Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Dessie
  • Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት

Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት Strive for the prevalence of Justice!

30/05/2026
27/05/2026
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እና የደሴ ዙሪያ ወረዳ  ፍ/ቤት በጋራ በመሆን የባህል ፍ/ቤት ዳኞችና ፅሀፊዎች ስልጠና ሰጡ፡፡==========+=========+=======             ...
25/05/2026

የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እና የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በጋራ በመሆን የባህል ፍ/ቤት ዳኞችና ፅሀፊዎች ስልጠና ሰጡ፡፡
==========+=========+=======
ግንቦት 16-17/2018 ዓ.ም
ደሴ
⏩ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት እና የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት በጋራ በመሆን ለባህል ፍ/ቤት ዳኞችና ጸሀፊዎች ስልጠና አካሂዷል፡፡
⏩ሰልጠናዉን የደ/ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ትዕግስት ዳኛቸዉ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረዋል፡፡
⏩ የባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች የአማራ ከልል የባህል ፍርድ ቤቶችን ለማቋቋምና እዉቅና ለመስጠት ባወጣዉ አዋጅ ቁጥር 298/2017 እና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 23/2018 ላይ የስራ ማስጀመር ስልጠና ለመስጠት በጋራ ባዘጋጁት መድረክ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አድስና የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሙሎጌታ አያሌዉ በተገኙበት ስልጠናዉን ክቡር ዳኛ አቶ ደግዋለ ሐይማኖት በአዋጁና መመሪያ ላይ ስፊ የሆነ ማብራሪያነ ገለፃ በማድረግ ስልጠናውን ተሰጥተዋል ።
⏩ አክለዉም ለሰልጣኞች የመወያያ ጥያቂዎችን በመስጠት በቡድን እንዲወያዩ በማድረግ የደረሱበትን ሐሳብ በዝርዝር አቅርበዉ በተጨማሪም በርካታ ጥያቂዎችን በማንሳታቸዉ ከሰዓት ብኋላ ባለዉ ጊዜ ሰፊና ገንቢ የሆነ ዳበረ ሐሳብ በማንሳት ዉይይት ተካሂዷል፡፡
⏩ በመጨረሳም የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ሽምልስ አድስና የደሴ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት ፕሪዝዳንት አቶ ሙሎጌታ አያሌዉ በስልጠናዉ ለተነሱ ሐሳብና አስተያየቶች ሰፊ ገላፃ በመድረግ፣ በስራ ላይ ም ለሚያጋጥ ችግሮች አብረዉ ከጉናቸዉ በመሆን እንደሚሰሩና በስልጠናዉ የተሳተፎትን በማመስገን የማደማደሚያ ሐሳብ በመስጥት የእለቱ ስልጠና በሰኬት ተጠቋል፡፡

የደሴ ከተማ የህ/ግንኙነት ዋና የስራ ሂደት

24/05/2026
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አስተዳደር የዳኝነትና ፍትህ አካላት ቴክኒክ ኮሜቴ የትብብር መድርክ  ዉይይት አደረጉ ፡፡============================            ግንቦት 13...
22/05/2026

የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አስተዳደር የዳኝነትና ፍትህ አካላት ቴክኒክ ኮሜቴ የትብብር መድርክ ዉይይት አደረጉ ፡፡
============================
ግንቦት 13/2018 ዓ.ም
ደሴ ከተማ ህዝብ ግንኙነት
⏩ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት አስተዳደር የዳኝነትና ፍትህ አካላት የቴክኒክ ኮሚቴ ትብብር መድረክ የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የወንጀል ስራ ሂደት አሰተባባሪና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አዕምሮ በየነ ውይይቱን አስጀምረዋል ፡፡
⏩ በዉይይቱ የተሳተፎት የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት፣ የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ፣የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊስ መምሪያ የደሴ ከተማ አስተዳደር 1ኛ፣2ኛ፣3ኛ4ኛ እና 5ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የምርመራ ክፍል ሐላፊዎች እና አቀራረቦች የደቡብ ወሎ ዞን ማረሚያ ቤት በጋራ በመሆን በተሰሩ ስራዎችና ባጋጠሙ ችግሮች ፣በወቅታዊ ጉዳዮች፣ በደራሽ ስራዎችና በተዘጉ መዝገቦች ላይ ስፊ ወይይት አደረጉ፡፡
⏩ ለዕለቱ ዉይይት እንደተገለጸው በ2 ወሩ ዉሰጥ በሁሉም ጣቢያዎች 25 መዝገብ ተከሳሽና ምስክር ባለመቅረብ መዘጋቱን፣በዋስትና አፈቃቀድ እነ በጊዜ ቀጠሮ ጥያቄዎች ዙሪያ ሰፊ ሐሳቦችን በማንሣት ተወያይተዋል ።

⏩ በተጨማሪም ተወያዩቹ ከሁሉም ጣቢያ የመጡት የምርመራ ክፍል ሐላፊዎችና አቀራረቦች በተነሱት ነጥብ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የተሰሩ ሥራዎችን በጥንካሬና በድክመት የታዩትን በዝርዝር በማነሳት ለወደፊቱ በመናበብና በትብብር ጠንክረዉ እንሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
⏩ በመጨረሻም ወቅታዊና ደራሽ ስራዎች በመደበኛዉ ስራችን ላይ ጫና ቢፍጥሩም ስራችንን ወቅቱን የዋጀ ሥራ እየሰራን ችግሮችን በጋራ እየተወያየንና መፍትሄ እየሰጠን በመሥራት በወጣዉ ፕሮግራም መሰረት እየተገናኘን በመዉያየትና በመናበብ መስራት አለብን በማለት የእለቱን ዉያይት በስኬት ተጠናቋል ፡፡
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ህዝብ ግንኙነት

Address

Dessie City
Dessie

Telephone

+251331125072

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Dessie City Administration Woreda Court/የደሴ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍ/ቤት:

Share