20/04/2026
ሴቶች- ወጣቶች- አካል-ጉዳተኞች- አረጋውያን የምርጫ ካርድዎን ወስዳችኋል? የመራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።
በመጪው ግንቦት በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ድምፅዎን ለመስጠት ተዘጋጅተዋል? የሀገርን ዕጣ ፈንታ በሚወስነው በዚህ ዴሞክራሲያዊ ሂደት ላይ የራስዎን አሻራ ለማሳረፍ የመጀመሪያው እርምጃ ለመራጭነት መመዝገብ ነው።
የመራጮች ምዝገባ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል። ይህ ማለት የምዝገባው ጊዜ ሊያበቃ 2 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎ! የሚበጅዎትን ለመምረጥ፣ በቀሩት 2 ቀናት ውስጥ ይመዝገቡ።