Anrs Ethics and Anticorruption Dessie Branch /የአብክመ ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮ/ደ/ ቅ/

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Anrs Ethics and Anticorruption Dessie Branch /የአብክመ ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮ/ደ/ ቅ/

Anrs Ethics and Anticorruption Dessie Branch /የአብክመ ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮ/ደ/ ቅ/ Creating awareness of corruption prevention

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ ******************** (የአብክመ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.ደ.ቅ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የ...
01/06/2026

በሙስና ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

********************

(የአብክመ.ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.ደ.ቅ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም) በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የአብማ ክፍለ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ከመሬት ጋር በተያያዘ ሙያቸውንና ስልጣናቸውን ተጠቅመው በፈጸሙት የሙስና ወንጀል 10 ተከሳሾች በእስራት ተቀጥተዋል፡፡

ተከሳሾች፣ የሰነድ አልባ መረጃን በማጽናት እና በማጽደቅ ሂደት የመንግስትን መሬት ለሌላ ግለሰብ አሳልፈው በመስጠት በፈፀሙት የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት መዝገቡን ለምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ መምሪያ መላክ መቻሉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የሙስና ወንጅሎች ምርመራ ዋና ክፍል ሃላፊ ኮማንደር ጌታነህ አሰፋ ገልጸዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ መምሪያ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና ክስ በመመስረት በህግ አግባብ ሲታይ ከቆየ በኋላ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀን በ19/9/2018 ዓ,ም በዋለው ችሎት ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተረጋግጧል፡፡

በዚህም 1ኛ አቶ አላምር ተስፋዬ፣ 2ኛ ወ/ሮ ሀይማኖት ታሪኩ፣ 3ኛ አቶ መኳንንት ጠለለ፣ 4ኛ አቶ እንዳልካቸው፣ 5ኛ አቶ ተሻለ መብራቴ፣ 6ኛ አቶ ዮሴፍ ጌትነት እና 7ኛ አቶ ስላንተ ጥበቡ እያንዳንዳቸው በሁለት መዝገብ በ10 አመት እስራት ተቀጥተዋል፡፡

8ኛ ወ/ሮ ታሪክ ሞትባይኖር በተለዬ መንገድ ከግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቴክኒክ ኮሚቴውንና የአብይ ኮሚቴውን በማሳመን ለግለሰቦች መብት ከመፍጠር ባሻገር በራሷ ልጆች ስም የመንግስትን መሬት በማዘወር መብት የፈጠረች መሆኑን በማስረጃ በመረጋገጡ በሁለት መዝገብ በ12 አመት እንዲሁም ወ/ሮ ሶሊያና መሀሪና ወ/ሮ አብዮት እጅጉ እያንዳንዳቸው በ3 አመት እስራት መቀጣታቸውን ገልጸዋል።

የሙስና ወንጀል የመልካም አስተዳደር ችግር ከመፍጠሩም በላይ በሀገር ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን በማስከተል በህዝብ እና በመንግስት መካከል መተማመን እና ተቀራርበው እንዳይሰሩ የሚያደርግ መጥፎ በሽታ በመሆኑ ማንኛውም ህብረተሰብ የሙስና ወንጀል ሊፈፀም መሆኑን ሲያውቅ ወይም ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት እና ለህግ ተባባሪ በመሆን የዜግነት ድርሻቸውን መወጣት እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ የፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

01/06/2026

መልካም ሥነምግባር ያለው መራጭ ለሀገሩ ዘላቂ ሰላም፣ ለፍትሕ መረጋገጥ እና ለጠንካራ ተቋማት ግንባታ መሠረት የሚጥል ንቁ ዜጋ ነው!

*****************

​የአንድን ሀገር እድገት የሚያሳድገውና ወደ ብልፅግና የሚያሸጋግረው በዕውቀት፣ በኃላፊነት ስሜት እና በበሰለ የሞራል እሴት የሚመራ ንቁ ዜጋ ሲኖር ነው።

በአንድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ውስጥ የመራጩ ሕዝብ ንቃተ ሕሊና እና የሥነምግባር ደረጃ የሂደቱን ስኬታማነት የሚወስን ዋነኛ ምሰሶ ነው። መራጮች መልካም ሥነምግባርን ተላብሰው ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን ሲወጡ የሚከተሉትን ጥቅሞች ይኖሩታል።

​👉 የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት ይንጸባረቃል፦ መራጩ ሕዝብ ከጥቅማ ጥቅም፣ ከዘር ወይም ከማስፈራራት ነፃ ሆኖ በራሱ ሕሊና እና በፓርቲዎች አማራጭ የፖሊሲ ሃሳብ ላይ ብቻ ተመስርቶ ድምፁን ሲሰጥ፣ እውነተኛ የሕዝብ ውክልና ያለው መንግስት ይቋቋማል።

​👉 ሰላማዊና ሥርዓታዊ ሂደት ይኖራል፦ ሥነምግባር ያለው መራጭ የሌሎችን የመምረጥና የመመረጥ መብት ያከብራል፤ የሐሳብ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ያስተናግዳል። ይህም በምርጫ ወቅትና ከምርጫ በኋላ ሊነሱ የሚችሉ አላስፈላጊ ጉዳዮችን ያስቀራል።

​👉 ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት ይገነባል፦ መራጮች ድምጻቸውን በጥንቃቄና በኃላፊነት ስሜት ሲሰጡ፣ ተመራጭ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ለሕዝብ ቃል የገቡትን ተግባራዊ ለማድረግና በቅንነት ለማገልገል ይገደዳሉ።

​በመሆኑም፣ እያንዳንዱ ዜጋ ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲያቀና፣ የሚሰጣት አንዲት ድምፅ የሀገርን የወደፊት ዕጣ ፈንታ፣ ሰላምና ልማት የመወሰን ታላቅ አቅም እንዳላት ማመን አለበት። ይህንን ኃላፊነት በሰላማዊ፣ በታማኝ እና በበሰለ ሥነምግባር መወጣት የሁሉም ዜጋ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል።

!

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስልቶች ********************ሙስናን በአንድ ተቋም ወይም በቅጣት ብቻ ከመዋጋት ይልቅ፣ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የተለያዩ እርስ በእርስ የሚደጋገፉ አካ...
30/05/2026

የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስልቶች

********************

ሙስናን በአንድ ተቋም ወይም በቅጣት ብቻ ከመዋጋት ይልቅ፣ ችግሩን ከመሰረቱ ለመቅረፍ የተለያዩ እርስ በእርስ የሚደጋገፉ አካሄዶችን አቀናጅቶ መተግበር ላይ ማተኮር ይገባል፡፡ ይህ ስልት በዋናነት በሥነምግባር ግንባታ፣ በሙስና መከላከል እና በህግ ተፈጻሚነት (እርምጃ) ምሰሶዎች ላይ የሚቆም ነው። በዚህም የተቀናጁ የሙስና መከላከል ዋና ዋና ስልቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

​✍ የህዝብ ግንዛቤን ማሳደግ እና የሥነ-ምግባር ግንባታ፡- ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል ማህበረሰቡ በሙስና አስከፊነትና በሥነ-ምግባር ላይ ያለው እውቀትና አመለካከት መቀየር አለበት። የሥነ-ምግባር ትምህርት ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድረስ በስርዓተ-ትምህርት ውስጥ በማካተት ታማኝ፣ ቅን እና መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ትውልድ መገንባት ይገባል፡፡

ሙስናን ለመከላከል የንቅናቄና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን በሚዲያ፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እና በህዝባዊ መድረኮች አማካኝነት የሙስናን ጎጂነት እና አስከፊነት ለህዝብ ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡

​✍ በተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነት ማስፈን፡- ሙስና የሚከሰተው አሰራሮች ግልጽ ካለመሆነና ለግል ውሳኔ ሰፊ እድል በሚሰጥበት ወቅት ነው። ግልጽነትና ተጠያቂነት የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን፣ የበጀት አጠቃቀምን እና የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለህዝብ ክፍት በማድረግ ሙስናን መከላከል ይገባል።

​✍ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ፡- የአገልግሎት አሰጣጥን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ከሰው እጅ ንክኪ በመቀነስ ጉቦ የመጠየቅና የመስጠት እድሎችን ማጥበብ ያስፈልጋል።

​✍ የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከር፡- የአገር ውስጥ እና ዓለምአቀፍ የህግ ማዕቀፎችን በማጣጣም የሙስና መከላከያ ህጎችን ማክበር እና ማስከበር ይገባል። የህግ ማሻሻያዎች የፀረ-ሙስና አዋጆችንና ደንቦችን ከወቅታዊ የሙስና ውስብስብ ባህሪ ጋር አብሮ እንዲሄድ ያስችላሉ።

​✍ ዓለምአቀፍ ስምምነቶችን መተግበር፦ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀረ-ሙስና ኮንቬንሽን (UNCAC) እና የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከልና መዋጋት ኮንቬንሽን (AUCPCC) እና ሌሎች የስምምነት መርሆች በአገር ውስጥ ህጎችና አሰራሮች ውስጥ ማካተት ሙስናን በተቀናጀ መልኩ ለመከላከል ከሚግዙ ስልቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

​✍ የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ተሳትፎን ማሳደግ፡- ሙስናን በአንድ ተቋም ብቻ መከላከል ስለማይቻል የተቀናጀ አቀራረብ የሁሉንም አካላት ተሳትፎ ይጠይቃል። ዘርፋ በግልጽነትና በፍትሀዊ ውድድር ላይ የተመሰረተ እንዲሆን መደገፍ እና የሲቪል ማህበራት በክትትል ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ያስፈልጋል።

በአጠቃላይ፣ የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስልት ስኬታማ የሚሆነው ተቋማትና ባለድርሻ አካላት በተናጠል ሳይሆን በቅንጅትና ትብብር ሙስናን መታገል ሲችሉ ብቻ ነው። ስለሆነም፣ ሙስናን በመታገል ሀገራችን በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ማህበራዊ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ውጤታማ የማድረግ ኃላፊነታችን መወጣት ይጠበቅብናል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!
ምንጭ:- የፌዴራል ስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ

ኩረጃን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?ኩረጃን ለመዋጋት የጋራ ጥረት ያስፈልጋል። ከትምህርት ቤቶች፣ ከመምህራንና ከተማሪዎች የሚጠበቁት ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ሀ) ...
29/05/2026

ኩረጃን ለመከላከል ከባለድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል?
ኩረጃን ለመዋጋት የጋራ ጥረት ያስፈልጋል። ከትምህርት ቤቶች፣ ከመምህራንና ከተማሪዎች የሚጠበቁት ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦
ሀ) ከትምህርት ቤቶች (አስተዳደር) የሚጠበቅ
• ጥብቅና ግልጽ መመሪያዎችን ማውጣት፦ በኩረጃ ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን (ለምሳሌ፦ ከማስጠንቀቂያ እስከ ትምህርት ቤት መባረር) በግልጽ አስቀምጦ በተግባር ማሳየት።
• የፈተና አሰጣጥ ሥርዓትን ማጠናከር፦ በፈተና ወቅት የተማሪዎችን አቀማመጥ ማራራቅ፣ በቂና ታማኝ ፈታኞችን መመደብ እና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን (ስልኮችን) መከልከል።
• የስነ-ምግባር ግንባታ ላይ መስራት፦ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የኩረጃን ጎጂነት የሚያስተምሩ የውይይት መድረኮችንና ክለቦችን ማቋቋም።
ለ) ከመምህራን የሚጠበቅ
• የፈተና አወጣጥ ስልትን መቀየር፦ በቀጥታ ከደብተር ተገልብጠው የሚመለሱ ጥያቄዎችን ከመጠየቅ ይልቅ፣ የተማሪውን የማሰብና የማገናዘብ ችሎታ የሚፈትኑ ጥያቄዎችን ማዘጋጀት።
• በፈተና ክፍል ውስጥ ንቁ መሆን፦ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት ስልክ ከመጠቀም ወይም ከመቀመጥ ተቆጥቦ፣ ክፍሉን በአግባቡ መቆጣጠርና መከታተል።
• ተማሪዎችን በእኩልነትና በአርአያነት መምራት፦ መምህራን ራሳቸው ታማኝና ለሙያቸው ታማኝ መሆን አለባቸው። እንዲሁም ተማሪዎች በራሳቸው እንዲተማመኑ የማበረታታት ሥራ መሥራት ይኖርባቸዋል።
ሐ) ከተማሪዎች የሚጠበቅ
• የእውቀት ባለቤት ለመሆን መጣር፦ የትምህርት ዓላማው ማለፍና ማርክ ማምጣት ብቻ ሳይሆን እውቀትና ክህሎት ጨብጦ ራስንና አገርን መጥቀም መሆኑን መገንዘብ።
• በራስ መተማመንን ማሳደግ፦ ከሰነፍ ጓደኞች ግፊት መውጣት፣ የራስን ጥናትና ዝግጅት በጊዜ መጀመር እና "ባገኘሁት ውጤት እሰማማለሁ" የሚል ታማኝነትን ማዳበር።
• ኩረጃን አለመተባበር፦ ለጓደኛ ማኮረጅ "ደግነት" ሳይሆን ጓደኛውን መግደልና አገርን መክዳት መሆኑን ማወቅ። ኮራጆችንም ማበረታታት ማቆም።
ማጠቃለያ፦ ኩረጃ አገርን በቁም የሚገድል መርዝ ነው። እሱን ማጥፋት የሚቻለው እያንዳንዱ ተማሪ ታማኝነትን ሲመርጥ፣ መምህራን ኃላፊነታቸውን በንቃት ሲወጡ፣ እና ትምህርት ቤቶች ህግን ሳያዳሉ ሲያስከብሩ ብቻ ነው።

ኩረጃ በሀገር ላይ ያለው ጉዳትኩረጃ (ፈተና መገልበጥ ወይም ማጭበርበር) በትምህርት ሥርዓት ላይ ብቻ ሳይሆን በአገር አጠቃላይ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ቀውስ የሚያስከትል አደገኛ በሽታ ነው። የአ...
29/05/2026

ኩረጃ በሀገር ላይ ያለው ጉዳት
ኩረጃ (ፈተና መገልበጥ ወይም ማጭበርበር) በትምህርት ሥርዓት ላይ ብቻ ሳይሆን በአገር አጠቃላይ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ቀውስ የሚያስከትል አደገኛ በሽታ ነው። የአንድን አገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚያበላሽ እና የትውልድ ስነ-ምግባርን የሚመርዝ ድርጊት ነው።
1. ኩረጃ በሀገር ላይ ያለው ጎጂነት (ጉዳቶች)
• ብቃት የሌለው የሰው ኃይል ማፍራት፦ ተማሪዎች ሳይማሩና ሳያውቁ በኩረጃ ውጤት አምጥተው ሲመረቁ፣ ነገ አገርን የሚረከቡት ዶክተሮች፣ መሐንዲሶች፣ መምህራንና መሪዎች ብቃት የሌላቸው ይሆናሉ። ይህ ደግሞ የሕዝብን ሕይወት ለአደጋ ያጋልጣል፣ የልማት ሥራዎችንም ያበላሻል።
• የስራ ባህልንና ጥረትን ማጥፋት፦ ኩረጃ ሰነፍና ሰርቶ የመለወጥ ፍላጎት የሌለው፣ ሁልጊዜም ባቋራጭ መንገድ ለመበልጸግ የሚጥር ትውልድ ይፈጥራል።
• ፍትሃዊነትን ማስቀረት፦ ሌሊትና ቀን ደክመው ያጠኑ ጎበዝ ተማሪዎች እና ሳይማሩ የኮረጁ ተማሪዎች እኩል ሲመዘኑ፣ በትጋት የሚሰሩት ተስፋ ይቆርጣሉ። ይህ ደግሞ በቅንነት መስራትን ዋጋ ያሳጣል።
• አገራዊ እምነትና እውቅናን ማጣት፦ የአንድ አገር የትምህርት ሥርዓት በኩረጃ የተሞላ ከሆነ፣ ያ አገር የሚያወጣቸው የምስክር ወረቀቶች (ዲፕሎማ/ዲግሪ) በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናና እምነት ያጣሉ።
• ሌብነትንና ሙስናን ማስፋፋት፦ በትምህርት ቤት መኮረጅን የለመደ ሰው፣ ነገ ወደ ሥራ ዓለም ሲገባ መሥረቅን፣ ማጭበርበርንና ሙስናን እንደ ቀላል ነገር ነው የሚያየው።

ሙስናን እንፀየፍ!!
29/05/2026

ሙስናን እንፀየፍ!!

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፦እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልጽግና ይሁንላችሁ!!          ...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ፦እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልጽግና ይሁንላችሁ!!

​ዒድ ሙባረክ!

በሐስተኛ ሰነድ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ተቀጡ***********************(የአብክመ ስነምግባርና ፀረሙስና ደሴ ቅርንጫፍ ግን...
25/05/2026

በሐስተኛ ሰነድ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል የፈጸሙ ተከሳሾች በፅኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ተቀጡ

***********************

(የአብክመ ስነምግባርና ፀረሙስና ደሴ ቅርንጫፍ ግንቦት 17/2018) የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ዙፋን ደቦጭ ሀይሉ እና ወ/ሮ እልፋነሽ መልቁ ዱዬ፣ የመንግስት ሰነዶችን በሀሰት በመለወጥና በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ፈጽመው በመገኘታቸው በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጥተዋል።

ተከሳሾቹ ከከተማው መሠረተ ልማት መምሪያ ሠራተኞች ጋር በጥቅም በመመሳጠር የ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ግምት ያለውን 575 ካሬ ሜትር የድርጅት ቦታ በሀሰተኛ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እና የ99 ዓመት የሊዝ ውል የራሳቸው አድርገው ማህደር አዘጋጅተው ነበር።

በተከሳሽ ስም የተዘጋጀ የባለቤትነት ማህደር እንዲዘጋጅላቸውና ወደ መስሪያ ቤቱ እንዲገባ ካደረጉ በኃላ፣ በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም የተደረገ በማስመሰል የቤትና ቦታ ሽያጭ ውል በማዘጋጀት መሬቱን ወ/ሮ ዘቢባ መሀመድ ለተባሉ ባለሀብት ለማስተላለፍ በሂደት ላይ እያሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

​የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ክርክር ካደረገ በኋላ፣ ተከሳሾቹ እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ5 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

በሀሰተኛ ሰነድ የያዙት 575 ካሬ ሜትር መሬት ተወርሶ ወደ ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የመሬት ባንክ ገቢ እንዲሆን ብይን ሰጥቷል።

ንብረቱን ለመግዛት ውል አድርጌያለሁ በማለት በክርክሩ ጣልቃ ገብታ የነበረችው ባለሀብትም መብት እንደሌላት ተገልጾ ውሳኔው እስከ አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ መጽናቱን አሚኮ ዘግቧል።

የደቡብ ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ አቃቤ ህግ አቶ ምናለ ደርሶልኝ እንደገለጹት፣ ውሳኔው በሙስና የተገኘን የህዝብ ሀብት በተለያዩ መንገዶች ወደ ሶስተኛ ወገን በማስተላለፍ ህጋዊ ማድረግ ፈጽሞ እንደማይቻልና መሰል የወንጀል አስተሳሰብ ያላቸው አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙያ ሥነ ምግባርን በብቃት የተላበሰ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ  ተቋምን ለመገንባት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።🌿🌿🌿🌿🌿🌿 ግንቦት 15/2018 ዓ.ም(አብክመ ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.ደ.ቅ) የወልድያ ከተማ...
23/05/2026

የሙያ ሥነ ምግባርን በብቃት የተላበሰ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ተቋምን ለመገንባት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ።
🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ግንቦት 15/2018 ዓ.ም(አብክመ ሥ.ፀ.ሙ.ኮ.ደ.ቅ) የወልድያ ከተማ አስተዳደር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የስራ ቡድን ከከተማ አስተዳደሩ የሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ጋር በመቀናጀት በሙያ ሥነ ምግባርና የሙስና ወንጀል አስከፊነት ላይ ለቀበሌ መዝጋቢ ባለሙያዎች ፣ ለክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች እና ለመምሪያ ባለሙያዎች ሥልጠና ተሰጥቷል።

በሥልጠናው የከተማ አሥተዳደሩ የሥነ ምግባር መኮነን የሆኑት አቶ ይሁን ዋሱ በቃ በሥነ ምግባር ምንነት፣ የሙያ ሥነ ምግባር እና የሙስና ወንጀል አሥከፊነትና መዘዙ እንድሁም እንዴት መከላከልና ለዜጎች ተገቢ የሆነ ፣ ሕግን እና አሠራርን የተከተለ የሲቪል እና ቤተሠብ ምዝገባ መረጃ ምዝገባ መሥራት እንደሚጠበቅ ሥልጠና ሰጥተዋል።

ሰልጣኞችም የተሠጠው ሥለጠና ወቅቱን የዋጀ ከመሆኑም ባሻገር አውቀው በመተግበር አቅም እንደፈጠረላቸው ገልጸው አሁን ላይ ግን ዜጎች ሕግና አሠራርን ጠብቀው የልደት ፣ የጋብቻ እና ሌሎችንም ኩነቶች መረጃ ማግኘት እየቻሉ ሕገ-ወጥ ሰነዶችን እያሠሩ በሕግ ጥላ ሥር የዋሉ እንዳሉ ገልጸው እንደ መንግሥት የቀበሌ የመታወቂያ አሠጣጥ ሥርዓት መስተካከል እንዳለበት እንድሁም የሕገ ወጥ ህትመት መፈልፈያ ቦታዎችን አጥንቶ እርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል።

በሥልጠናው የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊና የአሥተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሰማየ ፈለቀ ሕገወጥ ሰነድን ለመከላከል በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ እቅድን በመፈጸም ግንባር ቀደም እንደሆነ ሁሉ መልካም ሥነ ምግባርን ተላብሶ ሕገ-ወጥነትን መከላከል ይጠበቃል በማለት የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል አቶ ሰማዬ ።

በስልጠናው የወልድያ ከተማ አስተዳደር የፕላን መማሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ወይነጥበብ ተ/ማርያም ፣ የገቢዎች ተቋማት የሥነ ምግባር መኮነን ወ/ሮ ሮዚና ካሣውን ተጨምሮ ሌሎች ሕገ-ወጥን ከመከላከል አንጻር የሚመለከታቸው አጋር አካላትም የተገኘ መሆኑን የወልድያ ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።

21/05/2026

Address

Shel
Dessie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anrs Ethics and Anticorruption Dessie Branch /የአብክመ ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮ/ደ/ ቅ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Anrs Ethics and Anticorruption Dessie Branch /የአብክመ ሥነምግባርና ፀረሙስና ኮ/ደ/ ቅ/:

Share