04/01/2026
# የመጨረሻ ማስታወቂያ #
!!አስቸኳይ ማስታወቂያ!!
ለጊዶሌ ነባር የከተማ ቦታ ጣሪያና ግድግዳ ግብር ከፋዮች ÷
ከተማ ሊዝ ቦታ ተጠቃሚዎችና ግብር ከፋዮች እንዲሁም ማስፋፊያ አከባቢ መሬት ያላቸው በሙሉ:-
የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ነባር የጣርያና ግድግዳ ግብር የ2018ዓ. ም ግብር ያልከፈላችሁ ÷
ከዚህ ቀደም በተለያዬ ዙር የሊዝ ቦታ በጨረታ ተወዳድራችሁ በማሸነፍ የሊዝ ቦታ ውል የገባችሁና ተደጋጋሚ ጥሪ የቀረበላችሁ የ2018 ዓመታዊ ጨምሮ ውዝፍ የግብር ክፍያ ግዴታቸሁን ያልተወጣችሁ መኖራችሁ ይታወቃል።
በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በከተማው ማስፋፊያ አከባቢዎች ሳይፈቀድ የተያዙ ቦታዎችና ግንባታዎችን ስርዓት ለማስያዝ፣ ለመቆጣጠርና ለመከላከል በተወሰነው ውሳኔ መሠረት ቦታ ወስዳችሁ እስከ አሁን ድረስ ቅጣትና የሊዝ ቅድመ ክፍያ ያልፈፀማችሁ እንዲሁም የሊዝ ቅድመ ክፍያ ፈፅማችሁ
የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያልወሰዳችሁ ከሰኞ ታህሳስ 27/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30/2018 ዓ.ም ብቻ የማዘጋጃ ቤታዊ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ ለመጨረሻ ጊዜ ለማሳወቅ ይወዳል።
ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ አመታዊና ውዝፍ የሊዝ ቦታ ክፍያን ያለፈፀሙ እና ክፍያ ፈፅመው ካርታ ያልወሰዱ አካላት አስተዳደሩ በተሰጠው ስልጣንና ህግና ደንብ በሚፈቀድለት መሠረት ይዞታውን ወደ መንግሥት የመሬት ባንክ ተመላሽ እንደሚደረግ በጥብቅ ያሳስባል።
የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት