31/05/2026
የከላላ ወረዳ ፍ/ቤት ለባህላዊ ፍ/ቤት ሽማግሌዎችና ፀኃፊዎች የአቅም ማጎልበቻና የስራ ማስጀመሪያ ስልጠና ሰጠ።
===============//==========
ግንቦት 20/2018 ዓ.ም
*********************
የከለላ ወረዳ ፍ/ቤት ከከለላ ወረዳ አስ/ር፣ ከከለላ ከተማ አስ/ር ፣ከከለላ ወረዳ መሬት ጽ/ ቤት ጋር በመተባበር በከለላ ከተማ እና በወረዳው ገጠር ቀበሌዎች በሚገኙ #10 ቀበሌዎች የባህላዊ ፍ/ቤት ሽማግሌዎችና ጸሀፊዎች የአቅም ማጎልበቻና የስራ ማስጀመሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
የስልጠና መድረኩ የክብር እንግዳ የነበሩት የከለላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ደምሴ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ ይህ ስርዓት መዘርጋቱ በወረዳዉ፣ በከተማአስተዳደሩ ብሎም በሀገር ሰላም፣ደህንነትና መረጋግት እንዲኖር የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።አክለውም ማህበረሰቡ ባህሉን፣ወጉንና እሴቱን በማስጠበቅ እንዲኖርና የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን በሽማግሌዎችና ሀይማኖት አባቶች በመፍታት፣የማህበረሰቡን ግንኙነት በማጠናከር ህብረተሱቡ የልማት፤የእርሻ ስራው ላይ እንዳተኩር በማድረግ ለሀገር እድግትና ሰላም መምጣት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የከለላ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አውነቱ አምባው በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የባህል ፍርድ ቤቶች ከመደበኛው የሕግ ሥርዓት ጎን ለጎን ፍትሕን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ያላቸውን የማይተካ ሚና ገልጸዋል።
በህጉ የተቀመጡትን መሰረታዊ መብቶችንና መርሆዎችን በማክበር፡ እውነታው ላይ ለመድረስ እና ጉዳዮችን ለመፍታት ለዘመናት በባህል የዳበረውን ጥበብን መጠቀም ከባህል ፍ/ቤት ሽማግሌዎች የሚጠበቅ መሆኑን አሳስበው፤የተዘጋጀው ሥልጠና ዋና ዓላማም አሠራርን በማዘመን የባህል ዳኝነቶች በሰነድ አያያዝ እና ተግባራትን በዘመናዊና ስልታዊ መልኩ እንዲሰሩ ለማስቻል፤ ከመደበኛው የዳኝነት ስራ ጋር የተናበበና የተቀናጀ ሥራ በመስራት ማኅበረሰቡ በዝቅተኛ ወጭ በአጭር ጊዜ በአቅራቢያው ተደራሽ የሆነ የደኝነት አገልግሎት እንዲያገኝ ማስቻል መሆኑን አብራርተዋል ።
የስልጠናውን ሂደት አስመልክቶም አስተያየታቸውን የሰጡ አጋርአካላት መካከል፡-
✍የከለላ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ኃላፊ ወ/ሮ አለም በበኩላቸው፣የከለላ ወረዳ ፍ/ቤት የባህል ፍርድ ቤቶችን ከማቋቋም ጀምሮ ለማጠናከርና ዓላማውን ከግብ ለማድረስ አብሮ በመስራት ረገድ እስከ አሁን ድረስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝና ወደፊትም ድጋፉ ተጠናክሮ እንሚቀጥል አሳስበዋል።
፣ ይህ የሽምግልና ዳኝነት ስራ በማኅበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ እና አመኔታ የሚጣልበት ኃላፊነት በመሆኑ እና በወጣው ህግ ማዕቀፍ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ በቀጣይነት እንደሚያደርጉ ለሰልጣኞች አሳስበዋል።
🔹የወረዳው መሬት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ እንድሪስ ሙህዬ በበኩላቸው ይህ አዋጅ የመሬት ግጭቶችን በቀላሉ ለመፍታት፣ሴቶችን፣ህጻናት፣ድጋፍና ትኩረት የሚሹ አካላትንም የመሬት ተጠቃሚ እንድሆን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል
✔️በስልጠናው መጠናቀቂያም ላይ የሥልጠናው ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያት አቅርበው ስልጠናውን በሰጡት አሰልጣኝና በፍርድቤቱ ፕሬዘዳንት በጋራ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠባቸውሲሆን፣ሰልጣኞች
በሰጡት አስተያየት፣ የተሰጠው ሥልጠና ግልጽና ከበቂ ማብራሪያ ጋር የተሰጠ መሆኑ የሕግ ግንዛቤያቸውን እንደሚያሳድግላቸው ገልጸዋል።
በመጨረሻም የስልጠና ሰነዱ፣አዋጆችና መመሪያዎች በየቀበሌያቸው እንደሚላክላቸው፣ቢሮና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ የቢሮ ግብአቶችን በየቀበሌያቸው ሊቀመንበሮች በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ እንደሚያመቻች ቃል የተገባ መሆኑ፣ ምላሽ ተሰጥቶ፣የፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት ክቡር አቶ እውነቱ አምባው ስልጠናው በስኬት እንዲካሄድ አስተዋፅኦ ያደረጉትን የከለላ ወረዳ አስተዳደር፣ የከለላ ከተማ አስ/ር ፣የከለላ ወረዳ መሬት ጽ/ ቤት ፣የከለላ ወረዳ ግብርና ጽቤት እና የየቀበሌ አስተዳደሪዎች በወረዳ ፍርድ ቤቱ ስም የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበው፡መሰል ድጋፎችና ትብብሮች ስራን በቅንጅት መስራት ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበው የዕለቱ ስልጠና ፕሮግራም በስኬት ተጠናቋል።
የዕለቱን ስልጠና የሰጡት የከለላ ወረዳ ፍርድ ቤት ዳኛ የሆኑት ክቡር አቶ ሚካኤል አስራት ናቸው