28/05/2026
የአካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ፤ ሁለንተናዊ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ የ5 አመት ጉዞ!
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከአጋር መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያንን መብትና ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ባለፉት 5 ዓመታት አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በተቀናጀ ጥረት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እና የተገኙ አውጤቶች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
⚖️ የመብት ማስከበር ስራዎች
የዜጎቻችንን ሰብአዊና ማህበራዊ መብቶች ከማስከበር አንጻር ጥሰት የደረሰባቸውን ወገኖች በመለየት የህግና የጥበቃ ስራዎች ተከናውነዋል፡-
3,054 (1,704 ሴት) አረጋዊያን የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ተለይቶ የማስከበር ስራ ተሰርቷል።
2,187 (1,155 ሴት) አካል ጉዳተኞች የደረሰባቸው የመብት ጥሰት ተለይቶ የማስከበር ስራ ተሰርቷል።
🤝 የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፎች
ለአካል ጉዳተኞችና አረጋውያን ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በርካታ ሁለገብ ድጋፎች ተደራሽ ሆነዋል፡-
የአካል ጉዳተኞች ተሃድሶና የስነ-ልቦና ድጋፍ፦
ለ38,130 (13,012 ሴት) አካል ጉዳተኞች የአካላዊ ተሃድሶ ድጋፍ፣
ለ162,319 (95,615 ሴት) አካል ጉዳተኞች የማህበራዊ ተሃድሶ ድጋፍ፣
ለ31,281 (16,319 ሴት) አካል ጉዳተኞች የስነ-ልቦና ድጋፍ ተሰጥቷል።
የአረጋውያን ድጋፍ፦
ለ556,688 አረጋውያን ልዩ ልዩ ቋሚና ጊዜያዊ የማህበራዊ ድጋፎች ተመቻችቶላቸዋል።
🏡 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና ሰብዓዊ ድጋፍ
የህዝባችንን የመረዳዳት እሴት በመጠቀም በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ታላላቅ ስራዎች ተከናውነዋል፡-
ከ7,740,951 በላይ የተቋማችን ደንበኞችን (ሴቶች፣ ህጻናት፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞችን) በማሳተፍ ከ397,866,084 ብር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።
ከ33,923 ለሚበልጡ አቅመ ደካሞች አዲስ ቤት የመገንባት እና የማደስ ስራ ተሰርቷል።
ለ505,351 ለሚደርሱ አቅመ ደካሞች ልዩ ልዩ ጊዜያዊ ሰብዓዊ ድጋፎች ተመቻችተዋል።
በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡት እነዚህ ውጤቶች የጋራ ጥረታችን ፍሬዎች ቢሆኑም፣ እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ካለባቸው ውስብስብ፣ ስር የሰደዱና ዘርፈ ብዙ ችግሮች አንጻር ገና ብዙ ሊሰሩ የሚገቡ ሰፊ ስራዎች መኖራቸውን ቢሯችን በሚገባ ይገነዘባል።
የአረጋውያንንና የአካል ጉዳተኞችን ዘላቂ ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ አሁንም ሰፊ ርብርብ ይጠይቃል።
በመሆኑም በቀጣይም ከተለያዩ መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ካልሆኑና ከአለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ያለንን ቅንጅት ይበልጥ በማጠናከር፣ ችግሮቹን በዘላቂነት ለመቅረፍ እና ሁለንተናዊ ተሳትፏቸውን ለማረጋገጥ በትጋት መስራታችንን እንቀጥላለን።
ልዩ ትኩረት ለአረጋዊያን እና ለአካል ጉዳተኞች