገኝነት ለመላቀቅ ወደ አዲስና ሁለንተናዊ የሽግግር ጉዞ መግባት ይጠበቅብናል በማለት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።እንኳ 85ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ መልካም የድል በዓል!!

እንኳን አደረሳችሁ፡፡ለድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች፣ ሰራተኖችና  ተገልጋዮች በሙሉእንኳን ለዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የዘንድሮው...
30/04/2026

እንኳን አደረሳችሁ፡፡
ለድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አመራሮች፣ ሰራተኖችና ተገልጋዮች በሙሉ
እንኳን ለዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ የዘንድሮው የዓለም አቀፉ የሰራተኖች ቀን የሰላም ፣የምርታማነትና የውጤታማነት በዓል አንዲሆንላችሁ እየተመኘን፤ ከበዓል በኋላም የሥራ ሰዓታችንን በማክበርና በአግባቡ በመጠቀም ሰራተኞች ለአገራችን ዕድገትና ብልጽግና መረጋገጥ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንዘጋጅ እያልን በድጋሜ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን፡፡ መልካም የዓለም አቀፍ የሠራተኖች ቀን ይሁንላችሁ፡፡

Address

Dire Dawa Mariam Sefer
Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Urban Development and Construction Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share