ወይንአምባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ -Woin amba TVET College ሰራተኞች ገፅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • ወይንአምባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ -Woin amba TVET College ሰራተኞች ገፅ

ወይንአምባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ -Woin amba TVET College ሰራተኞች ገፅ የሚሰሩ እጆችን እንፈጠር!!

እንኳን ለብሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!
12/04/2026

እንኳን ለብሀነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም የስቅለት በአል!!
10/04/2026

መልካም የስቅለት በአል!!

01/04/2026
عيد مبارك!
20/03/2026

عيد مبارك!

05/03/2026

የሙያ ብቃት ምዘና ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ተደርጓል

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለምቶ ወደ ሥራ የገባው የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በውስጡ ከያዛቸው 23 ማይክሮ ሰርቪሶች መካከል ‹‹የሙያ ምዘና ሰርተፍኬሽን ›› አንዱ ነው፡፡

ይህ ሥርዓት ደረጃውን የጠበቀና የሙያ ብቃትን በትክክል ለመለካት በሚየስችል መልኩ ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ሆኖ መዘጋጀቱን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ፣ የሙያ ብቃት ምዘና ዴስክ ኃላፊ አቶ ምህረት ጥጋቤ ገልፀዋል፡፡

የዲጂታል ሥርዓቱ የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነት ያለበት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የምዘና መሳሪያዎችን የማዘጋጀትና ምዘናውን የማካሄድ፣ ክልሎች ሥርዓቱን የሚስተዳድሩበትን ፍቃድ የመስጠት፣ ከክልሎች የሙያ ብቃት ምዘና ሪፖርቶችን የመቀበልና አፈፃፀማቸውን የመከታተል ሥራ ይሠራል፡፡

የዲጂታል ሥርዓቱን በመጠቀም ተመዘኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም መመዝገብና ክፍያ መፈፀም የሚችሉ ከመሆኑም በላይ፤ ምዘናውን ባጠናቀቁ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀታቸውን ማግኘት መቻላቸው ሌላው የአገልግሎቱን ፍጥነትና ቅልጥፍና መገለጫ ነው፡፡

‹‹የሙያ ምዘና ሰርተፍኬሽን አውቶሜሽን›› ስርዓት ከሰው ንክኪ ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኖ የመዛኝ፣ የተመዛኝ፣ የምዘና ጣቢያና የሱፐርቫይዘር ምዝገባን በዲጂታል ሥርዓቱ ላይ በኦንላይን ብቻ የሚከወንበትን አሠርር ብቻ የሚከተል መሆኑ ከሙያ ብቃትና የሰርተፍኬት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ያስችላል፡፡

ማንኛውም ቀጣሪ ድርጅት የተቀጣሪዎቹን የሙያ ብቃት ምዘና ውጤት ትክክለኝነት ማረጋገጥ የሚችልበትን አገልግሎቱን አካቶ ይዟል፡፡

አንድ ጊዜ የተለካ የሙያ ብቃት ምዘና የሚያገለግለው ለሦስት ዓመት ብቻ እንደመሆኑ ተመዛኞች ጊዜውን ጠብቀው ብቃታቸውን እንዲያስመዝኑና ወቅታዊ ብቃትን እንዲላበሱ ከማድረግ አንፃርም ሥርዓቱ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አቶ ምህረት ጥጋቤ ያስረዳሉ፡፡

የካቲት 26/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI

30/01/2026
መልካም በአል!🙏🙏🙏
18/01/2026

መልካም በአል!🙏🙏🙏

የለገሂዳ ወረዳና አካባቢው እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!
12/01/2026

የለገሂዳ ወረዳና አካባቢው እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!

በድጋሜ የወጣ!!
23/12/2025

በድጋሜ የወጣ!!

የ2018 አጋማሽ የመውጫ ፈተና!  ለፈጣንና አዲዳስ መረጃ ቀጣዪን link ተጭነው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://t.me/woi123
20/12/2025

የ2018 አጋማሽ የመውጫ ፈተና! ለፈጣንና አዲዳስ መረጃ ቀጣዪን link ተጭነው የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! https://t.me/woi123

ለስራ ፈላጊዎች
18/12/2025

ለስራ ፈላጊዎች

✈️ውጪ ሀገር/UAE የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕድል

👉በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት በተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል።

👉አሁንም በዚሁ ህጋዊ የሥራ ስምሪት ወደተባበሩት አረብ ኤምሬትስ/UAE/ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የሰው ሃይል ይፈለጋል።

📌የኮንትራት ቆይታ:ሁለት አመት
📌ተፈላጊ ፃታ:ወንድ

🚧የሞያ ዘርፎች:-
1.Construction Laborers (የኮንስትራክሽን ሰራተኛ / ረዳት)
2.Mason(ግንበኛ)
3.እስቲል ፊክሰር (ፌራዩ)
4.Shuttering Carperter (አናፂ)
5. Delivery Boy (ሞተረኛ)
6. Walkers (እግረኛ ተላላኪ)
7. Plumber (የቧንቧ ሰራተኛ)
8. Electrician (የኤሌክትሪክ ሰራተኛ)
9. Scaffholders (የብረት መወጣጫ ባለሞያ)
10. Ductmen (የቬንትሌሽን ባለሞያ)
11. Supervisors and Foreman
12. Timekeepers (የሰራተኛ ሰአት ተቆጣጣሪ)
13. Camp Boss Assistant (የካምፑ አለቃ ተጠሪ)

☝️በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች ለመወዳደር https://forms.lmis.gov.et/triple-one-uae/ በመግባት ፓስፓርት፣ የሰራተኛ መለያ ቁጥር/Labor id/፣ የነዋሪነት መታወቂያ እና አስፈላጊ መረጃዎችን በማስገባት ከታህሳስ 08 እስከ ታህሳስ 14 2018 መወዳደር ይቻላል።

💰የትኬት፣ የጤና ምርመራ እና ቪዛ በአመልካቾች የሚሸፍኑ ወጪዎች መሆኑን እንገልፃለን። ሌሎች በስራ ቆይታ ላይ የሚያስፈልጉ የመኖርያ ቤት፣የማብሰያ ክፍልእና ከነማብሰያ እቃዎች፣ኢንሹራንስ እና የህክምና ወጪ በአሰሪው የሚሸፈኑ ወጪዎች ይሆናል።

✅ ለማንኛውም አስተያየትና ጥያቄ 9138 ነፃ የሥልክ መስመር ይጠቀሙ

ታህሳስ 9/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial
TikTok: tiktok.com/
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y

Address

Dessie

Telephone

+251924002866

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወይንአምባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ -Woin amba TVET College ሰራተኞች ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ወይንአምባ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ -Woin amba TVET College ሰራተኞች ገፅ:

Share