Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት The page is dedicate to promote developmental & democratic line of KWPP/kutaber woreda Prosperity Pa

26/05/2026
26/05/2026
26/05/2026
በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀሰን ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙...
26/05/2026

በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ሀሰን ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤

✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨

"የኢድ ውበቱ በምንለብሰው ሳይሆን፣ በምንካፈለው ፍቅር ይለካል!"

ኢድ አል-አድሐ ኢብራሂም ለአላህ ያሳዩትን ፍጹም ታዛዥነትና መስዋዕትነት የሚያስታውስ በዓል ነው። በእስልምና ታሪክ መሠረት አላህ ኢብራሂምን ልጃቸውን እንዲሠዉ በፈተና ሲፈትናቸው፣ እርሳቸው በሙሉ ታዛዥነት ፈቃደኛ ሆነው ነበር። ከዚያም አላህ በልጃቸው ፈንታ በግ እንዲሠዉ ያደረገበት ቀን ነዉ።

በዚህ የበረከት በዓል ላይ የተራበ ይጥገብ፣ የተቸገረ ይደገፍ፣ የተለያየ ይታረቅ፣ የተራራቀ ይቀራረብ። ደስታችን በፈገግታ ብቻ ሳይሆን በመካፈል ይብዛ፤ በረከታችንም በራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች በማድረስ የምናሳልፈዉ በአል በመሆኑ የበአሉ ዉበት
" በምንለብሰው ብቻ ሳይሆን፣ በምንካፈለው ፍቅር
ይለካልና!" በአሉ በጋራ በመተሳሰብ የምናሳልፈዉ በአል እንድሆን መልካም ምኞቴ ነዉ ሲሉ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን ለ1447ኛዉ አመተ ሂጅራ የኢድአል አድሀ አረፋ በዓል የ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

🌙 ኢድ ሙባረክ!

🌙መልካም የኢድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል! 🌙✨

"ዱንያ በሙሉ እንደ ዐረፋ ቀን የምትደምቅበት፣ አላህ በባሮቹ የሚመካበት፣ እዝነት እንደ ዝናብ የሚዘንብበት እና ወንጀል እንደ ቅጠል የሚረግፍበት ሌላ ቀን የለም"✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨የ...
26/05/2026

"ዱንያ በሙሉ እንደ ዐረፋ ቀን የምትደምቅበት፣ አላህ በባሮቹ የሚመካበት፣ እዝነት እንደ ዝናብ የሚዘንብበት እና ወንጀል እንደ ቅጠል የሚረግፍበት ሌላ ቀን የለም"
✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨🌙✨

የኩታበር ወረዳ ም/ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ይመር ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛዉ አመተ ሂጅራ የኢድአል አድሀ አረፋ በአል የ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፤

ኢድ አል-አድሐ የእምነት፣ የትዕግሥት፣ የመስዋዕትነት እና የመተሳሰብ እሴቶችን የምናስታውስበት የክብር በዓል ነው።
ይህ በዓል በሁላችንም ልብ ውስጥ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን እና በጎ ፈቃድን የምናሳይበትና ያየንበት የእዝነትና የምህረት በአል በመሆኑ "ዱንያ ላይ በሙሉ እንደ ዐረፋ ቀን የምትደምቅበት፣ አላህ በባሮቹ የሚመካበት፣ እዝነት እንደ ዝናብ የሚዘንብበት እና ወንጀል እንደ ቅጠል የሚረግፍበት ሌላ ቀን የለም" እንኳን ለዚህ ታላቅ ቀን የኢድአል አድሀ አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በአሉ
የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት እና የስኬት እንድሆንላችሁና በጋራ በመረዳዳትና በፍቅር አብሮነት የምታሳልፉት እንድሆንላችሁ እንድሁም ለሀገራችንም ዘላቂ ሰላምና እድገት እንድሰጥልን መልካም ምኞቴ ነዉ ሲሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

🌙✨ ኢድ ሙባረክ!

🌙✨ መልካም የኢድ አል-አድሐ (አረፋ) በዓል! 🌙✨

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kutaber Woreda Prosperity Party Office/ኩታበር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share