10/10/2021
በዕየለቱ የሟቾች ቁጥር አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ስለመጣ ከመቼውም ጊዜ በላይ እንጠንቀቅ።
***************
በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ይህም በበሽታው የሚያዙ ፤ በፅኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን ቁጥር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን እየጨምረ ይገኛል።
በኢትዮጵያ አንድ በኮቪድ-19 ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ከተመዘገበበት ዕለት መጋቢት 4/2012 ጀምሮ 354‚033 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ፤ 736 ሰዎች አሁን ላይ በፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ። እንዲሁም 5,950 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
አሁንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሀገራችን ላይ ስጋት መሆኑን ቀጥሏል። ስለሆነም እየአንዳንዱ ግለሰብ በሀላፊነት ስሜት እራሱን ፣ ቤተሰቡን ማስክ በማድረግ፣ የእጅን ንጽህና በተደጋጋሚ በመጠበቅ ፣ በማንኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እና ለመቆጣጠር የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ እናሳስባለን::
ስለ ሕብረተሰብ ጤና አደጋ የኮቪድ-19 ጨምሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት እንዲሁም ጥቆማ ለመስጠት 8335 ላይ ደውለው የጤና ባለሙያዎችን ማነጋገር ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
#እንድናገለግልዎማስክዎንያድርጉ
https://t.me/EthPHI
https://www.facebook.com/EPHIEthiopia
EPHI one of the oldest and known public health institutes in Africa. It is open 24/7 for public health emergency management through Emergency Operation Center. For any information and help call 8335 or send us a message through [email protected]