01/06/2026
"የዘንድሮው ምርጫ ከፍተኛ መራጭ የታየበት ነው" የብልጽግና ፓርቲ የደሴ ከተማ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ዶክተር ማህተመ ሀይሌ።
ዶክተር ማህተመ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በደሴ ከተማ በሮቢት የምርጫ ጣቢያ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።
ዶክተር ማህተመ ከፋና ሚዲዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ የዘንድሮ ምርጫ ፍፁም የተረጋጋ እና ከባለፉት አመታት የለዬ መሆኑን አንስተዋል።
ህዝቡ ይበጀኛል ይጠቅመኛል የሚለውን በነፃነት ሲመርጥ መመልከታቸውን ያነሱት ዶክተር ማህተመ ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ ምዕራፍ እየተሸጋገረች መሆኑን ያመላከተ ነው ብለዋል።
ምርጫው እስከ ምሽት 12 ሰዓት የሚቀጥል ነው ያሉት ዶክተር ማህተመ ሰው ያወጣውን የምርጫ ካርድ ሳያባክን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድምጽ በመስጠት ቀጣይ መሪውን እንዲመርጥ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ደሴ ፋና