Cadaster Dessie

Cadaster Dessie Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Cadaster Dessie, Government Organization, Dessie.

28/06/2022

የተመረጡ መፃሕፍትንና አስተማሪና አነቃቂ መልእክቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን👇👇 join ያድርጉ https://t.me/lighthouselearningcenter

23/06/2022

ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል።

ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል።

አልጋው የሚገኘው በክፍሉ ብቸኛ ከሆነው መስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል።

እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ...ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው ሰው ይገልጽለታል።

በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል በሀይቁ ላይ
ዳኪዬዎች ይዋኛሉ ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ...

ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል...በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ ይተርክለታል። በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ።

አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ጠራች።

ያ ብቻውን የቀረው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ ሊወስዱለት ይችሉ እንደሆነ ጠየቀ። ወሰዱለት። በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው።

ደነገጠ። ነርሷ ምን ሆንክ? አለችው።

ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር አላት። ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር አለችው።

ልብ የሚነካ ነገር...ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው።

አንዳንድ ሠዎች እንዲህ ናቸው። እነሡ እየሞቱ የሠውን የህይወት ብርሀን ያለመልማሉ። ሰው የመሆን ሚስጥር ደግሞ ይህ ነው። ለሰወች ደስታ መኖር።

ሰው ማለት ለሰው መኖር ተስፋ መሆን ነው እንጂ ለሰው የችግሩ መንስኤ መሆን ይደለም።

አንተስ? እስከመቼ የራስህ ብርሀን እያለህ የሠው ጭላንጭል ያስቀናሀል?

እስከመቼ የሰዎችን ደስታ ትገድላለህ?

እስኪ ለአንድ ደቂቃ ዝም ብለህ አስብ መልካምነት እኮ አያስከፍልም።

የሠው ህይወት ማዳን ባትችል እንኳን ቢያንስ ለሠው ተስፋ ስጥ። ይሄም የመልካምነት አንዱ ገፅ ነው።

አስታውስ ለሰዎች ደስታ መስጠት ባትችል እንኳን የስቃያቸው መንስኤ አትሁን!!

መልካም አድርግ መልካምነት አያስከፍልም ዋጋህን ከፈጣሪ ታገኘዋለህ!

ማዳን ባትችል ቢያንስ ለሰዎች ለህመም መንስኤ አትሁን!!

የቴሌግራም ቻናላችንን 👇👇👇 join ያድርጉ
https://t.me/lighthouselearningcenter

23/06/2022
29/04/2022

በአዳማ ከተማ የካዳስተር አተገባበር
“የካዳስተር ስራዉ ዉጤታማነት ከፍተኛ አመራሩ ለዘርፉ በሚሰጠዉ ትኩረት ይወሰናል” አቶ ሳሙኤል ሊዮን
(የአዳማ ከተማ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊና የካዳስተር ዘርፍ አስተባባሪ)
***********************************************************
የአዳማ ከተማ የካዳስተር ትግበራዉ ቀድሞ ከተጀመረባቸዉ የኢትዮጵያ ከተሞች ዉስጥ አንዷ ሲትሆን በአሁኑ ሰዓት ዘርፉ በከፍተኛ ፍጥነት ተጨባጭ ለዉጥ ካመጣባቸዉ ከተሞች መካካል ግንባር ቀደም ከተማ እየሆነች መምጣቷን ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እና ከተለያዩ የሀገር ዉስጥ የብሮድካስትና የፕሪንት ሚዲያ ጋዜጠኞች ጋር የህጋዊ ካዳስተር ትግበራዉን ትኩረት አድርጎ በተከናወነ የሚዲያ ቱር ላይ ለመመልከት ተችሏል፡፡

በከተማዉ በተለይም በህጋዊ ካዳስተር ዘርፉ የተሰሩ ስራዎች ማለትም ከመሬት ይዞታ ቅድመ ማረጋገጥ፣ ከማረጋገጥ፣ ከመመዝገብ፣ ከሲስተም ልማት፣ ከአገልግሎት አሰጣጥና ከግንዛቤ ፈጠራ አንፃር የተከናዎኑ ተግባራትን ውጤታማ ሥራ መሰራቱን ማየጥ ተችሏል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በካዳስተር ዘርፉ የተሰሩ ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ማብራሪያ የሰጡት የአዳማ ከተማ የመሬት አስተዳደር ቢሮ ም/ኃላፊና የካዳስተር ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሳሙኤል ሊዮን እንደገለፁት በ2014 በጀት አመት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ለዘርፍ በሰጡት ትኩረትና ክትትል እንዲሁም ህጋዊ ካዳስተር ለህብረተሰቡ የሚያስገኘዉን ዘርፈ ብዙ ጥቅም ለማስረዳት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በተሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች አማካኝነት የከተማዉ ህብረተሰብ እራሱ ያለ ማንም ቀስቃሽነት ይዞታዉ እንዲረጋገጥለትና እንዲመዘገብለት እንዲሁም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚጠይቅበት ደረጃ ላይ መድረስ እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳሙኤል አክለዉም በበጀት አመቱ በ60 ሰፈሮች ከ55 ሽህ በላይ ይዞታዎችን ማረጋገጥ እንደተቻለና በካዳስተር ዘርፉ በተሰጡ አገልግሎቶች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ እንደተቻለ በመግለፅ ከከተማዉ ስፋትና ከአገልግሎት ተጠቃሚዉ የህብረተሰቡ ክፍል ብዛት አንፃር የሚስተዋሉ እንግልቶችን ለመቅረፍ በአንድ መስኮት ብቻ ይሰጥ የነበረዉን አገልግሎት ወደ 9 መስኮት ማሳደግና ከክፍያ ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ህብረተሰቡ ፈጣን የአገልግሎት ያገኝ ዘንድ 3 ባንኮችን ማለትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክና ስንቄ ባንክ በቢሮዉ ህንፃ ላይ ቅርንጫፍ ከፍተዉ እንዲሰሩ በማድረግ ህብረተሰቡ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኝ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም ኃላፊዉ ሲናገሩ አዳማ ከተማ በካዳስተር ዘርፉ ይህን ስኬት ማስመዝገብ የቻለበት ዋናዉ ምክንያት በአመራሩ ቁርጠኝነትና ከመብት ፈጣሪዉ ጋር ባለዉ ቅንጂታዊ አሰራር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በውብሸት በለጠ

09/03/2022

ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?
✅✅✅✅✅✅
ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡
ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡- አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡ ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡ ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡
የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡ በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡
በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡ በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው:: ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡
የህጋዊ ካዳስተር ዝርጋታ ተግባራዊ መሆን የሚያስገኛቸው ፋይዳዎች
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
✍️በአገር ደረጃ በአገልግሎት አሰጣጥ የሚስተዋለውን የተወሳሰበ ችግር ይህ የአሰራር ስርአት ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት ይሄን ችግር በመሰረታዊነት እንደሚፈታ ይታመናል፤
✍️በዘርፉ የግብይት ስርአቱን ቀላል፣ ግልፅ፣ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረጉ ባሻገር በአገር ኢኮኖሚ እድገቱ ላይ የራሱን አውንታዊ ሚና መጫወት ይችላል፤
✍️በዘርፉ በመረጃ አያያዝ ጉድለት የነበረውን ችግር ተጠቅመው ጥቂቶች አላግባብ የሚበለፅጉበትንና ህጋዊ ባለይዞታዎችን ለተለያዩ ጉዳቶች ይዳርግ የነበረውን የአሰራር ችግር ሊፈታ ይችላል ተብሎ ይታመናል፣
✍️ በክልልም ሆነ በፌደራል ደረጃ በዘመናዊ መንገድ የሚደራጀው የከተማ መሬት ይዞታ መረጃ አዳዲስ ፖሊሲዎችን፣ አሰራሮችንና ህጎችን ለማመንጨት የተሻለ ግብአት ሆኖ ያገለግላል፤
✍️ የከተማ አስተዳደሮች የሚያስተዳድሩትን መሬት ቆጥረው እንዲያውቁ፣ የትኛውን መሬት ለየትኛው አገልግሎት ማዋል እንዳለባቸው አቅደው እንዲሰሩና በተገቢው መንገድ እንዲያስተዳድሩ ከፍተኛ እገዛ ያደርግላቸዋል፤
✍️ከተሞች ከመሬት ሃብታቸው መሰብሰብ የሚገባቸውን ግብር እና ኪራይ በተገቢው መንገድ በመሰብሰብ ለለከተማው የመሰረተ-ልማት ግንባታ በማዋል ከተሞች በስርአቱ ያድጋሉ፣ የከተማው ነዋሪም የልማቱ ተጠቃሚ ይሆናል፤
✍️የካዳስተር ስርአቱ በሚፈጥረው የመረጃ ምልዑነት በከተማ መሬት ይዞታ የሚስተዋለውን በዜጎች መካከል የሚፈጠረውን ክርክር ይቀንሳል፣ በዚህ ምክንያት የሚያጠፋውን ገንዝብ፣ ጊዜ እና የፍትህ መጓደል ይቀንሳል፤
✍️ማንኛውም ዜጋ በከተማ መሬት ይዞታ ዘርፍ ማግኘት የሚፈልገውን መረጃ ብዙ ውጣውረድ ሳይገጥመው በቀላሉ እንዲያገኝ ያደርጋል፤
✍️በከተሞች ህጋዊ ካዳስተርን መገንባት ከተቻለ የውጭም ሆነ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች እምነት ስለሚያሳድሩ ሃብታቸውን ልማት ላይ ያውላሉ በዚህም ነዋሪው ተጠቃሚ ይሆናል፣ ከተሞች ያድጋሉ፣ ሳቢም ይሆናሉ፤
✍️በዘርፉ ሙያ ለተሰማራው አመራርም ሆነ ባለሙያ የእውቀት ሽግግር እንዲፈጠር ያደርጋል፣ አቅምም ይገነባል፣ በዚህም በየደረጃው ተጠቃሚ እንዲሆን ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፡፡

23/10/2021

የከተማ መሬት መረጃ አያያዝ ስርአት / ካዳስተር/ ምንነትና የሚያስገኘው ጠቀሜታ
============================================
ካዳስተር ማለት የመሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) አንዱ ሲሆን የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እንዲሁም አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ይሆናል፡፡
ሁለተኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል ይታወቃል፡፡ ይህም የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ. እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን የሚያካትት ሲሆን እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡
ካዳስተር ህጋዊ ካዳስተር ፤ፊስካል ካዳስተር እና ሁለገብ ወይም ሁሉን አቀፍ ካዳስተር ተብሎ በሦስት ይከፈላል፡፡
ህጋዊ ካዳስተር ተብሎ የሚጠራው ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም የትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታው የይዞታ ዋስትና የሚረጋገጥበት ይሆናል፡፡
ሁለተኛው ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡
ሦስተኛው የካዳስተር ዓይነት ሁለገብ ወይም ሁሉን አቀፍ ካዳስተር የሚባለው ሲሆን በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ-ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡
የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡
በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፤ የተሞከረውም ሁለ-ገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር፤ ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡ በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለ-ገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን በመገንዘብ በአገራችን በሚገኙ ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ሁኖ ተገኝቷል፡፡
መሬት በቁጠባ ሊተዳደር የሚገባው አላቂ ሃብት በመሆኑ በአጠቃቀም እንዳይባክን ብክነት የሚወገድበትን አሰራር መፍጠር ያስፈልጋል፡፡
የመሬት መረጃ አያያዝ እንደ ወቅቱ የቴክኖሎጂ ደረጃ መንግስታት መሬትን ለማስተዳደር እንደሚከተሉት የመሬት አስተዳደር እንዲሁም መረጃን ዘመናዊ ለማድረግ ካላቸው ቁርጠኝነት ጋር ተያይዞ የሚወሰን ሲሆን ይህም በፖሊሲዎች እና በህግ ማዕቀፎች ላይ የሚንጸባረቅ ይሆናል፡፡
በዋናነት ካዳስተር መረጃ ላይ በመመርኮዝ በከተሞች የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ የቋሚ ንብረት ሃብት ወደ ገበያ እንዲገባ ከማስቻል ባለፈ ዜጎች የኢኮኖሚው እድገት እን

24/01/2019

በሆጤ ክ/ከተማ በዳውዶ ቀበሌ በምንትዋብ ሰፈር የቅየሳ ስራ ተጠናቋል፡፡

ዛሬ ማለትም በ14/04/2011 አ/ ም በኮምቦልቻ ከተማ የደሴ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም አጋር አካላት በተገኙበት ስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ።
27/12/2018

ዛሬ ማለትም በ14/04/2011 አ/ ም በኮምቦልቻ ከተማ የደሴ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም አጋር አካላት በተገኙበት ስልጠናና የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ዛሬ ማለትም በ 14/04/2011 በኮምቦልቻ ከተማ የተሻሻለውን መመሪያ ቁጥር 61 መሰረት ያደረገና በተለያዮ ጉዳዮች ላይ አጋር አካላት በተገኙበት ስልጠናና ውይይት ተካሂዷል
23/12/2018

ዛሬ ማለትም በ 14/04/2011 በኮምቦልቻ ከተማ የተሻሻለውን መመሪያ ቁጥር 61 መሰረት ያደረገና በተለያዮ ጉዳዮች ላይ አጋር አካላት በተገኙበት ስልጠናና ውይይት ተካሂዷል

በምንትዋብ ሰፈር የወሰን ማካለል ቡድንና የህዝብ ታዛቢዎች በጋራ የተወሰደ ምስል
29/11/2018

በምንትዋብ ሰፈር የወሰን ማካለል ቡድንና የህዝብ ታዛቢዎች በጋራ የተወሰደ ምስል

Address

Dessie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Cadaster Dessie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Cadaster Dessie:

Share