Mayor Office of Dessie City

Mayor Office of Dessie City Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mayor Office of Dessie City, Government Organization, dessie, Dessie.

በወቅታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መረጃ*****************የጤና ሚኒስቴር ለማኅበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና...
15/05/2025

በወቅታዊ የጤና አገልግሎት ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ መረጃ
*****************

የጤና ሚኒስቴር ለማኅበረሰባችን ጥራቱን የጠበቀ እና ፍትሐዊ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የጤና ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅረጽ የኅብረተሰቡን ባለቤትነት ባረጋገጠ መልኩ ሥራዎችን በትኩረት እያከናወነ መሆኑ የዐደባባይ ሐቅ ነው።

ምክንያቱም መቼምና በምንም ሁኔታ መቋረጥ ከሌለባቸው ማኅበራዊ አገልግሎቶች አንዱ የጤና አገልግሎት በመሆኑ፤ ስለዚህም ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናት በመላ ሀገራችን በሚገኙ የጤና ተቋማት እንደ ወትሮው ሁሉ መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ለማኅበረሰባችን ያለምንም መቆራረጥና መስተጓጎል እየተሰጡ ይገኛሉ፡፡

ይሄንን የተረዳው የጤና ባለሞያ በማኅበራዊ ሚዲያ በሚሠራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች ጫና ሳይገፋ የገባውን የሞያ ቃል ኪዳን እና መሐላ ጠብቆ ማኅበረሰቡን እያገለገለ በመሆኑ ምስጋና ይገባዋል፡፡

ይሁን እንጂ በጥቂት የማስተማሪያ የጤና ኮሌጆች/ተቋማት በመደበኛ የሥራ ገበታቸው ላይ ያልተገኙ የተወሰኑ ባለሞያዎች እንዳሉ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡ ከእነዚህ የጤና ባለሞያዎች መካከል ብዙዎቹ በሐሰተኛ መረጃ የተወናበዱ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ ጥፋትን ዓላማቸው ያደረጉ ናቸው።

ድርጊቱ የራስን ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ወገን እና መላውን ማኅበረሰብ ከመጉዳት ባለፈ ከሞያ ሥነ ምግባር፣ ከሰብአዊነት አኳያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

ከሕግ አኳያም የጤና ሞያ የሥራ ማቆም አድማ ከማይደረጉባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑ በግልጽ ተደንግጓል። የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ እንኳን ቢኖራቸው በሥራ ገበታቸው ተገኝተው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በመሆኑም እነዚህ የጤና ባለሞያዎች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ በየተቋማቸው ጥሪ ተደርጓል።

መንግሥት የጤና ባለሞያውን ዘላቂ ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ለመስጠት ቀደም ብሎ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1362 /2017 አጸድቆ ደንብና መመሪያዎችን በማውጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል።

በጎ ኅሊና ያላቸው የጤና ባለሞያዎች ይህንን በመገንዘብ ሥራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤታችን በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ ያቀርባል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኅብረተሰቡ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች በሚሠራጩ የሐሰት መረጃዎች ሳይረበሽ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት በተለመደው መልኩ በጤና ተቋማት ማግኘት እንደሚችል እናሳውቃለን ።

መንግሥት በሆደ ሰፊነት ችግሩን ለመፍታት ያሳየውን ትዕግሥት ወደጎን በመተው በሥራ ገበታቸው ላይ ባልተገኙ እንዲሁም በጤና ተቋሙም ሆነ ከጤና ተቋሙ ውጭ ሆነው ሁከትና ብጥብጥ በሚፈጥሩት ላይ አስፈላጊ የሆነ ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ቀድመን እናሳውቃለን፡፡

የጤና ሚኒስቴር

01/10/2024

"ሕግ የማስከበር ሂደቱ የሚቆመው የክልሉ ሰላም ሙሉ በሙሉ ሲረጋገጥ ነው" ኮሎኔል ጌትነት አዳነ

በክልሉ የተፈጠረውን የሰላም እጦት ለማስተካከል ሕግ የማስከበር እርምጃ እየተወሰደ ነው። የሕግ ማስከበር እርምጃውን በሚመለከት የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ መንግሥት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

በክልሉ ያለው የጽንፈኛ ቡድን የመከላከያን የቆየ ቁስል እየነካ እና ትዕግስቱን እየተፈታተነ የመጣ እንደ ነበር ይታወቃል ያሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ለሕዝብ ሰላም ሲባል ብዙውን ነገር በዝምታ አልፏል ብለዋል።

ለመከላከያ ሠራዊት የሚሰጠው ዝቅ ያለ ግምት፣ ስም ማጥፋት እና ማጠልሸት ከአማራ ሕዝብ ሥነ ልቦና የመነጨ እንዳልኾነ ሠራዊቱ ያውቃል ያሉት ኮሎኔል ጌትነት ሠራዊቱ ለሕዝብ ሰላም ሲባል ዛሬም ከኢትዮጵያዊነቱ ሳይወርድ ሕግ ያስከብራል ብለዋል።

የኦፕሬሽኑ ዓላማ ሁከትን እና ብጥብጥን አስወግዶ ለክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ ሰላምን ማስፈን ነው ያሉት ኮሎኔል ጌትነት አዳነ "ሕግ የማስከበር ሂደቱ የሚቆመው የክልሉ ሰላም ሙሉ በሙሉ ሲረጋገጥ ነው" ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት በጽንፈኛ ቡድኑ ላይ የሚወስደው ኦፕሬሽን የተጠና፣ አውድን የለየ፣ ጀሌን ከመሪ የነጠለ እና የቡድኑን ሴል በሚበጣጥስ መልክ የሚመራ ነው ብለዋል። ከሰሞኑ በከተሞች አካባቢ የተፈጸሙት እርምጃዎች ውጤት ያሳዩ ነበሩ ብለዋል።

መከላከያ የአማራን ሕዝብ ስለሚያከብር የክልሉ መንግሥት የጀመረው የሰላም ጥረት ዳር እንዲደርስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ያሉት ኮሎኔል ጌትነት ከመንግሥት ጋር በሰላማዊ መንገድ የሚነጋገሩ ካሉ በሮቹ ያልተዘጉ ቢኾኑም መከላከያ ግን ሕግ ማስከበሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ወታደራዊ ኦፕሬሽኑ በሚገባ የተጠና ነው ያሉት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው ንጹሐንን ለመጠበቅ ሲባል በጥንቃቄ ይመራል ብለዋል።

የማኅበራዊ ሚዲያው ጩኽት ግን የሚጠበቅ እንደኾነ ኮሎኔል ጌትነት ጠቁመዋል። በምንም መንገድ ቢኾንም ግን መንገድ ዝጉ እና ተማሪዎች አይማሩም ከሚል ጽንፈኛ ቡድን ጋር ከዚህ ያለፈ ትዕግስት አይኖርም ነው ያሉት።

አሚኮ

 #የደሴ ከተማ ውበት በምሽት
21/06/2024

#የደሴ ከተማ ውበት በምሽት

"አመራሩ በተሰጠዉ ተልዕኮ ልክ የመፈፀም አቅሙን በማጠናከር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ይገባዋል"አቶ አሸናፊ አለማየሁ የደሴ ከተማ ብልጽግ...
23/03/2024

"አመራሩ በተሰጠዉ ተልዕኮ ልክ የመፈፀም አቅሙን በማጠናከር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ይገባዋል"

አቶ አሸናፊ አለማየሁ
የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ቤት ኃላፊ

"ቃልን በማክበር በዘላቂነት እግር መትከል" በሚል መሪ ቃል የደሴ ከተማ የመምሪያ፣ የክ/ከተማና የቀበሌ አመራሮች ያለፉትን 8 ወራቶች የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ግምገመና የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ ዉይይት ተካሄደ።

በግምገማ መድረኩ ላይ በዕለቱ በክብር እንግድነት አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ የአብክመ ጤና ቢሮ ኃላፊና አቶ ወንድወሰን ጌታነህ የአብክመ የርዕሰ መስተዳደር የንግድና ፋይናንስ ጉዳዮች አማካሪ እንዲሁም አቶ አሸናፊ አለማየሁ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የደሴ ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ የመምሪያ አመራሮች፣ የክ/ከተማና የቀበሌ አመራሮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ አሸናፊ አለማየሁ ሲሆኑ በመልዕክታቸው እንደገለፁት አመራሩ በተሰጠዉ ተልዕኮ ልክ የመፈፀም አቅሙን በማጠናከር ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን ይገባዋል ብለዋል።

የከተማችን ህዝብ በምንፈጥራቸዉ የዉይይት መድረኮች የህግ የበላይነት እንዲከበርለት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮቹ እንዲፈቱለት በመጠየቅ የችግሩ ሰለባ ላለመሆንና ከጦርነት ትርፍ እንደማይገኝ በማመን አርቆ አሳቢነቱንና ለሰላሙ ባለቤት መሆኑን በተግባር አሳይቷል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ መድረክ በዋናነት የባለፉትን 8 ወራቶች የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎቻችን ላይ በጥብቅ የምንመክርበት መድረክ ነዉ ብለዋል አቶ አሸናፊ አለማየሁ።

የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸዉም እንደገለፁት በላፉት 8 ወራት የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በዘላቂነት ለህብረተሰቡ ዕዉን ማድረግ ላይ በስፋት ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ድልና ዕድል እየቀረ የመጣ በፈተናዎች ዉስጥ ነጥሮና ተፈትኖ ያለፈ ፓርቲ መሆኑን አቶ አብዱልከሪም ገልፀዋል። አያይዘውም ጥራት ያለዉ የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በማጠናከር ለህዝቡ እውነተኛ መረጃ መስጠት ላይ በስፋት መሰራት መቻል እንዳለበት ጠቁመዋል።

ባለፉት 8 ወራቶች የተከናወኑ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን አፈፃፀም ወ/ሮ አዝመራ ማስረሻ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቅርበዉ ዉይይት ተደርጓል።

የተፈጠረዉ መድረክ በዋናነት አመራሩ፣ አባላትና መላ ህዝቡ በክልሉ ዉስጥ የገጠመዉን የሰላም እጦት ችግርን ለመቀልበስ የተሰሩ የፀጥታ፣ የህዝብ ግንኙነት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠርና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ለመፈፀም የሚያስችል የጋራ ተልዕኮ በመስጠት የተረጋጋ ከተማና ክልል ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

አሁን ያለዉን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገር ለማድረግ በየደረጃዉ የሚገኘዉን አመራር፣ የፀጥታ አካላት፣ መላ ህዝብና መንግስት ሰራተኞችን የተለያዩ የዉይይት መድረኮች ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ በመፍጠርና የዉይይት መድረክ እንዲካሄድ በመደረጉ በአመራሩ በህዝቡ ዘንድ ቁርጠኝነት፣ ተነሳሽነትና ተስፋን በማለምለሙ በክልላችን በብዙ አካባቢዎች መደበኛና ወቅታዊ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማከናወን መጀመሩ ተገልጿል።

🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•~•~•

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ውሳኔ!የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ኮማንድ ፖስቱ በቀጠናው ፅንፈኛ ሀይሎች  ላይ እርምጃ  እየወሰደ በመሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው እና አካባቢው...
24/02/2024

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ውሳኔ!

የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ኮማንድ ፖስቱ በቀጠናው ፅንፈኛ ሀይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ በመሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው እና አካባቢውን በአጭር ቀናት ከፅንፈኛ ሀይሉ ነፃ የማድረግ ኦፕሬሽን ስራ ጀምሯል።

በመሆኑም ከ16/06/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከደሴ ወደ ሸዋሮቢት እና ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከደብረ ብርሃን ወደ ሸዋሮቢት እና ደሴ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቆም ስለወሰነ መላ ህዝቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና የፀጥታ ኃይሉም ውሳኔውን እንዲያስፈፅም አስታውቋል።

ማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት
ደብረ ብርሃን

🕊ሠላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊

የደሴ ከተማ  ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 39ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ።ደሴ:ጥር14/2016(የደሴ ከተማ ምክር ቤት ኮሙኒኬሽን )የደሴ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 39ኛ መደበ...
23/01/2024

የደሴ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 39ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ።

ደሴ:ጥር14/2016(የደሴ ከተማ ምክር ቤት ኮሙኒኬሽን )
የደሴ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ ዓመት 39ኛ መደበኛ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ህዝብ መዝሙር የተከፈተ ሲሆን የደሴ ከተማ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አህመድ ሙህየ በመክፈቻ ንግግራቸው ደሴ ከተማ ሠላምና መረጋጋት የሚታይባት ከተማ መሆኑዋን ገልጸው ከተማዋ የእድሜዋን ያህል እድገት ባይኖራትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በርካታ የልማት ስራ በመስራት ወደለውጥ መግባቷን ገልጸዋል።

በቅርቡም ለከተማዋ እድገትና የወደፊት የመልማት ራእይዋን ለማሳካት በኢክኖሚ የተሻለ ገቢ ለማግኘት የተጀመረው የፕሮጀክት እንዲሳካ ለማድረግ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጉ የከተማ አስተዳደር አመራሮች ምስጋናቸውን በምክርቤቱ ስም አመስግነዋል።

ለከተማችን እድገትም ከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሠላም በማስቀጠል፣ በህገወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል እየተደረገ ያለው እና ደንብን ከማስከበር ስራ እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሠራ ያለውን ስራ ቀጣይነት እንዲኖረው የምክርቤቱ አባላት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል።

ለ2ቀን በሚቆየው የምክርቤት ጉባኤም 37ኛውን መደበኛ ጉባኤ ቃለጉባኤ መርምሮ በማጽደቅ፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር የ2016የልማትና የመልካም አስተዳደር የ2ኛ ሩብአመት እቅድ አፈጻጸም ይቀርባል፣ የህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ረቂቅ ደንብ እንዲጸድቅ ለምክርቤት ውሳኔ ሀሳብ ይቀርባል፣የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እና የደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የውስጥ እዲት የስራ ሂደት የ2016የ2ኛ ረብ አመት አፈጻጸም ይቀርባል በመጨረሻም የከተማአስተዳደሩ ልዩልዩ ሹመቶች ቀርቦ ምክርቤቱ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ።

በጉባኤው ላይም የአፋር ምክርቤት አፈጉባኤዎች በእንግድነት ተገኝተዋል።

ሀገራዊ ክብርን የሚያረጋግጥ የውጭ ግንኙነት!ፓርቲያችን የውጭ ጉዳይን ከሀገር ውስጥ ጉዳይ የተነጠለ አድርጎ አይመለከትም። ይልቁንም የሀገር ውስጥ ጉዳያችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለ...
16/10/2023

ሀገራዊ ክብርን የሚያረጋግጥ የውጭ ግንኙነት!

ፓርቲያችን የውጭ ጉዳይን ከሀገር ውስጥ ጉዳይ የተነጠለ አድርጎ አይመለከትም። ይልቁንም የሀገር ውስጥ ጉዳያችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ነፀብራቅ ሆኖ ዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያልዘነጋ ነው።
የውጭ ግንኙነታችንም የዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ግንባታን የሚያረጋግጥ፤ የሀገር አንድነትን በማስጠበቅ ሀገራዊ ክብርን የሚያጎናጽፍ፤ ሀገራዊ ክብርን በማጎናጸፍ ሀገራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ይሆናል። ሀገራዊ ክብር የሌለው ሀገር ሀገራዊ ጥቅሙን ሊያስጠብቅ እንደማይችል ፓርቲያችን በጥብቅ ይገነዘባል።
በመሆኑም የኢትዮጵያን ታሪክ እና አንድነት እንዲሁም የዜጎቿን ክብርና ተስፋዋን የሚያንፀባርቅ የጋራ ስምምነት ያለው ሀገራዊ ክብርን እና ሀገራዊ ጥቅማችንን የሚያስጠብቅ የተቀናጀና የተማከለ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ትግበራን እውን ያደርጋል።
ሀገራዊ ክብራችንን ለማረጋገጥ እና ጥቅሞቻችንን ለማስከበር፣ አስቀድሞ ግንኙነትን በማደስና በማጠናከር ላይ ያተኮሩ ስራዎችን መስራት ላይ ትኩረት በማድረግ በግንኙነት ብልሽት ምክንያት የምናጣቸውን ሀገራዊ ጥቅሞቻችንን ለማስከበር አመች ሁኔታ ይፈጥራል።
በውጭ ግንኙነት መስክ ሀገራችን መልካም የሚባል ውጤት ያስመዘገበች ሀገር ብትሆንም የውጭ ግንኙነታችን ከጉድለት እና ከግድፈት የፀዳ አይደለም። ስለዚህ ግድፈቶቹን እና ጉድለቶችን መለየት፣ ማስተካከል እና መሙላት እንዲሁም የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠል የፓርቲያችን የውጭ ግንኙነት መሰረቶች ናቸው።

ከብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራም የተወሰደ ።

በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች ድጋፍ ተደረገ።የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጅ...
11/07/2023

በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ግለሰቦች ድጋፍ ተደረገ።

የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት ከደሴ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጅወች የቆርቆሮ እና ምስማር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፍ የተደረገላቸው ተጎጅወች በደሴ ከተማ አስተዳደር በገጠር ቀበሌወች ውስጥ የሚገኙ በጦርነት ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው 113 አቅመ ደካማወች ሲሆኑ 4000 ቆርቆሮ እና 560 ካርቶን ሚስማር ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተገልጿል።

Address

Dessie
Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mayor Office of Dessie City posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share