Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በማድረስ ለህብረተሰብ ለዉጥ እንተጋለን ።

የአውሮፓ ኅብረት እና ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤ የአውሮፓ ኅብረት እና ብሪታኒያ  ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእንኳን ደስ ያላ...
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረት እና ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤

የአውሮፓ ኅብረት እና ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢትዮጵያ የብሪታኒያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ያካሄደችው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት በስኬት በመጠናቀቁ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን ብሏል።

ለዕጩ ተወዳዳሪዎች፣ ለሲቪል ማኅበራት ታዛቢዎች፣ ለበጎ ፈቃደኞች፣ ለምርጫ አስፈጻሚዎች እና ምርጫው ስኬታማ እንዲኮን ጊዜያቸውን ለሰጡት ሁሉ ያላውን አድናቆት ገልጿል።

የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የታዛቢ ቡድኖች የነበራቸውን አስተዋጽኦ በበጎ እንቀበላለን ነው ያለው።

የአውሮፓ ኅብረትም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ መካሄዱን በደስታ እንቀበላለን ብሏል።

​ ለምርጫ መሳካት አስተዋጽዖ ያበረከቱትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ዕጩ ተወዳዳሪዎችን እና የሲቪል ማኅበራት ተዋናዮችን ጥረት እናደንቃለን ነው ያለው።

​የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ( ኢጋድ) እንደ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች የተጫወቱትን ወሳኝ ሚና እንገነዘባለን ብሏል። የታዛቢዎችን ሪፖርት በጉጉት እንደሚጠብቅም አስታውቋል።

​በግንቦት 24 ቀን ምርጫ ማካሄድ ያልቻሉ ሁሉም የምርጫ ክልሎች ምርጫውን የማካሄድ ዕድል እንደሚያገኙ ያለውን ተስፋም ገልጿል።

የእናቶችን እና የህጻናትን ሞት ለመቀነስ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።ደሃና ፡ አምደወርቅ  ፣ ግንቦት   26/ 2018 ዓ.ም ( Dehana Woreda  Communication) በዋግ ኸም...
03/06/2026

የእናቶችን እና የህጻናትን ሞት ለመቀነስ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።

ደሃና ፡ አምደወርቅ ፣ ግንቦት 26/ 2018 ዓ.ም ( Dehana Woreda Communication) በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የእናቶችን እና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ተገለጸ።

የደሃና ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የእናቶችና ወጣቶች ስነ- ተዋልዶ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሞገስ አራጌ እንደገለጹት በዩኒሴፍ /unicef/ፕሮጀክት በተገኘ ድጋፍ የእናቶችን ፣ የህጻናትን እና የወጣቶችን ሞት ለመቀነስ ከ6 መቶ ሽህ በላይ በሆነ ወጭ 26 እስትሬቸር እና 31 የደም ግፊት መለኪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል ።

አክለው እንደገለጹትም እናቶችና ህጻናት የሚሞቱት ብዙ ጊዜ የደም መፍሰስ እንደሆነ አመላክተው ቀጣይም እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እስትሬቸሮችን እና የደም ግፊት መለኪያዎችን ጤና ጣቢያና ጤና ኬላ በአላቸው ቀበሌዎች በማሰራጨት የእናቶችን እና የህጻናትን ሞት እንቀንሳለን በማለት ገልጸዋል።



ተጨማሪ መረጃዎችን እንድናደርስዎት የደሃና ወረዳመንግስት ኮሙኒኬሽንን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።

Facebook
https://www.facebook.com/profile.100066304790042
👉YouTube ፤
https://youtube.com/channel/UCBbTi4Tq6iNrrxwMyg22FtQ
👉Telegram
https://t.me/amd1512
👉TikTokሀ
tiktok.com/
👉
https://x.com/wereda169222/status/2000868480283730223?t=YDjfJGEF09wzCqZE6z-TCw&s=19
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን

የምርጫው አፈፃፀም ዴሞክራሲያዊነት፣ ውጤታማነትና ሰላማዊነት ተገመገመ  በዋግኸምራ ብሄረሰብ አስ/ር 7ኛው አገራዊ ምርጫ ተአማኝነት፣ ዴሞክራሲያዊነት፣ ውጤታማነትናሰላማዊነት ላይ ሁሉም የዞኑ ...
03/06/2026

የምርጫው አፈፃፀም ዴሞክራሲያዊነት፣ ውጤታማነትና ሰላማዊነት ተገመገመ

በዋግኸምራ ብሄረሰብ አስ/ር 7ኛው አገራዊ ምርጫ ተአማኝነት፣ ዴሞክራሲያዊነት፣ ውጤታማነትናሰላማዊነት ላይ ሁሉም የዞኑ አስተበባሪዎች በተገኙበት ገምግሟል።

በመድረኩ የህዝቡ ፅናትና የመምረጥ ፍላጎት፣ ከተፎካካሪ ፖርቲዎች ጋር የነበረው መስተጋብርና መደጋገፍ፣ የፀጥታ ስራችን ቅንጅትና የሎጅስቲክስ አቅርቦት ቁርጠኝነት፣ የአመራሩ ያልተቋረጠ ድጋፍ መናበብ ጀግንነት፣ የሚድያው ውጤታማነት የሪፖርት ቡድኑ ፅናት፣ የምርጫው ዴሞክራሲያዊነትና ስኬታማነት በአዎንታ ተገምግሟል።

አጠቃላይ ምርጫው በሁሉም መመዘኛ ውጤታማ ታማኝና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነበር ተብሏል።

በመጨረሻም በቀጣይ በወረዳ ደረጃ ጥልቅ የአፈፃፀም ግምገማ እንዲደረግና ትኩረት የሚደረጉባቸውን ጉዳዮች በመድረክ መሪዎች አቅጣጫ ተሰጥቶበት ተጠቃሏል።

 !በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምርጫው በሰላም ተጠናቋል።ግንቦት 25/2018 ዓ.ም  በብሔረሰብ አስተተዳደሩ ሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በስኬት መ...
02/06/2026

!

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምርጫው በሰላም ተጠናቋል።

ግንቦት 25/2018 ዓ.ም በብሔረሰብ አስተተዳደሩ ሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በስኬት መጠናቀቁን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታውቋል።

የምርጫ ሂደቱ በሁሉም የብሔረሰቡ አካባቢዎች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በእቅድ የፀጥታ መዋቅሩን በማደራጀትና እንዲሁም ከሕዝብ ጋር በቅንጅት በመሠራቱ ምርጫው ሰላማዊና ስኬታማ ኾኖ መጠናቀቁን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ዋና ኃላፊ ፶ አለቃ አዘዘው አዳነ ገልፀዋል።

ስራው ብዙ ጥረትና ዝግጅት የደረገበት እንዲሁም ዋጋ የተከፈለበት ነበር ያሉት ኃላፊው በፀጥታ መዋቅራችን አይበገሬነትና በማኅበረሰባችን አጋዥነት ጥረታችን ፍሬ አፍርቶ ተፈላጊው ስኬት ተገኝቶበታል ብለዋል።

የምርጫ ሂደቱን ለማደናቀፍ ብዙ ትንኮሳዎች ቢደረጉም ማኅበረሰባችን ለፀጥታ መዋቅራችን ዐይንና ጆሮ ኾኖ በቅንጅት በመሠራቱ ትንኮሳዎች ሁሉ ከሽፈው የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊ ኾኖ ተጠናቋል ነው ያሉት።

የምርጫ ስራው ስኬታማ እንዲሆን ከወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውጤታማ ስራዎች መሠራታቸውን አክለዋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ ሕዝብ ከምርጫ ምዝገባ፣ ካርድ ማውጣትና እስከ ምርጫው ፍፃሜ ድረስ ያሣየው ቁርጠኝንና ትብብር የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ከፀጥታ መዋቅራችን ጋር በፍቅር ተጋምዶ በማስተባበር፣ አካባቢውንና ቀየውን እንዲሁም የጎረቤቱን ቤት በመጠበቅ ምርጫው መተሳሰብ፣ አብሮነትና መተባበርን ያጎናፀፈ እንደነበር አውስተዋል።

እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር በተሰሩ ስራዎች ሁሉም ተግባራት ያለምንም የፀጥታ ችግር በታቀው ጊዜና ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ ማስቻሉንም አስረድተዋል።

በምርጫው ሂደቱ የታየው ማኅበረሰባዊ ሥርዓት አክባሪነትና ሰላም ወዳድነት ለዘላቂ ሰላም መምጣት ተስፋ ሰጭና ተምሣሌት የሚሆን ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ምርጫው በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና ለተጫወቱ ለመላው የፀጥታ መዋቅርና ለማኅበረሰቡ የመምሪያው ዋና ኃላፊ ፶ አለቃ አዘዘው አዳነ ምሥጋና አቅርበዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ። ግንቦት 25/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ...
02/06/2026

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ግንቦት 25/2018 ዓ.ም በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በከፍተኛ ስኬት፣ ሥልጡን እና ሕዝባዊ ተሳትፎ በጎላበት መልክ በታላቅ የሕዝብ ድል መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ተወዳዳሪ የሌለው ሚና ለተጫወቱት የክልሉ ፖሊስ፣ ለጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌደራል የጸጥታ እና የብሔራዊ ደኅንነት አካላት ፣ለክልሉ ሚሊሻ፣ ሰላም አስከባሪ እና ለመላዉ ሕዝብ ምስጋና አቅርቧል።

ሁልጊዜ ሰላም እና ልማትን ቀዳሚ የሚያደርገው የክልሉ ሕዝብ የምርጫ ካርድ ከመውሰድ ጀምሮ በምርጫው ዕለት በታላቅ ትዕግስት እና ሥነ ሥርዓት ድምፅ እስከመስጠት ድረስ ያሳየው ፍቅር እና ሀገር ወዳድነት የታሪክ ማህደር የማይረሳው መኾኑን ገልጿል።

በምርጫው ዕለት ኅብረተሰቡ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመውጣት በክልሉ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ያከናወነው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ያለምንም መሰላቸት እስከ ምሽት ሰአት መከናወኑን አረጋግጧል።

ኅብረተሰቡ ረጅም ሰልፎችን በታጋሽነት በመሰለፍ፣ የመምረጥ መብቱን በአግባቡ መጠቀሙ የሠለጠነ ዴሞክራሲያዊ ባሕሉን ያሳየበት እና ለምርጫው ስኬታማነት ትልቁን ድርሻ ያበረከተበት መኾኑንም ጠቁሟል።

ምርጫው የክልሉን ሕዝብ ብስለት፣ ሰላም ወዳድነት እና ለሀገር ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት ዳግም ለዓለም ያስመሰከረበት ታሪካዊ ምዕራፍ መኾኑንም ዋና ጠቅላይ መምሪያው አመላክቷል።

የጸጥታ ኃይሉ ሂደቱን በበላይነት በመምራት፣ የእያንዳንዱን አካባቢ ኅብረተሰብ በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ በማንቀሳቀስ፣ ከሕዝብ የተውጣጡ የሰላም ኮሚቴዎችን እና አደረጃጀቶችን ከራሱ የጸጥታ መዋቅር ጋር በማስተሳሰር የጋራ የሰላም ግንባር መፍጠር በመቻሉ ሰላሙን ማረጋገጥ መቻሉንም አስታውቋል።

ይህንን ሥራ ስኬታማ ለማድረግ የጸጥታ ኃይሉ አባላት ሌት ከቀን ያሳዩት ከፍተኛ ልፋት፣ ድካም እና ተጋድሎ በአንዳንድ ቦታዎች የምርጫውን ሂደት ለማደፍረስ እና ሁከት ለመፍጠር አልመው የተንቀሳቀሱ ሕገ ወጥ አካላትን የጥፋት ሴራ ቀድሞ በተዘጋጀ ስልታዊ የመከላከል እቅድ ሙሉ በሙሉ ማክሸፍ መቻሉንም አመላክቷል።

የጸጥታ ኃይሉ የተጣለበትን ታሪካዊ አደራ የመወጣት ጀግንነት፣ ሙያዊ ብቃት እና የገባውን ቃልኪዳን በታማኝነት በመፈጸም የሕዝቡን ደኅንነት በልዩ ጥንቃቄ የማስጠበቅ ሥራ፤ ከተቋማዊ ኩራት ባሻገር ለክልሉ እና ለሀገሪቱ ታላቅ ክብርን ያጎናጸፈ ተግባር በመኾኑ ላቅ ያለ ምስጋናና እውቅና ሰጥቷል ነው ያለው።

ምርጫውን ለማወክ የሞከሩ ማናቸውንም የጸረ ሰላም ኃይሎች የጥፋት አጀንዳ ሙሉ በሙሉ ያከሸፈ ታላቅ የሕዝብ ድል የተመዘገበው ሕዝቡ ያሳየው አስተዋይነት እና የሰላም ባለቤትነት ስሜት በመኖሩ እንደኾነም አንስቷል።

ለታሪካዊ ድሉ መገኘት ሕዝቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም፣ መረጃዎችን በወቅቱ በመለዋወጥ እና ለሰላም ጥበቃው ግንባር ቀደም ጠባቂ በመኾን ያሳየው ጠንካራና የተቀናጀ ጥምረት ዋነኛ መሠረት ነበር ተብሏል።

በምርጫው ወቅት የታየውን መልካም የሕዝብ፣ የፖሊስ ቅንጅታዊ አሠራር እና አደረጃጀት ይበልጥ በማጠናከር የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በቀጣይም በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቋል።

ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ለሲቪክ ማኅበራት፣ ለመገናኛ
ብዙኃን ተቋማት፣ ለውጭ እና የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች እና ለሰላም ወዳዱ ማኅበረሰብ በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።

ከአማራ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው የተጀመረውን የሰላምና የዴሞክራሲ ጉዞ በጋራ ለማስቀጠል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደሚሠራም አስገንዝበዋል።

#አሚኮ

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባችኋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
02/06/2026

በብዙ ውጣ ውረዶች መካከል ያሳያችሁት ጽናት ለዴሞክራሲና ለሀገር ሕልውና የተከፈለ ነውና ከልብ የመነጨ ምስጋና ይገባችኋል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

02/06/2026

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት መግለጫ
!!

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ...
02/06/2026

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡

በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡

ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡

የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡

የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል - ቦርዱግንቦት 24፣ 2018 የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እ...
01/06/2026

የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል - ቦርዱ

ግንቦት 24፣ 2018 የድምፅ መስጠት ሒደቱ ከ12 ሰዓት በፊት ሰልፍ ይዘው የቆዩ መራጮች እስኪመርጡ ይቀጥላል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፡፡

በዛሬው ዕለት ከጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በነቂስ በመውጣት ድምጹን እየሰጠ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳ 12 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሒደት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሒደቱ እስከ 12 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሒደቱ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።

Address

Amdewerqe
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dehana Woreda Communication Affairs office የደሀና ወረዳ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share