Prosperity Party Dire Dawa - ብልፅግና

Prosperity Party Dire Dawa - ብልፅግና ይህ የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው። Prosperity Party Dire Dawa is the ruling political party in Dire Dawa, Ethiopia established in December 2019.
(35)

Having an overall objective of making Ethiopia a prosperous country, its values are dignity of the people, justice.

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መርጣለች ፤ የህዝብ ተሳትፎና የዲሞክራሲ ጉዞ​ምርጫ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታሪካዊ ፋይዳ አለው ።7ኛውን ...
02/06/2026

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ መርጣለች ፤ የህዝብ ተሳትፎና የዲሞክራሲ ጉዞ

ምርጫ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታዋን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታሪካዊ ፋይዳ አለው ።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮች ማልደው ተነስተው በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት ቀጣይ እጣ ፈንታቸውን እና ሀገሪቱን ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የሚመራውን መንግስት ለመምረጥ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመምረጥ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ምዝገባ ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን የድምፅ መስጠት ሂደቱ ላይም ሕዝቡ ያሳየው ተሳትፎ እጅግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ ነበር።

​የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የልማት ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፥ ህዝቡ በነፃነትና በንቃት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻውን ተወጥቷል።

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተስተዋለው የመራጮች ሰልፍ ህዝቡ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ያለውን ጽኑ ፍላጎት ያሳየበት ሆኗል። በተለይም የሴቶች፣ የወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑ ተስተውሏል።

ይህ ምርጫ ከፖለቲካዊ ውሳኔነቱ ባሻገር በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በማህበራዊ ልማትና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች ላይ ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት መሰረት የሚጥል ነው።

ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዷ በራሷ፥ የዲሞክራሲ ጉዞዋ ወደ ኋላ የማይመለስ መሆኑንና በትክክለኛ መስመር ላይ እየተጓዘች ለመሆኗ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።

እንኳን ደስ አላችሁእንኳን ደስ አለን“ኢትዮጵያ መርጣለች”“ድሬ መርጣለች”Hambalyo Hambalyo!Itooobiya Way Dooratay!Diridhaba Way Dooratay!
02/06/2026

እንኳን ደስ አላችሁ
እንኳን ደስ አለን
“ኢትዮጵያ መርጣለች”
“ድሬ መርጣለች”

Hambalyo Hambalyo!
Itooobiya Way Dooratay!
Diridhaba Way Dooratay!

02/06/2026

ኢትዮጵያ!🇪🇹
መርጣለች፤ ፀንታለች ፤ አሸንፋለች!

Itti Aanaan Waajjira paartii Badhaadhinaa damee dirree dhawaa fi Itti Gaafatamaan Roga Siyaasaa fi Qaadhimamaan paartii ...
01/06/2026

Itti Aanaan Waajjira paartii Badhaadhinaa damee dirree dhawaa fi Itti Gaafatamaan Roga Siyaasaa fi Qaadhimamaan paartii Badhaadhinaa Obbo Shaakir Ahammad, Aana 06 Buufata Filannoo Qafiiraa Hulaa Bahinsaatti arkamuun sagalee isaanii kennanii jiran.

Obbo Shaakir Yeroo sagalee kennanitti yaada laataniin filannoon dhimma Hegeree biyyaatiif murteeysaa tahe waan taheef Hawaasichi qaama biyya tana ni ceesisa jedhee amuuf sagalee isaa kennuun qooda gama isaa bahachuu akka qabu dhaaman.

Bulchinsa Aanaa 06 buufataalee filannoo 15 keeysatti Adeemsi sagalee kennuu gaggeeyfamaa jira.

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!የብልፅግና ፓርቲ ምክትል እንዲሁም የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻኪር አህመድ በወረዳ 06 በሚገኘው የኡላ በሂንሳ ቀፊራ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸው...
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል እንዲሁም የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻኪር አህመድ በወረዳ 06 በሚገኘው የኡላ በሂንሳ ቀፊራ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

​አቶ ሻኪር አህመድ ድምፅ በሰጡበት ወቅት ምርጫው የሀገራችንን የዲሞክራሲ እጣ ፈንታ የሚወስን በመሆኑ ማህበረሰቡ ባመነበት አካል ላይ ድምፁን እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል።

​በወረዳ 06 በሚገኙ 15 የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እየተካሄደ ይገኛል።

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በቀልአድ ክላስተር ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በቀልአድ ክላስተር ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

"ምርጫ ዜጎች የስልጣን ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ነው።"‎አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ‎የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ‎
01/06/2026

"ምርጫ ዜጎች የስልጣን ባለቤት መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ነው።"

‎አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ
‎የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ሰጡ።በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በሚወዳደሩበት በድሬደዋ አስተ...
01/06/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፃቸውን ሰጡ።

በዛሬው ዕለት እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በሚወዳደሩበት በድሬደዋ አስተዳደር ከተማና ገጠር ወረዳዎች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

‎ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!‎‎ከንቲባ ከድር ጅሃር ድምፅ ሰጡ፤ ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ መብቱን እንዲጠቀምም ጥሪ አቅረበዋል።‎‎​የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር በ7ኛው ጠቅላላ...
01/06/2026

‎ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

‎ከንቲባ ከድር ጅሃር ድምፅ ሰጡ፤ ህብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ መብቱን እንዲጠቀምም ጥሪ አቅረበዋል።

‎​የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጅሃር በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዛሬው ዕለት በግንባር ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።

‎ከንቲባው ድምፃቸውን የሰጡት በአስተዳደሩ ወረዳ 04 በሚገኘው ምርጫ ጣቢያ አንድ ነው።

‎​ከንቲባ ከድር ጁሃር ድምፅ በሰጡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ዜጎች በሕገ-መንግስቱ የተሰጣቸውን የመምረጥ መብት በአግባቡና በሃላፊነት ስሜት ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በአገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት መደረጉን የገለጹት ከንቲባው፤ መላው ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ፓርቲ ለመምረጥና የአገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ መራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች ሁሉ በሂደቱ ላይ በነቂስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

‎​በምርጫ ጣቢያው የነበረውን ድባብ በተመለከተም፤ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አዛውንቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማለዳውን ጀምሮ በሰላማዊ ሁኔታ ሰልፍ በመያዝ ድምፅ በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።


Kantiibaan bulchiinsa Dirree Dhawaa fi kaadhimamaan mana marii bakka bu'oota ummataa obbo Kadiir Juhaar aanaa 04 buufata filannoo giriik kaampii lakkoofsa 1'tti argamuun sagalee kennan.

Obbo Kadiir Yaada laataniin filannoon marsaa 7ffaa karaa seera qabeeysaafi naamusa qabuun gaggeeyfamaa jiraachuu kan taajjaban tahuu ibsanii jiran.

Address

Numberone
Dire Dawa
3000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity Party Dire Dawa - ብልፅግና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share