Kutaber woreda industry and investment office

Kutaber woreda industry and investment office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kutaber woreda industry and investment office, Government Organization, kutaber, Dessie.

08/06/2022
26/05/2022
ኑ! የደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳን በጋራ እናልማወረዳችን ኩታበር ከአገራችን ርዕሰ መድና አድስ አበባ በ421ኪ/ሜ ርቀት ላይ እና ከክልላችን ዋና ከተማ ባህር ዳር ደግሞ በ520 ኪ/ሜ ርቀ...
01/05/2022

ኑ! የደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳን በጋራ እናልማ
ወረዳችን ኩታበር ከአገራችን ርዕሰ መድና አድስ አበባ በ421ኪ/ሜ ርቀት ላይ እና ከክልላችን ዋና ከተማ ባህር ዳር ደግሞ በ520 ኪ/ሜ ርቀት ላይ እንድሁም ከደቡብ ወሎ ዞን እና ደሴ ከተማ ደግሞ በስተምስራቅ በኩል በ20ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ጥንታዊ ከተማ ነች፡፡
ከተማችን ኩታበር ውብ መልከዓምድርና ለኑሮ ተስማሚና ለኢንቨስትመንት ምቹ የአየር ንብረትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት ስትሆን ሰፊ የሆነ የእንሰሳት እና የደን ሃብት;የከበሩና ከፊል የከበሩ ማዕድናት በውስጧ የያዘች ባለ ብዙ ፀጋ ወረዳ ነች፡፡
ስለሆነም ጽ/ቤታችን ኑ! ወረዳዋን በጋራ እናልማ የሚል ጥሪውን እያስተላለፈ ወረዳችንን ለማልማት ሃሳብና ፍላጎት ያላችሁ የውስጥና የውጭ ባለሃብቶች ሊለማ የሚችል ሰፊ የተንጣለለ መሬት እና ሊያለማ የሚችል ሰፊ የተማረ የሰው ሃይል መኖሩን እየገለፅን ካፒታልና እውቀት ያላችሁ ባለሃብቶች ሁሉ ወረዳችን መጥታችሁ እንድታለሙ ጥሪያችንን እያቀረብን:-
የኩታበር ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1443ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን እየገለፀ በዓሉ የሰላም;የፍቅር; የአንድነትና የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቱ ነው፡፡
ኢድ-ሙባረክ
የኩታበር ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት

ቀን 10/07/2014የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በSMEFP ; በስነ-ልቦና ማነቃቃት እና በኢንተርፕራይዝ ልማት ላይ...
20/03/2022

ቀን 10/07/2014
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በSMEFP ; በስነ-ልቦና ማነቃቃት እና በኢንተርፕራይዝ ልማት ላይ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ለክልል; ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ;ዳይሬክተሮች; ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች በደሴ;በወልድያና በከሚሴ ከተሞች ከ10/07/2014 ዓ.ም ጀምሮ በወራሪው የትግራይ ሃይል የደረሰውን የስነ ልቦና ስብራት በመጠገን ለቀጣይ ቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራቶች መከናወን ያለባቸውን ተግባራቶች በውል ለይቶና በመልካም ስነ-ልቦና ወደ ስራ ለማስገባት የሚያስችል የስራ ስልጠና በደሴ ከተማ ሉሲ ሆቴል እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናው በቀጣይም በወልዲያ እና በከሚሴ ከተሞች ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮና ከኢንዱስትሪ ሚኒስተር ጋር በመተባበር በትግራይ ወራሪ ሃይል በአማራ ክልል በተለይም ደግሞ በ...
17/03/2022

የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮና ከኢንዱስትሪ ሚኒስተር ጋር በመተባበር በትግራይ ወራሪ ሃይል በአማራ ክልል በተለይም ደግሞ በኢኮኖሚው ሴክተር የደረሰውን የኢኮኖሚ ድቀት ሊያክም የሚችል የስነ-ልቦና ግንባታ የሚሆን የባለሙያ እና የአመራር የስነ-ልቦና ግንባታ ስልጠና በደሴ; በወልድያና በከሚሴ ከተሞች ከ10/07/2014 ዓ.ም ጀምሮ ስልጠና ለመስጠት በእቅድ እንደያዘ አስታወቀ፡፡

የውይይት መድረክ ተካሄደበወራሪው የትግራይ ሃይል የተጎዱ የምስራቅ አማራ አካባቢዎች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት በቀን 15/05/2014 በደሴ ከተማ አይጠየፍ አዳራሽ በተ...
24/01/2022

የውይይት መድረክ ተካሄደ
በወራሪው የትግራይ ሃይል የተጎዱ የምስራቅ አማራ አካባቢዎች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት በቀን 15/05/2014 በደሴ ከተማ አይጠየፍ አዳራሽ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተደድር ይልቃል ከፋለ(ዶ/ር);የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል; የጠቅላይ ሚኒስተሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው; የኢፌዴሪ የስራ-ዕድል ሚኒስተር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና ሌሎች የክልልና የዞን የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በዉይይታቸውም በወራሪው ሃይል ጉዳት የደረሰባቸውን እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታ ለመግባት በዝግጅት ላይ የነበሩ ባለሃብቶችን ደግፎ ወደ ስራ በማስገባት የተቀዛቀዘውን የክልላችን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት እና በአጠቃላይ በክልላችን ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ ለሚታዩ ማነቆዎች ላይ ተወያይቶ ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ ውይየት ነበር፡፡

Address

Kutaber
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kutaber woreda industry and investment office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share