የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ/Gedeo Zone Education Dep't

  • Home
  • Ethiopia
  • Dila
  • የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ/Gedeo Zone Education Dep't

የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ/Gedeo Zone Education Dep't የዞኑን ትምህርት የሚመለከቱ ወቅታዊ ተዓማኒ መረጃዎችን ለተከታዮቻችን ማድረስ ተቀዳሚ ተግባራችን ነዉ።

‎የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ትምህርት ቢሮ በት/ቤቶች ምገባ ፕሮግራም ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነዉ‎‎ #ዲላ ታህሳስ 17/2018‎የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ትምህርት...
26/12/2025

‎የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ትምህርት ቢሮ በት/ቤቶች ምገባ ፕሮግራም ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ነዉ

‎ #ዲላ ታህሳስ 17/2018
‎የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ትምህርት ቢሮ በሀገር በቀል ትምህርት ቤቶች ምግብ ፕሮግራም በምግብ ደህንነት ፣ አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም አዘገጃጀት እና ንጽሕና አጠባበቅ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በዲላ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ የትምህርት ቤቶች ምገባ ፕሮግራም የተማሪዎች መጠነ መቅረት፣ መጠነ ማርፈድ እና መጠነ መድገም ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጿል።

የት/ቤቶች ‎ምገባ ከምግብነት ባለፈ የተማሪዎችን ውጤት ስለሚያሻሽል ምግቡ በሚዘጋጅበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥቷል።

‎በመድረክ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢሳያስ እንድርያስ ከምግብ ዝግጅትና አያያዝ ምግብ አዘጋጆች የግልና የማብሰያ ዕቃ ንጽሕና አጠባበቅ ፣ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀምና የውሃ ንጽሕና አጠባበቅ ልዩ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ ገልጿል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአለም ምገባ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ልዑልሰገድ ይመር የትምህርት ቤቶች ምገባ አላማዎች መካከል የተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ መጨመር፣ ወላጆች ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንድልኩ እንደሚያደርግ ፣ የአጭር ጊዜ ረሀብ እንደሚያሳታግስ ፣ የሴት ተማሪዎችን ተሳትፎ ማሳደግ ፣ የተማሪዎችን ጤና ማሻሻል እና የአርሶ አደሮችን ምርታማነት ማሳደግ ከአላማዎቹ እንደሚጠቀሱ መሆኑን ገልጸዋል

‎ስልጠናው ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን
‎ከክልሉ ከሁሉም ዞኖች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

‎@የጌዴኦ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን

14/10/2025
ቀን 19/2018 ዓ.ም                                        ‎ማስታወቂያ‎የ2018 ዓ.ም በትምህርት  ሚንስቴር ለአዳሪ ትምህርት ቤት በወጣው ማስታወቂያ  ተመዝግበው ...
29/09/2025

ቀን 19/2018 ዓ.ም ‎

ማስታወቂያ
‎የ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚንስቴር ለአዳሪ ትምህርት ቤት በወጣው ማስታወቂያ ተመዝግበው ለፈተና ያለፉ ተማሪዎች ነጌ ማለት 20/1/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8.00 ሰዓት በዩኒቨርሲቲ ግቢ በመገኘት መፈተኛ ክፍላቸውን እንዲያውቁት እና በ21/1/2018 ዓ.ም ጧት 2.00 ላይ መፈተኛ አዳራሽ እንድገኙ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ተማሪዎች በእረፍት ግዜያቸው የኢትዮ ኮደሪስ ስልጠና እንዲወሰዱ በትኩረት ይሰራል፦ በጌዴኦ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ‎‎( #ዲላ ሐምሌ 16-2017 ዓ/ም) መምሪያው በክረምት...
23/07/2025

ተማሪዎች በእረፍት ግዜያቸው የኢትዮ ኮደሪስ ስልጠና እንዲወሰዱ በትኩረት ይሰራል፦ በጌዴኦ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ

‎( #ዲላ ሐምሌ 16-2017 ዓ/ም) መምሪያው በክረምት ወራት የዩኒቨርስቲ፣ የኮሌጅና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በእረፍት ግዜያቸውን የኢትዮ ኮደራስ ስልጠና እንዲወስዱ በትኩረት እንደምሰራ አስታውቋል።

‎በጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረ የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በይፋ ከተጀመረ ወራቶች ተቆጥረዋል ።

‎ኢኒሼቲቩ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስና በኢትዮጵያ መንግስት የሚተገበር ሲሆን፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ አምስት ሚሊዮን ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና እንዲወስዱ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

‎መምሪያው የክረምት ወራት የተማሪዎች የኢትዮ ኮደሪስ ስልጠና በተመለከተ የአስተዳደር፣ የትምህርት፣ የተክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የኮሙኒኬሽን እና ሳይንስና ተክኖሎጂ አካላት በተገኙበት ንቅናቄ መድረክ አካሄደዋል ።

‎የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ሮቤ በመልዕክታቸው በክረምት ወራት የዩኒቨርስቲ፣ የኮሌጅና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በእረፍት ግዜያቸውን የኢትዮ ኮደሪስ ስልጠና እንዲወሰዱ ማመቻቸት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎ለስልጠና የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን በሟሟላት በትምህርት ቤቶችና በኮሌጆች ስልጠና ማዕከሎች እንዲወስዱ አስፈላጊ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረግ እንዳለበት አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል።

‎በጌዴኦ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደረጀ ሾንጣ በ2017 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30 ድረስ 7 ሺህ 233 ስልጣኖች ስልጠና እንዲወስዱ ታቅደው ከ2 ሺህ ስልጣኖች በላይ ሰርተፊኬት መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

‎በዞኑ በሶሥት ዓመታት ውስጥ 39 ሺህ የሚጠጉ ሰልጣኞች ስልጠና እንዲወስዱ መታቀዱን ገልጸው ኃላፊው በክረምት ወራት ከ13 ሺህ 107 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች ለማሰልጠን መታቀዱን ተናግረዋል።

‎ኢትዮጵያ ዓለም በቴክኖሎጂ የደረሰችበት ደረጃ ለመድረስ እያደረገች ላለው ጥረት ትልቅ ፋይዳ ያለውና ተማሪዎች የዲጂታል እውቀታቸውንና ክህሎት በማሳደግ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያግዝ መሆኑን የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘማች ክፍለ ገልጸዋል።

‎ሰልጠናው በቀጣይ ክረምት ወራት ውስጥ በንቅናቄ እንደሚመራና በዚህም ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ዩኒቨርስቲና የኮሌጅ ተማሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

‎በነጻ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ለመገንባት በተመቻቸው ዕድል ዛሬወኑ http://www.ethiocoders.et/ ሊንክን በመጫን ይመዝገቡ።

‎ Zone Public affairs

5 Million Ethiopian Coders Advancing Digital Literacy for Ethiopia’s Youth Acquire the essential digital skills necessary to establish a promising career in the ever-evolving technology industry with our comprehensive, fully-funded courses. Get started About this Initiative 5 Million Ethiopian Cod...

  on በCloud client Computer   መማር ማስተማር #የማጠናከሪያ ትምህርትየፈጠራ ሥራዎችወናጎ 2ኛ ደረጃ
12/04/2025

on በCloud client Computer
መማር ማስተማር
#የማጠናከሪያ ትምህርት
የፈጠራ ሥራዎች

ወናጎ 2ኛ ደረጃ

Tutorial Class  Primary Schools
08/04/2025

Tutorial Class

Primary Schools

Address

Abysinia Building Street Near Gedeo Zone Admin. Head Office
Dila

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ/Gedeo Zone Education Dep't posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share