01/01/2025
በግብር ከፋዩ ከንግድ ስራ ገቢ ግብር ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት የክህሎትና ስልጠና መስጠቱ ቀዳሚ ተግባር ነው :- አቶ አሸናፊ ሀልቻዬ
(ዲላ ፣ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም )
በግብር ከፋዩ ከንግድ ስራ ገቢ ግብር ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመሙላት የክህሎትና ስልጠና መስጠቱ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን የዲላ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ሀልቻዬ ተናግሯል ።
ኃላፊው ይህንን የገለጹት የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ ከዲላ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በወረዳ ለሚገኙ ለደረጃ ''ሀ'' እና ''ለ'' ግብር ከፋዮች በታክስ ሂሳብ መዝገብ አያያዝ ፤ በደረሰኝ አጠቃቀም እና በሪፖርቱ አቀራረብ ላይ የክህሎት ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው ።
ለግብር ከፋዮች ግንዛቤ በመፍጠር መንግስት ማግኘት ያለበትን ሀብት እንዲያገኝና ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ለማስቻል ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ነው ያስረዱት ።
መንግሥት ከዜጎች በሚሰበሰበው ግብር የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት በሚያደርገው ጥረት ግብር ከፋዩ የሚጠበቅበትን ግብር የመክፈል ግዴታ እንዳለበት ጠቁሞ ለግብር ከፋዩ የተሻለ ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብና ግብር ከፋዩ በህግ የተፈቀደለትን ወጪዎች በመለየት የታክስ ስርዓትን በተከተለ መልኩ በመስራት የሚጠበቀውን ግብር ለመክፈል የሚያስችል ስልጠና መሆኑ አያይዘው ገልጸዋል ።
የክህሎት ስልጠና የሠጡት በጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ የትምህርት ስልጠና ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ወይንሸት በቀለ በበኩላቸው በወረዳ ለሚገኑ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች ከታክስ ሂሳብ መዝገብ ፣ ደረሰኝ አጠቃቀም እና በሪፖርት አቀራረብ ጋር ተያይዞ በውስጡ ሊይዝ የሚገባውንና ከግብር ከፋዩ ህብረተሰብ መረጃን በተጀራጀ አግባብ በመያዝ ከመንግስት የሚጠበቅበትን ግብር ለመክፈል የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠሪያ መሆኑን ገልፀዋል ።
በዞኑ በፈቃደኝነት እና በታማኝነት ግብርን የሚከፍሉ የንግዱን ማህበረሰብ መጠን ለማሳደግ መሰል ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በየደረጃው በገቢ ጽህፈት ቤቶች ተጠናክረው የሚቀጥል መሆኑን መግለጻቸውን የዘገበው የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ነው ።