26/06/2018
የንግድ ሥራ ፈቃድን ስለማሳደስ
1 የንግድ ሥራ ፍቃድ በየበጀት ዓመቱ ከሐምሌ 01 ቀን እስከ
ታህሳስ 30 ቀን ባሉት 6 ወራት ዉስጥ መታደስ አለበት፡፡
2 ኃላፊነታቸዉ የተወሰኑ የንግድ ማህበራት ካስመዘገቡት
ካፒታል ሦስት አራተኛ የበሉ ከሆነ የንግድ ሥራ ፍቃዳቸዉ
አይታደስም፤ ሆኖም ማህበሩ ያስመዘገበውን ኪሳራ ሃምሳ
በመቶ በሰነድ አረጋጋጭ በጸደቀ ቃለ ጉባኤ የማህበሩ አባላት
ወደ ንግድ ድርጅቱ ሂሳብ ያስገቡበት ማረጋገጫ ሰነድ ከቀረበ
የንግድ ሥራ ፍቃዱን ሊታደስ ይችላል፡፡
3 የንግድ ሥራ ፈቃድን ለማሳደስ የሚፈልግ ነጋዴ ለዕድሳት
የተዘጋጀውን ማመልከቻ ቅጽ በመሙላት አዋጁን ለማስፈጸም
በወጣው ደንብ ከተመለከቱት ሰነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
4 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) በተጠቀሰው የፍቃድ ማሳደሻ
ጊዜ ውስጥ ነጋዴው የንግድ ፈቃዱን ካላሳደሰ ከጥር 01 ቀን
እስከ ሰኔ 30 ቀን ላለው ጊዜ ከፍቃድ ማሳደሻው በተጨማሪ
ፈቃድ ማሳደሱ ለዘገየበት ለጥር ወር ብር 2,500 (ሁለት ሺህ
አምስት መቶ ብር) እና ለሚቀጥለው እያንዳንዱ ወር ብር
1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ቅጣት በመክፈል
ፈቃዱን ያሳድሳል፡፡
5 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) በተደነገገው መሠረት
በቅጣት የማሳደሻ ጊዜ ውስጥ ያልታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ
አግባብ ባለው ባለስልጣን ይሰረዛል፡፡
6 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) መሠረት የንግድ ፈቃዱ
የተሰረዘ ከሆነ፣ ነጋዴው ፈቃዱን በወቅቱ ላለማሳደሱ ያቀረበው
ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት አግባብ ባለው ባለሥልጣን
ተቀባይነት ካገኘ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) የተደነገገውን
ቅጣት በመክፈል ፈቃዱ ከተሰረዘበት እስከ አንድ ዓመት ባለው
ጊዜ ውስጥ የተሰረዘውን የንግድ ፈቃድ እንደገና ማውጣት
ይችላል፡፡
7 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ (4) መሰረት የንግድ ስራ ፈቃዱ
እንዲታደስ ካልተፈቀደ ነጋዴው ያንኑ የንግድ ሥራ ፈቃዱን
የሚያወጣው የንግድ ፈቃዱ ከተሰረዘበት ከአንድ ዓመት በኋላ
ያለቅጣት ይሆናል