የደሴ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • የደሴ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ

የደሴ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ Welcome to Dessie City Woman Children and Social Affair Organization FB Page.

01/06/2026

ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!

ዛሬ ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች የታሪክ፣ የዲሞክራሲና የሉዓላዊነት ትልቅ ቀን ነው። እያንዳንዱ ድምፅ የነገዋን ኢትዮጵያ መልክ የሚቀርጽ፣ የሰላምና የልማታችንን መሠረት የሚያጠናክር በመሆኑ መምረጥ መብት ብቻ ሳይሆን የዜግነት ግዴታም ጭምር ነው።

ለሀገር ግንባታ፣ ለሕፃናት፣ ለሴቶችና ለጠቅላላው ማኅበረሰብ ዘላቂ ዕድገት ሲባል ሁላችንም በንቃትና በታላቅ የኃላፊነት ስሜት ድምፃችንን እንስጥ።

01/06/2026

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ድምጽ ሰጡ።

በባሕርዳር ከተማ ምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ፓርቲውን ወክለው በባሕር ዳር ከተማ ለክልል ምክር ቤት ዕጩ ኾነው የቀረቡት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በከተማዋ ድምጽ ሰጥተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ርእሰ መሥተዳድሩ ድምጽ የሰጡት በባሕርዳር ከተማ ግሽ ዓባይ በሚገኘው ሕዳሴ የምርጫ ጣቢያ ነው።

amhara prosperity

01/06/2026

የምርጫ ጣቢያ ሂደቶችን ቀድመን እንወቅ፤ ስርዓቱን ጠብቀን ድምጻችንን እንስጥ!

ነገ መላው ህዝባችን በነፃነትና በሰላማዊ መንገድ የዜግነት ድምፁን የሚሰጥበት የውሳኔ ቀን ነው።

ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ስናመራ፣ ሂደቱ ቀልጣፋ፣ ስልጡንና ሰላማዊ እንዲሆን በጣቢያው ውስጥ የሚኖሩትን ቅደም-ተከተሎች አስቀድሞ ማወቅ ጊዜያችንን ይቆጥባል፤ መስተጓጎልንም ያስቀራል።

እያንዳንዱ መራጭ ወደ ጣቢያው ከገባበት ቅጽበት ጀምሮ ድምፁን ሰጥቶ እስከሚወጣ ድረስ የሚከተላቸውን ግልጽና ደረጃ በደረጃ የተቀመጡ ሂደቶችን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖስተር አዘጋጅቶ ይፋ አድርጓል።

ይህ መረጃ ነገ ወደ ምርጫ ጣቢያ ከመሄዳችን በፊት የምናደርገውን ዝግጅት የተሟላ የሚያደርግና በጣቢያዎች ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ መጉላላቶችን የሚያስቀር ነው።

እባክዎ መመሪያውን በጥንቃቄ ይመልከቱ፤ ሂደቱን ጠብቀው በስነ-ስርዓት በመምረጥም ለሌሎች አርአያ ይሁኑ!

01/06/2026

ድምፃችንን በጥንቃቄ እንስጥ፤ ውድቅ ከሚሆኑ ስህተቶች እንጠበቅ!

ነገ ታሪካዊ በሆነው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ላይ በመሳተፍ የዜግነት አሻራችንን የምናሳርፍበት፣ የነገውን እጣ ፈንታችንን በነፃነት የምንወስንበት ታላቅ ቀን ነው።

ይሁን እንጂ በከፍተኛ ጉጉት የምንሰጠው ድምፅ ሙሉ ዋጋ ኖሮት ለውጥ እንዲያመጣ፣ በምርጫ ወረቀት አሞላል ላይ የሚፈጠሩ ጥቃቅን ስህተቶችን በጥንቃቄ ማስወገድ ይኖርብናል።

ካለማወቅ ወይም በጥንቃቄ ጉድለት የሚበላሹ ድምፆች እኛን ብቻ ሳይሆን ክልላችንንና ሀገራችንንም ጭምር ዋጋ ያስከፍላሉ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ወረቀታችን ውድቅ (ዋጋ አልባ) የሚሆንባቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች በዝርዝር የሚያሳይ ይፋዊ ማብራሪያ አዘጋጅቷል።

ነገ ወደ ምርጫ ጣቢያ ከመሄዳችን በፊት፣ እያንዳንዱ የጣላናት ድምፅ በትክክል መቆጠሩን ለማረጋገጥ ይህንን የቦርዱን መመሪያ በጥንቃቄ እንመልከት፤ ለሌሎችም እናጋራ።

01/06/2026
01/06/2026

ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም!

ነገ አገራችን ታላቅ ታሪክ የምትሰራበት የ7ኛው ብሔራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ዕለት ነው።

የጽሞና ጊዜ ህጋዊ ድንጋጌዎችን በአግባቡ በማክበር፣ ዛሬ በሀሳብ የምንረጋጋበት እና ነገ በሰላም ወጥተን ድምጻችንን የምንሰጥበትን ምቹ ድባብ የምንፈጥርበት ዕለት ነው።

ምርጫ ውበት የሚሆነው ፍጹም ሰላማዊ ሲሆን ብቻ ነው። የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶች እና መላው ማህበረሰብ የአካባቢያችንን ሰላምና ጸጥታ በንቃት በመጠበቅ፣ የነገው ታሪካዊ ቀን በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላችንን ታላቅ ኃላፊነት እንወጣ።

ሰላማችን የጋራ አሻራችን ነው!

01/06/2026

ኢትዮጽያ። ትመርጣለች !

ምርጫው ነገ ነው።

እርስዎም ድምፅዎን ሊሰጡ ይሄዳሉ። ነገር ግን ለምርጫ ሲሄዱ ወደ ምርጫ ጣቢያ እንዳይገቡ የሚከለከሉ ነገሮች አሉ። ለጥንቃቄ እንዲረዳዎ እነዚህን ነገሮች እናስታውስዎ:-

1. በራሪ ወረቀት፣ ፖስተር እና በሌሎች አጭር ጽሑፍ መልክ የተዘጋጁ የምርጫ ቅስቀሳ ሰነዶችን ይዘው ወደ ምርጫ ጣቢያው መግባት አይችሉም፡፡

2. የጦር መሳሪያ ወይም እንደጩቤና ሴንጢ የመሳሰሉ ስለትነት ያላቸውን ወይም እንደየአካባቢው ሁኔታ ለሀይል መጠቀሚያነት የሚውሉ እንደዱላ፣ አለንጋ ፣ ቁራጭ እንጨት ወይም ብረት ወይም ሌላ ማንኛውንም ተቀጣጣይ ወይም የሚፈነዳ ጠጣር ወይም ፈሳሽ ነገር ይዘው ወደ ምርጫ
ጣቢያ መግባት የለብዎትም።

3. የተከለከሉ ነገሮችን ወደምርጫ ጣቢያ ይዘው ከመጡ የምርጫ ጣቢያው የሰልፍ አስከባሪ በሚሰጥዎት መመሪያ መሰረት በአደራ አስቀምጠው መግባት አለብዎት።

ፋና ብሮድካስት

01/06/2026

" 'መንገድ ተዘግቷል' በሚል የሚራገበው ፕሮፖጋንዳ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ወሬ ነው" እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ የጸጥታ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል።

የምርጫ ቁሳቁስ በክልሉ በሚገኝ የምርጫ ክልሎች ያለምንም ጸጥታ ስጋት እንዲደርስ መደረጉንም አስታውቀዋል። መራጩ ሕዝብም በምርጫው ዕለት ያለ ምንም ስጋት ድምፁን መስጠት እንዲችል በየጣቢያዎቹ በቂ የጸጥታ ስምሪት ተደርጓል ነው ያሉት።

የጸጥታ ኀይሉ ሰላምን የማስከበር እና ደኅንነትን የማረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ መኾኑንም አስገንዝበዋል።

ከጸጥታ መዋቅሩ በተጨማሪ መላው ማኅበረሰብ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ በንቃት እየተሳተፈ መኾኑን አብራርተዋል። በተለይም ወጣቶች አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ለጸጥታ አካላት በመጠቆም ትልቅ እገዛ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

"መንገድ ተዘግቷል" በሚል የሚራገበው ፕሮፖጋንዳ የጽንፈኛ ኃይሉ የተለመደ የሐሰት ወሬ ነው፤ በዚህ ወቅት መደበኛ ሥራዎችም ኾኑ ወቅታዊ ተግባራት በአግባቡ እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

በዚህ ወቅትም በክልሉ የምርጫ ቁሳቁስ እና የአፈር ማዳበሪያ በተፈለገው አካባቢ ያለምንም ችግር እንዲደርስ እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል። ኅብረተሰቡም ለተለመደ የመንገድ ተዘግቷል የጽንፈኛ ኀይል የማደናገሪያ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ጀሮ ሳይሰጥ የእለት ከእለት ተግባሩን ያለምንም ስጋት እንዲከውን አሳስበዋል።

ግንቦት 22/2018 ዓ.ም

አሚኮ

25/05/2026
22/05/2026

ሴቶች ተጠቃሚነታቸውን በምርጫ ካርዳቸው ይወስናሉ!

ባሕር ዳር: ግንቦት 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የዴሞክራሲ ግንባታም ሆነ የሀገር ሁለንተናዊ እድገት ያለ ሴቶች ተሳትፎ ሙሉ ሊሆን አይችልም። ሴቶች ከሚሳተፉባቸው የፖለቲካ መድረኮች አንዱ ምርጫ ነው። ሴቶች ግንቦት 24 ለሚደረገው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።

የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዋ ሰናይት ጸጋዬ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመራጭነት ካርዷን ቀድመው ካወጡት ሴቶች መካከል አንዷ ናቸው።


ምርጫ የሴቶችን መብትና ተጠቃሚነት ለማስከበር ትልቅ መሣሪያ መሆኑን የምታምነው ሰናይት "ለሴቶች መብት ጥብቅና የሚቆምና የተሻለ አማራጭ ይዞ የመጣን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅቻለሁ" ስትል የነቃ ተሳትፎዋን ትገልጻለች።

ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ገነት መስፍንም በተመሳሳይ የምርጫን ጥቅም በመረዳት ካርዷን በቀዳሚነት ወስዳለች።

ምርጫ ሴቶች ድምፅ የመስጠት ብቻ ሳይሆን ወደ መሪነት የመምጫ መድረክ መሆኑን የምታነሳው ገነት ሂደቱ ሰላማዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻዋን እየተወጣች መሆኑንም ትናገራለች።

እነዚህ እናቶች ግንቦት 24 በንቃት እየጠበቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የአብክመ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዝና ጌታቸው እንደገለጹት በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሰፍን የሴቶች የምርጫ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሴቶች በአደረጃጀት ተዋቅረው ካርድ እንዲያወጡ ሰፊ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል።

በዚህም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የክልሉ ሴቶች በልዩ ሁኔታ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያሉት ምክትል ኃላፊዋ።

ተሳትፎው ከመራጭነት ባለፈ በዕጩነት፣ በተመራጭነት እና በታዛቢነት ጭምር መሆኑንም ጠቁመዋል።

"ካርድ ማውጣት ብቻውን ግብ አይደለም" የሚሉት ምክትል ኀላፊዋ ሴቶች በቀጣይም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ሊያረጋግጥላቸው የሚችለውን ፓርቲ በካርዳቸው ሊመርጡ ይገባል ብለዋል።

ምርጫው ሰላማዊ፣ ነጻና ፍትሐዊ እንዲሆን ሴቶች እያደረት ያለውን ሁለገብ አስተዋጽዖ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አሚኮ

Address

Dessie

Telephone

+251331124287

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደሴ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share